Showing posts with label ሐይማኖት. Show all posts
Showing posts with label ሐይማኖት. Show all posts

Apr 30, 2019

የዲያቆን ኄኖክ ኃይሌ ሕማማት መፅሐፍ ዳሰሳ

የሕማማት መፅሐፍ አጭር የግል ምልከታ::


(ተስፋ በላይነህ)


ዲያቆን ኄኖክ "ሕማማት" የተሰኜውን ድንቅ የፍልስፍና መፅሐፍ ሲፅፍ የተሰማኝ ጉዳይ ቢኖር :- አምላክ በየትኛውም ዘመን ቢሆን ቃሉን ሊገልፁልን የሚችሉ ደቀመዝሙራትን በየትኛውም ጊዜ እንደሚዘክረን ማስመስከርያ ነው:: 


በበኩሌ የተሰጠኝን አዕምሮ እጠራጠረዋለሁ:: እያንዳንዷን የእግዚአብሔር ቃል በጥያቄ እና ዝርዝር ሀቲቱን አውቅ ዘንድ በምርምር ስሌት አነባለሁ:: አንኳኳለሁ ፅድቁን እሻለሁ:: ነገር ግን በስጋዊ አዕምሮዬ ጠይቄ በስጋዊው አዕምሮዬ መልሱን እንዳልመልስ ስለምፈራ የእግዚአብሔርን መንፈስ ቅዱስ እማፀናለሁ:: ነገር ግን ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ቅርበት የትየለሌ ክንዶችን የራቅሁኝ ርኩስ ሰው ነኝ:: በፆም በፀሎት:: በስአታት ምልጃ እና ንሥሃ እንዲሁም ለቅዱስ ቁርባን ያልበቃሁ ጭንጋፍ ስለሆንኩ የእግዚአብሔርን ቃል ራሴው ጠይቄ ራሴው እንዳልመልስ ራሴው ስለሚጠይቀኝ:: ራሴን አላምነውም:: 


በዚህ ማንነቴ ውስጥ ሆኜም ቢሆን የማይጥለኝ ጌታ ፥ በዚህ ድኩማንነቴ ውስጥም ሆኜም የማይተወኝ አምላክ ፥ አልፎ አልፎ ትጉሃን ሰባኪዎችን ፀሀፊ ዲያቆን ካህናትን ይሰጠኛል:: የማይተወኝ አምላክ በሄድኩበት ሁሉ ተአምር ድንቅ የማዳን ስራውን ሸሽጎብኝ አያውቅም:: የምሸሸገው እኔው ብሆንም ቅሉ:: ያቺን የቃዬል ድንጉጥ አይነት መሸሸ:: 


በሚያዝያ 2011 አ.ም የሁዳዴ ፆም ለንባብ የፈቀድሁት መፅሐፍ "ሕማማት" የተሰኜውን ነው:: መፅሐፉን ከዛሬ ሁለት አመት በፊት ለሕትመት እንደበቃ አንድ ወዳጄ ገዝቶት ለማንበብ ሞክሬው <<ከብዶኝ>> የተውሁት ነበር::


መንፈሳዊ መፅሐፍትን የመረዳት ዝንባሌ የራሱ የሆነ ወቅት ፥  የራሱ የሆነ ኃይል  ፥ ጊዜና ቦታ ይፈልጋል:: አንድ አማኝ የመንፈሳዊ መፅሃፍትን የመረዳት አቅሙን እና ዝንባሌውን ፈቃድ ፥ ቁርኝቱን በመመልከት ብቻ ራሱን ሊመዝን ይገባዋል:: የዛሬ 15 አመት አንድ የመፅሃፍ ቅዱስ ቃል አንብቤ ምንም አይነት ትርጉምም ይሁን ፍቺ ላገኝ የምችልበት ሁኔታ ላይ አልነበርሁም::


አይደለም አንድ ምእራፍ አንድ ገፅ እንኳ አነብንቤ (አንብቤ ላለማለት) ስዘጋው የምረዳው አንዳች ነገር አልነበረም:: ልቤ ምን ያክል ደንዳና እና ለቃሉ ያን ያክል "ዝግ ዓለት" እንደነበረ  ማሰብ አያዳግትም::


በጊዜው እንዲህ ነበር:: የጌታ ፈቃድ ሆኖ መፅሐፍ ቅዱስን በማንበብ ቢያንስ ለጠያቂ አዕምሮ ባለቤትነት መሰጠትን መታደል ትልቅ እድለኝነት ነው:: ደንዳና ልብን እንደመስበር የሚሰጥ እድል ፈንታ ቀላል የሚባል በረከትም አይደለም:: 

"እነሆ በድጅቆሜ አንኳኳከለሁ..." የሚለው ጌታ የማንኳኳቱን ድምፅ ችላ ያልነው ስንቶቻችን ነን? 


የተሰበረ ልብ ፥ የተሰነጣጠቀ ልብ ልክ እንደ "ሰፍነግ" መልሶ ቆምጣጣ እና መራራ ፥ መርዛማ ምድራዊ ክህደቶችን ፥ ጥላቻ ስንፍናዎችን እንዳይሞላም የዘወትር ጥንቃቄን የሚጠይቅ ዓቢይ ጉዳይ ነው::


ልባቸው ተሰብሮ ፥ ለተጠሙ የሚያዝኑ የነበሩ ባልታወቀ የህይወት መስመር ሳቢያ እጅግ ጨካኞች ፥ እጅግ ዘማዎች ፥ እጅግ ክፉዎች ሲሆኑ ታይተዋልና ትልቅ ጥንቃቄን የሚጠይቅ የህይወት መዳረሻ ይህ መስመር ነው:: የተሰበረን ልብ መጠገኛ ወጌሻውን የመምረጥ ጉዳይ!!


በተሰነጣጠቀ ልብ ውስጥ ስጋዊ እና መንፈሳዊ ኃይላት እየተፈራረቁ መሻማታቸው አይቀርም:: የህይወት ግቡ ልብን መስበር:: የተሰበረውን ልብ በብርሃን ጫጩት አስፈልፍሎ ለብቁ ንስር ወፍ እንዲበቃ ማስቻል ነው:: 


አልፎ አልፎ ወቅቱ በፈቀደ መጠን የእግዚአብሔር ድጋፍ ያልተለያቸው የሃይማኖት መንፈሳዊ መሪዎች ብቅ ይላሉ:: በእርግጥ በየትኛውም ዘመን በየትኛውም ክፍለ አለም እነዚህ ስዎች አሉ:: ጉዳዩ የኛ አይን እነዚህን ሰዎች ፈልጎ የማግኜት የምርጫ እድል ፈንታን መውሰድ ትልቁ ድርሻችን ሊሆን ከተገባው ነው:: 


እንደኔ አይነት በጥያቄ አዕምሮ ለተሞሉ ጭንጋፎች ገለባነታችንን የሚነግሩን መንፈሳዊ መምህራን በየቦታው አሉ:: 


እያንዳንዷን የእምነት ነክ ታሪክ ፥ ክስተቶች እና ቅዱሳት መፃፍት ላይ የተከሰቱ ድርጊቶችን በጥልቅ ትንታኔ ፥ በድብቅ ውብ ምስጢራት ፍቺ ፥ ትርጓሜ እና ተያያዥነትን አመሳክሮ የሚመግብ ፥ ልብን ሰብሮ ብርሃናዊ ወበቅን በስንጥቁ ልሙላ የሚል ፀሐፊ ምንኛ ማለፊያ ምንኛ ባይለጠጋስ ነው? 


