ስለ ሥእለት ሲወራ በመጽሐፍ ቅዱስ ከሚገርሙኝ ሥእለቶች ውስጥ የዮፍታሔን ሥእለት የሚያክል አልተፈጠረም፡፡ ዮፍታሔ በነበረበት
ትውልድ ቦታ ከወንድሞቹ ጋር ተለያይቶ ተሰድዶ በሌላ ቦታ ይኖር ነበር፡፡ ከጊዜያት በኋላም ዮፍታሔ በሄደበት ቦታ ጠላቶቹን በጦር
ማንበርከክ የሚያስችል ሐይል እና እድሉን ማግኘት እንዲችል ይሳላል፡፡ ይህም ሥለት “ዮፍታሔ ሥእለት” በመባል ይታወቃል፡፡
ዮፍታሔ ለአምላኩ የተሳለው ነገር ምንድን ነው? በብሉይ ኪዳናት ተጽፎ እንደምናየው በእስራኤል ሕዝብ ለእግዚአብየር በሚቃጠል
መስዋዕት/በግ፣ፍየል… ከአምላካቸው ጋር ይገናኙ፣ይታረቁ ነበር፡፡ በዚህም ልምድ መሰረት ዮፍታሔ “ጦርነቱን በድል ከተመለሰ በቤቱ
መጀመሪያ ላይ የሚያገኘውን ነገር ለእግዚአብሔር እንደሚሰዋለት” ይሳላል፡፡
ከአሞን ልጆች ዘንድ በደኅና በተመለስሁ ጊዜ፥ ሊገናኘኝ ከቤቴ ደጅ የሚወጣው ማንኛውም ለእግዚአብሔር ይሆናል ለሚቃጠልም መሥዋዕት አቀርበዋለሁ ብሎ ለእግዚአብሔር ስእለት ተሳለ። መሳፍንት 11፡31
ከአሞን ልጆች ዘንድ በደኅና በተመለስሁ ጊዜ፥ ሊገናኘኝ ከቤቴ ደጅ የሚወጣው ማንኛውም ለእግዚአብሔር ይሆናል ለሚቃጠልም መሥዋዕት አቀርበዋለሁ ብሎ ለእግዚአብሔር ስእለት ተሳለ። መሳፍንት 11፡31
ሥእለት ቀላል ነገር አይደለም፡፡
ጦርነትም ተካሄደ፡፡ ድሉም በእግዚአብሔር ሐይል ለዮፍታሔ ሆነ፡፡ ዮፍታሔ
እና ጦረኛው እንዲሁም የመንደሩ ሰው በደስታ ተሰባሰበ፡፡ ዮፍታሔ ወደ ቤቱ ሲመለስ እና ወደ መኖሪያው ሲቃረብ የመጀመሪያ መስዋዕት
የሚጠብቀው በግ፣ ላም፣ ፍየል እንጂ ሌላ ነገር አልነበረም፡፡ ጠብቆ የነበረው ነገርም በዚህ የሚገመት አልነበረም፡፡ የመጀመሪያ
እና ብቸኛ ልጁ ወደ እርሱ መጣች… በዕልልታ፣ በከበሮ… ደስታዋን እያሳየች በዝማሬ ወደ አባቷ መጣች… ቀረበች… ዮፍታሔ ደስተኛ
አልነበረም… “ወዮ! “እያለ በመጮህ ልጁን እንድትመለስ ተማጸነ…! አልተግባቡም… አልተመለሰችም… መጥታም ተገናኘችው… ለምን መመለስ እንዳለባትም
ስጥጠይቀው ለእግዚአብሔር መስዋዕትነት እንደተሳላት ነገራት….!!
መሳፍንት 11፡34-36
እዚህ ታሪክ ላይ እጅግ በጣም የሚደንቅ ውሳኔ እንመለከታለን፡፡ ልጁ መስዋዕት
ለመሆን ፍቃደኛነቷን ትገልጻለች… ለእኛም ስለት/ቃል ቃል ፣ሆኑን እና አስቀድመን ማሰብ እንዳለብን፣ የማናደርገውን ነገር መሳልም
ሆነ ቃል መግባት እንደሌለብን ያስተምረናል… ለእግዚአብሔርም ከተሳልን መፈጸም እንዳለብን፣ ምንም ነገር ቢሆን ከእግዚአብሔር እንደማይበልጥ
መረዳት እንዳለብን እንገነዘባለን፡፡
አብርሃም ይስሃቅን እንዲሰዋለት ሲልከው ፈቃደኛ ነበር፡፡ ልጁም ወደየት
እነደሚሄዱ ሳያውቅ አባቱን ግን ከመታዘዝ አልከለከለም፡፡ ምናልባት የዮፍታሔን እና የአብርሃምን የሚለየው አብርሃም በይስሃቅ ምትክ
ሊሰዋ የተዘጋጀ በግ ከፈጣሪ እንደተላከለት ነው፡፡ ዮፍታሔ ግን አልተላከለትም! ምን ማድረግ አለበት? ያሉት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ
ሲባል ሰምተን ይሆናል፡፡
እርስዋም፦ አባቴ ሆይ፥ አፍህን ለእግዚአብሔር ከከፈትህ፥
እግዚአብሔር በጠላቶችህ በአሞን ልጆች ላይ ተበቅሎልሃልና በአፍህ እንደ ተናገርህ አድርግብኝ አለችው።
|
|
አባትዋንም። ይህ ነገር ይደረግልኝ ከዚህ ሄጄ በተራሮች ላይ
እንድወጣና እንድወርድ፥ ከባልንጀሮቼም ጋር ለድንግልናዬ እንዳለቅስ ሁለት ወር አሰናብተኝ አለችው።
|
|
እርሱም፦ ሂጂ አለ። ሁለት ወርም አሰናበታት ከባልንጀሮችዋም
ጋር ሄደች፥ በተራሮችም ላይ ለድንግልናዋ አለቀሰች።
|
|
ሁለትም ወር ከተፈጸመ በኋላ ወደ አባትዋ ተመለሰች፥ እንደ
ተሳለውም ስእለት አደረገባት እርስዋም ወንድ አላወቀችም ነበር።
|
|
የእስራኤልም ሴቶች ልጆች በዓመት በዓመቱ እየሄዱ
የገለዓዳዊውን የዮፍታሔን ልጅ በዓመት አራት ቀን ሙሾ እንዲያወጡ በእስራኤል ዘንድ ልማድ ሆነ።
መሳፍንት 11፡36-40
ምስጢሩ በብርሃን አይን ይታያል!
|
No comments:
Post a Comment