በዚህ አገላለፅ ዲያቆን ኄኖክ ኃይሌ የክርስቶስን የሕማም ጉዞ እያንዳንዷን ክንዋኔ ምስጢር እና ፍቺ ከብሉይ ፥ ከቅዱሳን ድርሳናት እና ከአበው ትውፊታት ጋር እያዋዛ ለደንዳና ልብ ሊሆን ዘንድ የተመረጠን "ማሽያ" የታመመ "ወለምታ ልብን" ይፈውሳል:: 


በክርስቶስ ሕማም ወቅት የተደረጉ ታላላቅ ንግርቶችን ጥቃቅን ኩነቶችን እና ምሳሌዎችን ከመዳናችን ምስጢር ጋር እያጣበቀ ቤዛችንን በጉልህ ያቀርብልናል:: 


"እኔስ ትል ነኝ" የሚለውን የዳዊት መዝሙር ክርስቶን በስቅለቱ ወቅት "አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ?" ኦሎሄኦሎሄ ላማ ሰበቅታኒ  የሚለውን ቃሉን ይዞ ፥ የልበ አምላክ የዳዊት 21ኛ መዝሙር ጋር አቆራኝቶ ፥ ለስጋ አዕምሮ የሚደንቀውን የሰው ልጅ የድኅነት ድንቅ ተአምር በ"ቪዝዋላይዥሽን" አብርቶ ያቀርብልናል:: 





ክርስቶስ ትል ሆኖ ፥ በአሳ የተመሰለውን ዲያቢሎስን በመስቀሉ መቃጥን ላይ ወጥመዱን አነጣጥሮ ፥ ክርስቶስ ነፍሱን ከስጋው ሊለይ ሲል ፥ ሊጨልፍ የተጠጋውን አሳ (ዲያቢሎስ) ፥ "ትል አገኜሁ" "የሰው ስጋ በላሁ" ሲል በወጥመድ መቃጥን ውስጥ የተጠመደውን ዲያቢሎስ አያያዝ ፥ ለእስር መዳረግ ተንትኖ ያቀርብልናል:: ይህ ለአዕምሮ የሚከብድን ዘመን አይሽሬ ትዕይንት ዲያቆን ኄኖክ ኃይሌ በቀላል አማርኛ ሳያንዛዛ እንደ ህፃን ወተት ይግተናል:: 


ከዚህ በላይ ዋጋ ከዚህ በላይ ድኅነት ከዚህ በላይ ድንቅ ምስጢር ከዚህስ በላይ አቀራረብ ከወዴት ይገኛል? ስንል አፋችንን ፥ ጭንቅላታችንን ፥ አደብ የለሽ አንደበታችንንም ልንይዝ እንገደዳለን:: 


ብቻ ልባችን ከዘመነኛ የክህደት ትምህርት የኑፋቄ ግኖስጣዊያን ረብ የለሽ ፍልስፍና ስር ወድቀን ፥ ሰባራ ልባችንን ክፉኛ መርዘን ፥ የዲያቢሎስ ፈረስ እንዳንሆን ወደ ፈትና እንዳንጣል ዘንድ "የሕማማቱን" ስእል ትርጉም እና ምስጢር በህይወት ዘመናችን ኹሉ እንከትበው ዘንድ ዲያቆን ኄኖክ "እነሆ!" ብሎናል:: 


ልብ የሕይወት መውጫ ነውና አጥብቀን እንጠብቀው ዘንድም ተነግሮናልና ፥ መውጫ መግቢያውን በጥንቃቄ እናሰምር ዘንድ የነፃ ፈቃድ አምላክ እድል ፈንታውን ችሮናልና:: ከሕማማቱ:: ከሞቱ:: ከትንሣኤው:: ከትንሣኤ በኋላ ያሉት ዕለታትንም ፥ ማዕዶት ፥ ቶማስ ፥ አልዓዛር ፥ አዳም ፥ ቤተ ክርስቲያን ቅዱሳት አንስት ፥ ዳግማዊ ትንሣኤ:: እስከ ምፅዓት እለተሞታችን ድረስ ልንይዘው የሚገባን ትምሕርት መሆኑን የዚህ ኅፂር ፅሁፍ ፀሐፊ ምስክርነቱን ይሰጣል:: 


"ለልብ ጠበቃ ይሆኑልን ዘንድ የሚመላለሱ ጙቤኛዎችን(ጠባቂዎችን) አምላክ አይንሳን" እያልን:: የአገልግሎት ዘመናቸውንም ያብዛልን:: በቤቱም አያርቃቸው:: ድንቅ ተአምራትህን ያሳዩን ዘንድ የኛንምልብ ስበር የእነርሱንም ፀጋ አብዛላቸው ...:: ይሁን:: አሜን! እያልን:: እንማፀናለን::


(መፅሃፉን ተርኮ በዩቱብ ላቀረበው እዮብ ዮናስ ምስጋና ይግባው!!)


ወስብሃት ለእግዚአብሔር::




Nov 27, 2014

Lucy!

Lucy!
“... The man said, I was afraid, I was naked so I hid.” Genesis 3:10
Starting from the name “Lucy” came to my mind, as an Ethiopian and the scientists claiming Ethiopia as the "cradle of mankind", for me Lucy was just a name!

After many Years realizing the history of Ethiopia, we End up the 1966 (Ethiopian calendar) in which so many things has happened in this year. It was simply after 33 years of the king Hailesilassie came from London by the help of English war leaders Sanford and Wingate. The militarily Junta DERG came to power in 1966 E.C /1974 G.C/ and For the first time in Ethiopian History, Ethiopia become in the hand of anti religious system and became a `socialist` country! Let the history writers’ study the event and we will jump to our Conspiracy theory on the name LUCY!

Lucy was found in 1967 E.C/1974 G.C/ by the famous English archaeologist Donald Johansson in Afar, north east of Ethiopia. The name Lucy was given because they were listening the Beatles song called LUCY THE SKY WITH DIAMONDS. As they say!

If you really are curious for the things happened in the past and ask why? How? And some other human questions, you may get so many reasons and evidences to show yourself the truth behind all histories. Not an easy thing any way!

One is because we are manipulated and sharpened like a pencil that they want to write anything they want on our history papers. We are what they want; we read what they wanted us to write, we write what they wanted us to read. And we will never believe what others tell us. The king of pop, M.J said one historical testimony about it: “They manipulate our history books. The history books are not true, it’s a lie. The history books are lies. You must know that… this is all complete conspiracy.”

Here we are in the history of Lucy: as they say more than 3.4? million years back, Evolution has got a proof that we are evolved from this apelike creature and the missing link was found which Lucy is!
Lucy in Latin word means Light! And the name Lucy has many interpretations in different places. I have tried to see the lyrics THE SKY WITH DIAMONDS (LSD) and thanks for my age celebrities Rhihana and Miley cirus, They played what Lucy and diamonds were meant to be. See `Sky with diamonds` by Miley Cyrus (https://www.youtube.com/watch?v=a77SVKEXLQE) and `shine like a diamond` by Rihana {https://www.youtube.com/watch?v=lWA2pjMjpBs}.

For me Lucy is the LUCIFER: As they believe he is the god and the one who brought knowledge and freedom to the human beings. Remember Donald Johansson wrote his book after the finding of Lucy, his book titled LUCY: THE BEGENING OF HUMAN KIND. That was for a purpose.

It makes me to write it in my blog after I watched the movie Lucy! It is the movie that shows how Darwin’s theory be presented in a way that all people in the world now could accept his Evolutionary theory, with the help of Einstein’s E=MC2.

We will right away see with the eyes that they gave us as our mind sees what they wanted us to see, we see the beauty of Scarlet Johansson not the secret behind the message of the movie. We only see the technology, the violence, the action, the suspense- not the teachings of how we can use our knowledge and become gods!
Remember: the beginning of sin was tricked by the snake. As the bible says “The snake was the cleverest of all the wild animals that Lord God had made”. After the trick questions we always know from the bible given to Eve, the snake said to the women that “You will not die. God knows that if you eat the fruit from that tree you will learn about good and evil. And you will be the same as God!” Genesis 3:5
This is it; this is how all starts to fall- when we start to be God! This is what the bible has been telling us for the past thousand years, to be the same as God. To be everywhere as God, to claim that I Am that I am!
We cannot be everywhere, we cannot be God! But here is what “Lucy” is telling us! “To be the same as God.” They are telling us how to be a God.
If anyone has a mind, spirit and the heart, it will be so easy to realize how Charles Darwin told Donald Johnson to name the ape like animal found in Ethiopia as Lucy.
As we see from the movie Morgan Freeman {as professor} preaches how earth and we humans evolve and use 20% of our mind in the future, (like dolphins use “sonar” to understand their environment remotely and we can imagine what will happen if we use 100% of our brain (cerebral capacity).
In the movie we see the professor lecturing how the nature interacts with all organisms and until this time we only use 10% of our brain. It is all about to “use” 100 percent of our brain and be like “LUCY”. To use the mass and the Energy, with the help of the computers and to be lost but everywhere!
This was not an easy way tough; Scarlet {as Lucy} has to go way far to reach 100% of her cerebral capacity. She has to take CPH4 and increase her knowledge and be “everywhere”. To be fearless, to have no desire….!

Just see the movie and ask 3 questions, shown the pictures below,   
                         Any one who knows Michael Angelo’s Paint about the creation of Adam and see the movie Lucy will understand what I wanted to say here.

 And any one who has read the bible, and know that who said “I AM” will notice how the movie ends with this word,



Then both the man and the woman changed. It was like their eyes opened, and they saw things differently. They saw that they had no clothes on- they were naked.


Did you want to be naked? Be like Lucy!

“…You must not even touch that tree or you will die.” Genesis chapter 3:3

Jul 29, 2014

ቁልቢ



ቁልቢ


ከአራቱም መዓዘናት የሚመጡ ሰዎችን የምታስተናግደው ቁልቢ  ለድሬዳዋመ ሆነ ለሐረር ቅርብ ስትሆን፤ በዓመት ውስጥ በተለይ ታህሳስ እና ሐምሌ ወር ላይ ከፍተኛ የሆነ ምዕመንን ታስተናግዳለች፡፡
የቁልቢ ገብርኤል ሲባል ሁላችንም እንሰማለን፡፡ ታሪኩን በአጭሩ ለመጥቀስ ስንሞክር፡-
 በዮዲት ዘመን ከአክሱም ጽዮን ጽላተ ሙሴ ጋር በደባልነት ይኖር የነበረውን የቅዱስ ገብርኤልን ጽላት እና ንዋዬ ቅዱሳቱን ይዘው ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ጉዙ ቀጥለው፤ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት በዝዋይ ሀይቅ ውስጥ ደብረ ጽዮን ማርያም ተብላ ከምትጠራ ደሴት እንደተቀመጡ መዛግብት ያስረዳሉ፡፡
በዚያን ጊዜ የ5 ዓመት ንጉስ እንደነበር የሚነገረው አንደሳ ውዱም፤ ዮዲት ከ40 ዓመታት በኋላ ከዙፋን ስትወርድ በሸዋ ተሸሽጎ የነበረው አንበሳ ውዱም ተመልሶ አክሱም ላይ ነገሰ፡፡
በዚህም ጊዜ በዮዲት የተቃጠለውን የአክሱም ጽዮን ቤተክርስትያን አሳድሶ ጽላቱን ሲያኖር የቅዱስ ገብርኤል ጽላት (ታቦት) እንዳልተመለሰ ተነገረው፡፡
ይሕም ለምን ሆነ ሲባል ካህናቱ ከሁሉም ንዋዬ ቅዱሳት እና ታቦተ ጽዮን(ጽላተ ሙሴን) ጨምረው ለመውሰድ ሲሞክሩ የቅዱስ ገብርኤል ታቦት ግን ለመነሳት ‹‹እምቢ አለ››፡፡
ንጉሱም አዘኑ፡፡ በዚህ ወቅት ኤርትራ ውስጥ ከሚገኝ አባ አጽቀ ሌዊ የተባሉ ባህታዊ መጥተው ታቦቱን እንዲያመጡት ፈቃድ ጠየቁ፡፡
በማህተም የተደገፈ የይለፍ ደብዳቤ እና ስንቅ ይዘው ዝዋይ ደብረ ጽዮን ማርያም ደረሱ፡፡ /እንግዲህ ከዛሬ አንድ ሺህ ዓመት በላይ ኤርትራ፣ ደቡቡ የኢትዮያ ክፍል ይገናኙ እንደነበር ማሰብም ያስደስታል/
እቦታው ደርሰው ታቦቱንም ይዘው ሲወጡ አንድ ሰው ከፊት ቆሞ “ወዴት ትሄዳለህ?” ብሎ ጠየቃቸው፡፡ ወደ ሰሜን እንደሆነ መለሱላቸው፡፡ ወደ ሰሜን መሄድ እንደሌለበት እና ወደ ምስራቅ መሄድ እንዳለበት ይነገራቸዋል፡፡
የንጉስ ትዕዛዝ እንደሆነና ወደ ምስራቅ መሄድ እንደማይችሉ ነገር ግን ወደ ሰሜን መሄድ እንዳለባቸው ተናገሩ፡፡ በዚህ ክርክር መሃል ተናጋሪው ሰው ወደ ብርሃን ተለወጠ፤ ተናጋሪውም የጽላቱ ባለቤት ገብርኤል መሆኑ ተነገራቸው፡፡ ተከተለኝ በሚል ትዕዛዝ ጉዟውን ቀጠሉ…፡፡
አባ አፅቀ ሌዊም በመልዐኩ ቅዱስ ገብርኤል ተመሪነት ወደ ተቀደስ ተራራ ታህሳስ 19 ቀን ሀረርጌ ጠቅላይ ግዛት እንደደረሱ ተዓምሩ ላይ ተጠቅሷል፡
ባህታዊውም ቃልኪዳኑን ከመልዐኩ ተቀብለው በጾም በጸሎት ከኖሩ በኋላ ታሪኩን በድንጋይ ላይ ጽፈው በማኖር፤ ስውር ሆኖ እንዲኖር በማድረግ  ህልፈተ ሕይታቸውን ተቀበሉ፡፡
ከዚህም በኋላ ለብዙ ዓመታት ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ምስራቅ 150 ኪ.ሜ በቡልጋ አምባ በአጋዥጌ ካህናተ ሰማይ ቤተክርስትያን ውስጥ በደባልነት ይኖር ነበር፡፡
አጼ ምኒልክ በ1882 ሀረርን ሲጠቀልሉ ራስ መኮንን ከሾሙ በኋላ፤ ራስ መኮንን ሀረርን መናገሻ ቢያደርጉም ቁልቢንም በነበራት የቅዝቃዜ አየር ጠባይ እንደ ሁለተኛ ከተማቸው እንደመረጡ ይነገራል፡፡
ራስ መኮንንም ይሕንን ቦታ ከባህታዊያን ጋር በመነጋገር የነበረውን ታሪክ በመረዳት ታቦቱ መጥቶ እንዲቀመጥ አድርገዋል፡፡ ቦታውንም መጠነኛ መጠለያ በማዘጋጀት ካስቀመጡ በኋላ ስዕለት እንደተሳሉም የሚነገር ሲሆን፤ አካባቢን ሰላም ካደረክልኝ ህንጻ እንደሚያሰሩ ተሳሉ፤ …ይሕም ሆነ፡፡
አድዋ ሲዘምቱ እዚህ ቤተ-ክርስትያን ጸልየው፣ ቆርበው እና ተስለው እንደሄዱም ይነገራል፡፡ በብዛት እንደ አሁኑ ሰው የማይጎበኘው የበነረበት ወቅት እንዳለ ቢታወቅም፤ አጼ ኃይለ ሥላሴ በ1954 ዓ.ምህረት የህንጻው መሰረት ድንጋይ አኖረው፤ በ1957 ዓ.ምህረት ታኅሣሥ 19 ቀን ተመረቀ፡፡/ በ423 ሺህ ብር እነደሆነም ተጠቅሷል/፡፡.. አጠቃላይ ታሪኩን ለማግኘት መዛግብትን ማጋላበጥ እንሚያስፈልግ እየጠቀስኩ መ/ር ኃይለ መስቀል ፋንታሁን ያዘጋጀውን ባለ 40 ገጽ ጥራዝ ለዚህ ጽሑፍ ዋቢ አድርጌ የተጠቀምኩ መሆኑንም በማጣቀስ ለአዘጋጁ ላቅ ያለ ምስጋዬን አቀርባለሁ፡፡

በቁልቢ ገብርኤል ምን እንታዘባለን…?
ህንጻ ቤተክርስትያኑ ተገንብቶ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር መተዳደሪያ ደንቡንም አብሮ መመልከት ይቻላል፡፡ ከክርስትና ትምህርት መስፋፋት ጥቅም ባሻገር ሌሎች እሴቶችን ይዞ እንደተመሰረተም መመልከት ይቻላል፡፡
በመኪና ፓርክ በኩል ከፍተኛ የሆነ ምስቅልቅል/ ብዛት ስላለበት/ የሚታየውን ችግር ለመፍታት ዘመናዊ የሆነ አሰራር እንደሚያስፈልግ ለመገንዘብ ይቻላል/
አካባቢውን ማደራጀት፣ ከተማዋን ማሳደግ እና በተለይ ከከተማዋ ወደ ደብሩ የሚወስደውን መንገድ ‹‹በአስፓልት›› አሊያም ‹‹በኮልብ ስቶን›› ማልበስ ግድ የሚባልበት ወቅት ላይ ነን፡፡ ይሕም ደብሩ ከሚየገኘው የስዕለት ገቢ እና በየጊዜው የሚሄደውን ምዕመን ለዚህ አገልግሎት የሚል የገንዘብ ማሰባሰብ መርሃ ግብር አዘጋጅቶ ማሳካት የሚቻል ሲሆን፤ መንግስትም የበኩሉን ድርሻ መወጣት አለበት፡፡
ከከተማዋ እስከ ደብሩ ያለው ስፍራ የረብሻ እና የምስቅልቅል ሂደት እንደሆነ መመልከት ይቻላል፡፡ ቤተክርስትያናችን የንግድ መገበያያ መንገድ አድርጎ መውሰድ እና ይሕንንም ስርዓት ማስቀጠል የክርስቶስን ጅራፍ መቀበል ነው፡፡ ‹‹የሞንታርቦች›› እና የረብሻ ድምጽ የአርምሞ እና የጸጥታ እንዲሁም የመረጋጋት መንፈስን አይፈጥርም፡፡ / ደብሩ ቅጥር ግቢ ውስጥ ስንገባ ግን የተሻለ መረጋጋት እና ጸሎት ለማድረስ ሚያስችል ድባብ ነበረው፡፡
የስርቆት ነገር አያድርስ ነው፡፡ የቦታውን ኃያልነት እና ቅዱስነት በከፍተኛ ሁኔታ ያሳጣዋል፡፡ ለስርቆት ብቻ የሚመጡ አረመኔዎች እንዳሉም ይነገራል፡፡ / ስራውን አምላክ ካላገዘን ቀላል ነገር አይደለም/ ፖሊሶች ጳጳሱን ከሚጠብቁበት ጥንካሬ አንጻር ለምዕመኑም በተመጣጣኝ ሁኔታ ሊያስቡበትት ይገባል፡፡
መብላት፣ መጠጣት፣ መስከር ከኃይማኖት ስርዓት አንጻር የማይዛመዱ ናቸው፡፡ ቤተክርትያን በየሓይማኖት ስርዓቶች ይሕንን አይነት ነገር በማስተዋል በከፍተኛ ሁኔታ ከሚጠበቀው በላይ እየተስፋፋ በመሄዱ ማውገዝ አለባት፡፡ ነጋዴው ይሕንን ነገር ባይፈልግም ቦታው ላይ አልኮል መጠጦችን እና ከሐይማኖት ስርዓት ውጭ የሆነውን ነገር ሁሉ መቆጣጠር መቻል አለብን፡፡  የቢራ ፋብሪካ ማስታወቂያዎች “እንኳን ለቁልቢ ገብርኤል በዓል አደረስዎ” ብለው ሰፋፊ መጋረጃዎችቸን ሰቅለው ተመልክተናል፡፡ ….እኛንም ጋርደውብናል፡፡
ሐይማኖታችንን መጠበቅ ያለብን እኛ ነን፡፡ ይሕን ነገር ልንቃወም ይገባል፡፡ እርግጥ  ደብሩ ቅጥር ግቢ በተቃረብን ቁጥር እና ቅጥር ግቢው ውስጥ ይህ አይነት ችግር አለ ባንልም…አነስተኛዋን የቁልቢ ከተማ መቆጣጠር እና በተለይ በዓሉን በምናከብርበት ጊዜ ሃይማኖታዊ ስርዓቱ ተጠብቆ በረከቱን ተካፍለን ብንመለስ አማራጭ የማይቀርብለት መንገድ ነው፡፡
ይሕ ሁሉ ህዝብ ምን ይሳላል…?
መቼስ ስዕለት በልብ ለእግዚአብሔር ብቻ የሚነገር የሕይት ፍላጎት ነው፡፡ ጣልቃ አንገባም፡፡ ሁሉም ሰው ግን ለራሱ ብቻ ስዕለቱን ተናግሮ፤ ከሚመለስ በሕብረት ብንጸልይ እና በአገራችን ስርዓት ያለበትን፣ እውቀት የሚስፋፋበትን መረዳዳት የሚስተዋልበትን የማስተዋልና እና የጥበብን ስብዕና እንዲያላብሰን ብንመኝ ሊሻል እንደሚችል በግሌ ሃሳቤን እሰነዝራለሁ፡፡  ሰላም ያገናኘን!! ታኅሳስ 19/ 2006 ሀረር

Jun 10, 2014

የዲ/ን ዳንኤል ክብረት እይታዋች ምነው የጎንደሩን ንስር ሽልማት ማየት ተሳናቸው ……?

(((ጀሮ ዳባ ሲለብስ)))
የዲ/ን ዳንኤል ክብረት እይታዋች ምነው የጎንደሩን ንስር ሽልማት ማየት ተሳናቸው ……?


‹‹‹‹‹‹‹ተስፋ በላይነህ›››››››
ኢትዮጵያ ውስጥ የምታስገርመኝ ነገር አለች፡፡ ጆሮ ዳባ ስትለብስ! ዳባ  ግን ምን ማለት ነው? ከቆዳ የሚሰራ የሚከናነቡት ነው አሉ፡፡ ያንን የተከናነበ ሰው የሚሰማው ነገር የለውም!! ጀሮ ዳባ ሲለብስ ልብንም የሚያደነድን አቅም ሊኖረው ይችላል፡፡ ጀሮ ዳባ ሲለብስ ከባድ ነገር ነው….!

በጀሮዎቻችን ላይ ብቻም ሳይሆን ልባችንንም፣ አይኖቻችንንም ጨምሮ ዳባ ስናለብሳቸው፤ ሁሉም ነገር አይታየንም፡፡ 

አገራዊ መግባባትም ሆነ አገራዊ አንድነት በዳባ ተሸፋፍኖ ሲታለፍ ከተመለከትን ዓመታት ነጎዱ…፡፡ በታሪክ በርካታ ልዩነቶች፣ ክስተቶች፣ እውነታዎች ዳባ ለብሰዋል፡፡ ዳባ መልበሳቸው በአንድ ኩታ እንደሰበሰባቸው አይነት ቢሆን ጥሩ ነበር፡፡ ነገር ግን መተያዬት፣ መደማመጥ፣ መግባባትን አልፈጠረልንም፡፡

“አሸናፊዎች ታሪክን ይጽፋሉ!” እንዲባል፤ አሁን አሁንም ጆሮ ዳባ እየለበሰ፣ መናገር ያለባቸው ሰዎች እየተናገሩ የዳባው ‹‹ሳውንድ ፕሩፊንጉ›› ስላየለ፤ የሚያዳምጥ ጠፋ፡፡ ውሾች ይጮሃሉ… ግመሎቹ… ዓይነት ዘይቤ መሆኑ ነው!!

የዲ/ን ዳንኤል ክብረት እይታዋች ምነው የጎንደሩን ንስር ሽልማት ማየት ተሳናቸው ……?

 በዲያቆን ዳንኤል ፊት አውራሪነት የሚመራው የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት፤ መመለስ የሚገባቸው ጥያቄዎች እንዳሉ ይሰማኛል፡፡ ‹‹ጀሮ ዳባ ልበስ›› አይነት ነገር ከሆነ ያስተዛዝባል!!!!

‹‹የበጎ ሰው ሽልማት›› አላማውን ሆነ ጅማሮውን እንዲሁም ቀጣይ ተግባሩን የሚያጣጥል ሐሳብ አልያዝኩም፡፡ በፍጹም፡፡ በእጅጉ የሚደገፍ እና የሚበረታታም ነው፡፡ በዚህ ቅሬታ የለኝም!!

ሆኖም ይሕ የሽልማት ድርጅት ባለፈው ዓመት ሲቋቋም ‹‹ንስር የሽልማት ድርጅት›› ከሚባል ተቋም ጋር ያለውን መጠጋጋት፣ የሐሳብ መወራረስ፣ እንዲሁም እውቅና ሳይሰጥበት መቋቋሙ ፍተሻ የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው ባይ ነኝ!!

‹‹የንስር ሽልማት ድርጅት›› ከተቋቋመ 5 ዓመታትን እንዳሳለፈ ሁሉ፤ አሁን የዲያቆን ዳንኤል ክብረት ‹‹በጎ ሰው ሽልማት ድርጅት›› ለእጩነት ያቀረባቸውን የመወዳደሪያ መስፈርቶች /የውድድር ጽንሰ ሐሳብ አለው ብዬ አላምንም/ ከንስር የሽልማት ድርጅት የተቀዱ ናቸው ብዬ ለመሟገት ያስገድደኛል፡፡ ይሕንንም ለማለት የንስር ሽልማት ድርጅትን አነሳስ፣አላማ፣ ግብ  እና ራዕይ መመልከት በቂ ይመስለኛል፡፡ ያው እንደዘመኑ ‹‹ዳርዊናዊ ማሕበረሰብ›› አኪያሄድ እየተሳለጥን ካልሆነ በቀር….!!! ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ዳርዊናዊ ማሕበረሰብ ፍልስፍና ይከተላል ብዬ ማሰብ ስለሚያዳግተኝ..!!

የመናገሪያ ልሳን እና ድምጽ አንድን ነገር ለመግለጽ እና ለማስተዋወቅ ቁልፍ መሰረት እንደሆነ ዘመኑ በሚገባ እየነገረን ነው፡፡ የመረጃ ዘመንን አድበስብሰው አያልፉትም፡፡ ለጀሮ ዳባ ባሕል ግን አሳልፎ ሲሰጠን አሁንም ያስተዛዝባል..!

የሚዲያ ሰዎችን መያዝ፣ ታዋቂ ድርጅቶችን መጠጋት፣ ስመ- ጥር መሆን በአሁኑ ሰዓት ራስን የመግለጽ ቁልፍ ግብዓቶች ናቸው፡፡ ሰው ያስፈልግሃል!! ሰው ከሌለህ የሚሰማህ የለም!! ከላይ እስከ ታች ሰው ለ ሰው ሆኗል!! ሰው የሌላቸው ሰዎችስ ምን ይሁኑ??

የዲያቆን ዳንኤል ሽልማት ድርጅት ከባለፈው ዓመት በሰፊው  በተጠናከረ እና በተደራጀ እየተንቀሳቀስ እንደሆነ አይተናል፤ ራሱም በኢቢኤስ አርአያ ሰብ ዝግጅት ላይ ተናግሮታል፡፡
የኔ የመጀመሪያ ጥያቄም ይሕ ነው፡፡ አንድ ድርጅት ሐሳቡን፣ አላማውን እና ራዕዩን ይዞ ሲንቀሳሰቅ እና ወደ ስራ ሲገባ፡- የመጀመሪያውን ስራ ማሰብ ያለበት አላማውን ግምት ውስጥ በማስገባት፣ የሐሳቡን ጭብጥ እና አጠቃላይ ይዘት ወደ ተግባር ማስገባት በሚችልበት አቅሙ ሲገኝ ነው፡፡ ይሕም ማለት ሐሳቡ ሰፊ፣ ጭብጡ መሬት የሚይዝ፣ ራዕዩ ጥልቅ ሆኖ ወደ ስራ ሲገባ፤ የአቅም ማነስ ጉዳይ የሚያጋጥመው ከምን አንጻር ነው? ሆኖም ካለፈው ት/ት ወስዶ ተሸሽሎ ሲገኝ ያስመሰግነዋል፣ በርታ ያስብለዋል!!  በመንገድ ላይ እየተራመደ እየተቋቋመ ያለ ድርጅት መሆኑን ግን ልብ ይሏል፡፡ የኔም አባባል ይኸው ነው… አነሳሱ ላይ ተጠናክሮ ያልታዬበት ጉዳይ፡- ሳይጠናከር ለምን መጀመር አስፈለገ? ሳይተናከር እንዲጀምርስ ምን አስገደደው? ምን ገፋፋፈው? ማን ነገረው?

 የዲያቆን ዳንኤል በጎ ሰው ሽልማት ድርጅት እንደ ድርጅት ሲቋቋም በኢትዮጵያ ውስጥ እንደዚህ አይነት መሰል ድርጅት አለ ወይንስ የለም ብሎ መፈለግ፣ መጠየቅስ እንዴት አቃተው?? የዲያቆን ዳንኤል እይታዎች የጎንደሩን ንስር ሽልማት እንዴት ሳያስተውለው ቀረ? ለቀረበለት ጥያቄስ መልስ ለመስጠት ጆሮን ዳባ ማለት ለምን አስፈለገ? ጆሮ ዳባ ልበስ ያስተዛዝባል!! አሁንም ወደ ሚቀጥለው ፍተሻ እና ጥየቃ መቀጠላችን አይቀርም፡፡ እውነትን ለማውጣት!!
 ብዙ ማለት ይቻላል፡፡ ብዙ ሐሳብ ማቅረብም ቀላል ነው፡፡ ነገሩን ቀለል እናድርገው፤ ለዲያቆን ዳንኤል ክብረት የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅትን በርታ ከማለት ግን አንቆጠብም፡፡ ዋናው የስራው አላማ በጎ ሰዎችን ያብዛልን፣ በጎ ሰዎችን ትውልድ ይወቃቸው፣ የሚተጉ፣ የሚሰሩ ሰዎች ይሸለሙ፣ ይበረታቱ ነው፡፡ ….
የገቢ ምንጭነቱ እምብዛም አልታየኝምም፡ ምናልባትም የንስር ሽልማት ድርጅትንም ሆነ የዲያቆን ዳንኤልን በጎ ሰው ሽልማት ድርጅት ሁለቱንም የማቀርብላቸው ነገር ቢኖርም፡- ይሕ አይነት ድርጅት ሲቋቋም በግለሰብ ደረጃ የግለሰባዊነት ዕውቅናን እንዳያስፋፋ፣ የተወሰኑ ግለሰቦችን ለገቢ ምንጭነት ብቻ እንዳያሳድግ ነው፡፡ ዘመኑ ከባድ ነው!! እከከኝ ልከክክ አይነት ቀመር፡፡….

ማስታወቂያ ስራዎች፣ ድርጅቶች፣ አዳዲስ ተቋሞች ረብጣ ብር እየገበሩ ራሳቸውን እያስተዋወቁ ድርጅት ያሳብጣሉ፡፡ ይሕ የዘመኑ ቀመር ነው!!! ዓላማ እየላቸው፣ ራዕይ አንግበው ረብጣ ብር ጋር መደራደር ካልቻሉ ይደፈጠጣሉ….!!! ይሕ የዘመኑ ቀመር ነው!!!
ንስር የሽልማት ድርጅት ከተቋቋመ 5 ዓመታትን አስቆጥሯል
የሚገርመው ዶ/ር በላይ አበጋዝ/ በልብ ህሙማን ህክምና/ ፍቅረ ስላሴ የቱሪዝም አባት እና ዶ/ር በርናንድ አንደረስንን መሸለሙ ብቻ ሳይሆን ከላይ የቀረቡት ሁለቱ በዳንኤል ክብረት በጎ ሽልማት ድርጅት በዕጩነት መቅረባቸው ሲሆን ዶ/ር በርናንድ አንደርሰን ደግሞ በንስር ሽልማት ድርጅት ከተሸለመ በኋላ በጎንደር ህክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ/ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ/ በ60ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ ክብረ በዓሉ ላይ በልዩ ሽልማት መሸለሙ ነው፡፡ ይሕ ለንስር ሽልማት ድርጅት ድርብ ድል ሆኖ ሊቆጠርለት ይችላል፡፡ የንስር አይን አስቀድሞ ሰዎቹን ጎብኝቷቸዋልና!!! የስራ ዓላማው ጅምሩ ጽንሰ ሐሳቡ ከስንር ሽልማት ለማየት ይቻላል! https://www.facebook.com/niser.awarde?fref=ts መጎበኘት ይቻላል!!

ሆኖም የሽልማት ድርጅቶች የግለሰብ መጠቀሚያ ሆነው ሲቀጥሉ ያስተዛዝባል፤ ተሸላሚ ሰዎችንም እያነጣጠሩ፤ ከፖለቲካ ፍራቻ፣ ከመንግስት፣ ከአለም አቀፋዊ ተጽኖዎች ተለይተን በጎ ሰዎችን እንድንፈልግ እና እንድንሸልም፤ የጀሮ ዳባ ማልበስን ባሕልን አሽንጥሮ ፤ ኩክ የሚጠርግ  ጸሎት እንዲያበዛልን… እግዚአብሔር ይርዳን!! ሌላ ምን ይባላል?


May 16, 2014

Lets read the holy bible and books filled with holy spirits

I am not sure you need to have this book!
read the words of God first to tackle the evil spirit
http://awdemehret.org/index.php/polls/

but if you have the words of God inside you and if you are ready to see how the world is deceived! so the blogger advices the reader to read The bibe/ "Metsah Kidus"

May 9, 2014

ዮፍታሔን ሥእለት

   

ስለ ሥእለት ሲወራ በመጽሐፍ ቅዱስ ከሚገርሙኝ ሥእለቶች ውስጥ የዮፍታሔን ሥእለት የሚያክል አልተፈጠረም፡፡ ዮፍታሔ በነበረበት ትውልድ ቦታ ከወንድሞቹ ጋር ተለያይቶ ተሰድዶ በሌላ ቦታ ይኖር ነበር፡፡ ከጊዜያት በኋላም ዮፍታሔ በሄደበት ቦታ ጠላቶቹን በጦር ማንበርከክ የሚያስችል ሐይል እና እድሉን ማግኘት እንዲችል ይሳላል፡፡ ይህም ሥለት “ዮፍታሔ ሥለት” በመባል ይታወቃል፡፡
ዮፍታሔ ለአምላኩ የተሳለው ነገር ምንድን ነው? በብሉይ ኪዳናት ተጽፎ እንደምናየው በእስራኤል ሕዝብ ለእግዚአብየር በሚቃጠል መስዋዕት/በግ፣ፍየል… ከአምላካቸው ጋር ይገናኙ፣ይታረቁ ነበር፡፡ በዚህም ልምድ መሰረት ዮፍታሔ “ጦርነቱን በድል ከተመለሰ በቤቱ መጀመሪያ ላይ የሚያገኘውን ነገር ለእግዚአብሔር እንደሚሰዋለት” ይሳላል፡፡
ከአሞን ልጆች ዘንድ በደኅና በተመለስሁ ጊዜ፥ ሊገናኘኝ ከቤቴ ደጅ የሚወጣው ማንኛውም ለእግዚአብሔር ይሆናል ለሚቃጠልም መሥዋዕት አቀርበዋለሁ ብሎ ለእግዚአብሔር ስእለት ተሳለ። መሳፍንት 11፡31
ሥእለት ቀላል ነገር አይደለም፡፡
ጦርነትም ተካሄደ፡፡ ድሉም በእግዚአብሔር ሐይል ለዮፍታሔ ሆነ፡፡ ዮፍታሔ እና ጦረኛው እንዲሁም የመንደሩ ሰው በደስታ ተሰባሰበ፡፡ ዮፍታሔ ወደ ቤቱ ሲመለስ እና ወደ መኖሪያው ሲቃረብ የመጀመሪያ መስዋዕት የሚጠብቀው በግ፣ ላም፣ ፍየል እንጂ ሌላ ነገር አልነበረም፡፡ ጠብቆ የነበረው ነገርም በዚህ የሚገመት አልነበረም፡፡ የመጀመሪያ እና ብቸኛ ልጁ ወደ እርሱ መጣች… በዕልልታ፣ በከበሮ… ደስታዋን እያሳየች በዝማሬ ወደ አባቷ መጣች… ቀረበች… ዮፍታሔ ደስተኛ አልነበረም… “ወዮ! “እያለ በመጮህ ልጁን እንድትመለስ ተማጸነ…!  አልተግባቡም… አልተመለሰችም… መጥታም ተገናኘችው… ለምን መመለስ እንዳለባትም ስጥጠይቀው ለእግዚአብሔር መስዋዕትነት እንደተሳላት ነገራት….!!
ትክክለኛ መልካቸው እና የቀለም ገጽታቸው ይህ ነው ብለን አናምንም!
  “እነሆም ልጁ ከበሮ ይዛ እየዘፈነች ልትገናኘው ወጣች ለእርሱም አንዲት ብቻ ነበረች ከእርስዋም በቀር ወንድ ወይም ሴት ሌላ ልጅ አልነበረውም።
እርስዋንም ባየ ጊዜ ልብሱን ቀድዶ። አወይ ልጄ ሆይ! ወደ እግዚአብሔር አፌን ከፍቻለሁና፥ ከዚያውም እመለስ ዘንድ አልችልምና በጣም አዋረድሽኝ አስጨነቅሽኝም አላት።
እርስዋም፦ አባቴ ሆይ፥ አፍህን ለእግዚአብሔር ከከፈትህ፥ እግዚአብሔር በጠላቶችህ በአሞን ልጆች ላይ ተበቅሎልሃልና በአፍህ እንደ ተናገርህ አድርግብኝ አለችው።
መሳፍንት 11፡34-36
እዚህ ታሪክ ላይ እጅግ በጣም የሚደንቅ ውሳኔ እንመለከታለን፡፡ ልጁ መስዋዕት ለመሆን ፍቃደኛነቷን ትገልጻለች… ለእኛም ስለት/ቃል ቃል ፣ሆኑን እና አስቀድመን ማሰብ እንዳለብን፣ የማናደርገውን ነገር መሳልም ሆነ ቃል መግባት እንደሌለብን ያስተምረናል… ለእግዚአብሔርም ከተሳልን መፈጸም እንዳለብን፣ ምንም ነገር ቢሆን ከእግዚአብሔር እንደማይበልጥ መረዳት እንዳለብን እንገነዘባለን፡፡
አብርሃም ይስሃቅን እንዲሰዋለት ሲልከው ፈቃደኛ ነበር፡፡ ልጁም ወደየት እነደሚሄዱ ሳያውቅ አባቱን ግን ከመታዘዝ አልከለከለም፡፡ ምናልባት የዮፍታሔን እና የአብርሃምን የሚለየው አብርሃም በይስሃቅ ምትክ ሊሰዋ የተዘጋጀ በግ ከፈጣሪ እንደተላከለት ነው፡፡ ዮፍታሔ ግን አልተላከለትም! ምን ማድረግ አለበት? ያሉት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ ሲባል ሰምተን ይሆናል፡፡

እርስዋም፦ አባቴ ሆይ፥ አፍህን ለእግዚአብሔር ከከፈትህ፥ እግዚአብሔር በጠላቶችህ በአሞን ልጆች ላይ ተበቅሎልሃልና በአፍህ እንደ ተናገርህ አድርግብኝ አለችው።
አባትዋንም። ይህ ነገር ይደረግልኝ ከዚህ ሄጄ በተራሮች ላይ እንድወጣና እንድወርድ፥ ከባልንጀሮቼም ጋር ለድንግልናዬ እንዳለቅስ ሁለት ወር አሰናብተኝ አለችው።
እርሱም፦ ሂጂ አለ። ሁለት ወርም አሰናበታት ከባልንጀሮችዋም ጋር ሄደች፥ በተራሮችም ላይ ለድንግልናዋ አለቀሰች።

ሁለትም ወር ከተፈጸመ በኋላ ወደ አባትዋ ተመለሰች፥ እንደ ተሳለውም ስእለት አደረገባት እርስዋም ወንድ አላወቀችም ነበር።

የእስራኤልም ሴቶች ልጆች በዓመት በዓመቱ እየሄዱ የገለዓዳዊውን የዮፍታሔን ልጅ በዓመት አራት ቀን ሙሾ እንዲያወጡ በእስራኤል ዘንድ ልማድ ሆነ።

መሳፍንት 11፡36-40
ምስጢሩ በብርሃን አይን ይታያል!

Apr 29, 2014

ኦሪት ዘሌዋውያን 19




ከደሙ ጋር ምንም አትብሉ አስማትም አታድርጉ፥ ሞራ ገላጭም አትሁኑ።
27 የራስ ጠጕራችሁንም ዙሪያውን አትከርክሙት፥ ጢማችሁንም ዙሪያውን አትቍረጡት።
28 ስለ ሞተውም ሥጋችሁን አትንጩ፥ ገላችሁንም አትንቀሱት እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
29 ምድሪቱ ከግልሙትና ከርኵሰትም እንዳትሞላ ሴት ልጅህን ታመነዝር ዘንድ አታርክሳት።

ወደ ገላትያ ሰዎች 5

ወደ ገላትያ ሰዎች  5



1   በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ።
2   እነሆ፥ እኔ ጳውሎስ እላችኋለሁ። ብትገረዙ ክርስቶስ ምንም አይጠቅማችሁም።
3 ሕግንም ሁሉ እንዲፈጽም ግድ አለበት ብዬ ለሚገረዙት ሁሉ ለእያንዳንዶች ደግሜ እመሰክራለሁ።
4 በሕግ ልትጸድቁ የምትፈልጉ ከክርስቶስ ተለይታችሁ ከጸጋው ወድቃችኋል።
5 እኛ በመንፈስ ከእምነት የጽድቅን ተስፋ እንጠባበቃለንና።
6 በክርስቶስ ኢየሱስ ሆኖ፥ በፍቅር የሚሠራ እምነት እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና።
7 በመልካም ትሮጡ ነበር፤ ለእውነት እንዳትታዘዙ ማን ከለከላችሁ?
8 ይህ ማባበል ከሚጠራችሁ አልወጣም። ጥቂት እርሾ ሊጡን ሁሉ ያቦካል።
9-10   የተለየ ነገር ከቶ እንዳታስቡ እኔ በጌታ ስለ እናንተ ታምኜአለሁ፤ የሚያናውጣችሁ ማንም ቢኖር ግን ፍርዱን ሊሸከም ነው።
11 ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ገና እስከ አሁን መገረዝን ብሰብክ እስከ አሁን ድረስ ለምን ያሳድዱኛል? እንኪያስ የመስቀል ዕንቅፋት ተወግዶአል።
12 የሚያውኩአችሁ ይቆረጡ።
13 ወንድሞች ሆይ፥ እናንተ ለአርነት ተጠርታችኋልና፤ ብቻ አርነታችሁ ለሥጋ ምክንያትን አይስጥ፥ ነገር ግን በፍቅር እርስ በርሳችሁ እንደ ባሪያዎች ሁኑ።
14 ሕግ ሁሉ በአንድ ቃል ይፈጸማልና፥ እርሱም፦ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የሚል ነው።
15 ነገር ግን እርስ በርሳችሁ ብትነካከሱና ብትበላሉ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ።
16 ነገር ግን እላለሁ፥ በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ።
17 ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ላይ ይመኛልና፥ እነዚህም እርስ በርሳቸው ይቀዋወማሉ፤ ስለዚህም የምትወዱትን ልታደርጉ አትችሉም።
18 በመንፈስ ብትመሩ ግን ከሕግ በታች አይደላችሁም።
19 የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው እርሱም ዝሙት፥ ርኵሰት፥
20     መዳራት፥ ጣዖትን ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት፥
21 መለያየት፥ መናፍቅነት፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜም እንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።
ወደ ገላትያ ሰዎች  5
22     የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።
23     እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም።
24     የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ።
25     በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ ደግሞ እንመላለስ።
26     እርስ በርሳችን እየተነሣሣንና እየተቀናናን በከንቱ አንመካ።


Jan 29, 2014

የሰው መንፈስ የእግዚአብሔር መብራት ነው” ምሳሌ 20፡27

“የሰው መንፈስ የእግዚአብሔር መብራት ነው”
ምሳሌ 20፡27

አግዚአብሔር ሆይ! ባሳለፍናቸው መራራ እና ጣፋጭ ቀናት ያለፉብንን እና ያለፍናቸውን የህይወት ክስተቶች በሙሉ እያስታወስንህ እናመሰግንሃለን፡፡ በእርግጥ ብዙ ነገሮች አልፈውናል፡፡ 

ያሳለፍናቸው እና ያለፉብን በቁጥር ጥቂት የሚባሉ አይደሉም…! ጥቂት አለመሆናቸው ብቻም ሳይሆን በቁጥር አንሰው ቢገኙም ለዘመናት የምንኖርባቸው እና የምንኖርላቸው ይመስለን ዘንድ ተጣብቀናቸዋል፡፡ እጅ ሰጥተንላቸዋል፡፡ ክብር አጥተንባቸዋል፡፡ በሚዛን ቀልለንባቸዋል፡፡ በስጋ-በመንፈስ ረክሰንባቸዋል፡፡ ታስረን-ተተብትበንባቸዋል፡፡ ወደ ዘላለሙ ጸጥታ ስንሄድ ግን አንዳቸውንም አላስከተልናቸውም፡፡ የሚከተለን ጭለማን አሊያም ብርሃንን የሚያዝለው መንፈሳችን ብቻ  ነው፡፡ በማይከተሉን እላፊዎች የዘላለሙን መንፈስ ማጠልሸት ምንኛ ምርጫ ነው..?

አግዚአብሔር ሆይ!  የተማርንባቸው እላፊዎች እንዲበዙ ፤ የተማረርንባቸው ቢሆኑም እንኳ ጭለማን እንዳይዘሩብን፤ ምሬትን በሬት ለውሰው መንፈሳችንን ጽልምት እንዳያወርሱት እንለምንሃለን፡፡ ለዚህም እንተጋለን!! ሳናቋርጥ እንተጋለን!!
ጨለማን እንዳላወረስከንም ስናስብ የምናመሰግንበት ዋነኛ ምክንያት ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ከብርሃን በብርሃን እና ወደ ብርሃን እንደሆንን ስናስብ አብልጠን እንድንከተልህ መነሻ እና መድረሻ ምክንያታችን ነው፡፡ 

እንደ ደመና በተመሰለው ሕይወታችን ውስጥ ብርሃኑ ሰንጥቆ ለዘላለም ያበራ ዘንድ ዛሬ ብርሃንህን ላክልን፡፡  በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚደንቀን አባባል አለ፡፡

“የሰው መንፈስ የእግዚአብሔር መብራት ነው” የሚለው፡፡

እውነት ባሳለፍናቸው፤ ባለፍናቸው፤ ባለፉን እና በተላለፍናቸው እንዲሁም በተማርንባቸው እና በተማረርንባቸው የሕይወት ጊዜያት ውስጥ ያጋጠሙን "እላፊዎች" በሙሉ የመብራታችንን ብርሃን እንዳያጨልሙብን እንንጠንቀቅ፡፡ መንፈሳችን በብርሃን ሆኖ ብርሃንን ይወረስ ዘንድ እንትጋ፡፡ ብርሃኑ በምድርም በህላዌም ያበራ ዘንድ በብርሃን እንመላለስ፡፡ የዘወትር ምግባችን እና ጥረት ትጋታችን ለዚሁ ነው፡፡ አሜን- ይሁንልን!
የሰው መንፈስ የእግዚአብሔር መብራት ነው የሆዱን ጕርጆች ሁሉ የሚመረምር። ምሳሌ 20፡27


የሎዛ ማርያም”፡፡

Jan 23, 2014

‹‹የቢዮንሴ አላማ እና ኢላማ!››

የቢዮንሴ አላማ 
                                                              በታምራት ፍስሃ

ይቺ የምናያት ዘፋኟ ቢዮንሴ ናት የመጨረሻው እራት ተብሎ በሚታወቀው ስእል ፊት ለፊት ተቀምጣለች፡ ፊት ለፊት በመቀመጧ ማንን እንደከለለች ታያላችሁ? ተወዳጅ መድሃኒት ክርስቶስን ነው በርግጥ እሱን መከለል ይቻላታልን? እርሱ በሁሉ ስፍራ ሙሉ ነውና ነገር ግን የሰይጣንን ተልእኮ ታስፈፅም ዘንድ በክርስቶስ ፈንታ እሷ መታየትን ወዳ እርሱን ከለለችው አለም ከክርስቶስ ይልቅ ለእርሷ እንደተማረከ አይታለችና አለም ከክርስቶስ ይልቅ ለዲያቢሎስ እንደተገዛ አይታለችና በዲያቢሎስ ሃይል ከፍ ብላ የክርስቶስን ቦታ ልትይዝ ደፈረች፡፡ 


ይህን ለማድረግ ይቻላታልን? እርሱ ተወዳጅ መድሃኒት ክርስቶስ የማይደፈር ሃያል የማይነቀንቁት ልዑል የማይነኩት ግሩም ነውና ከእርሱ ይልቅ ማን ይበረታል? ከአፉ በሁለት ወገን የተሳለ ስለታም ሰይፍ ያወጣል ፊቱም ከፀሃይ ይልቅ ያበራል አይኖቹ የእሳት ነበልባል ናቸው እግሮቹም በእቶን የነጠረ የጋለ ናስ የሚመስሉ በእጁ መዳፍ ምድሪቷን የያዘ የሰማይና የምድር ንጉስ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስን ማን ሊገዳደረው ይችላል?

ነገር ግን የመጨረሻው ዘመን እንደደረሰ ያሳዩ ዘንድ እኒህ የበረቱ መሰሉ የነፃነት አምላክ እርሱን ተፈታተኑት የፍቅር አምላክ እርሱን ከፉበት በዝና በገንዘብ በውበት ህይወት ክርስቶስን ካዱ መድሃኒት ክርስቶስን ሰደቡ ፡፡ አንደበትን የፈጠረ ጌታ በፈጠረው አንደበት ተሰደበ ሽክላ ሰሪውን አዋረደ ፡፡ 

ምን እንላለን? አለም በክርስቶስ ላይ ጦርነት አውጃለች አለም ለዲያቢሎስ ተንበርክካለች ነፍሷንም ለእሱ አስማርካለች ክርስቶሳውያን ጠውልገው ዲያቢሎሳውያን ደምቀው እያየን ነው እንግዲህስ አሰላለፋችንን እናስተካክል የማን አድናቂ ነን? ለማን እናጨበጭባለን? ለማን ነፍሳችን ትማረካለች? የማንንስ ተልእኮ እናስፈፅማለን


መድሃኒት ክርስቶስ ግን በጴጥሮስ በኩል አሁንም እኛን ትወዱኛላችሁን? ይለናል ምን እንመልሳለን? ይህን ተወዳጅ ጌታ እንወደዋለንን? እንኪያስ ይችን አለም ክደን ለክርስቶስ እንበርከክ የዚችን አለም ጣእም ንቀን መድሃኒት ክርስቶስን እንከተል አለም የክርስቶስ የሆኑትን ልትሰቅል የዲያቢሎስ የሆኑትን ልትሾም በርትታለችና ክርስቶስን የምንወድ የክርስቶስን መስቀል እንሽከም፡፡

ዮሃ ራእ 2211 "ዓመፀኛው ወደፊት ያምፅ ርኩሱም ወደፊት ይርከስ ፃድቁም ወደፊት ፅድቅ ያድርግ ቅዱሱም ወደፊት ይቀደስ"
https://www.facebook.com/tamirat.fisseha