Apr 6, 2014

ሳራ ባርትመን- የምዕራባዊያኑ ክፉ ወጥመድ ትላንትና እና ዛሬ…

ሳራ ባርትመን- የምዕራባዊያኑ ክፉ ወጥመድ ትላንትና እና ዛሬ…
ተስፋ በላይነህ

ሳራ ባርትመን ስሟ በከፊል የተቀየረ በ19ኛው ክፍለዘመን መጀመሪያዎች ወደ አውሮፓ ተግዛ የሄደች፤ የአፍሪካኖች ጭቆና ከስጋ ባርነት  ወደ መንፈሳዊ እስራት የተሸጋገረበት መገለጫ ስም ነው፡፡ ይህንን ስንል እና መዝግበን ስናስቀምጥ ነጮች በጥቁሮች ላይ ያደረሱትን በደል እያስታወሱ ጥላቻ ለመዝራት ከቶ አይደለም፡፡ ቂም በቀል ለመርጨትም አይደለም፡፡ የትላንትናው የስጋ ባርነት ወደ ዛሬው የመንፈስ እስራት እንዴት ተጀምሮ እንዴት እንደተሸጋገረ ለማመላከት የተቀመጠ ሃሳብ እንጂ…!
ሳራ ባርትመን ማን ነች?
Sarah Baartman   በእንግሊዝኛ መጠሪያዋ ሳራ ተብላ ስትጠራ Saartjie በደች ግዥ ግዛት ስር በነበረበው የአፍሪካ ደቡባዊ ክፍል በጋምቶስ ሸሎቆ አካባባ የተወለደች፤ በ20ዎቹ የእድሜ ደረጃዋ በአንድ አሌክሳንደር ደንሎፕ በሚባል ስኮትላንዳዊ ዶክተር አማካኝነት ወደ ለንደን ተሸጣ የሄደች ጥቁር ሴት ነበረች፡፡ በለንደን ለ4 ዓመታት ለእይታ ቀርባ ነበር፡፡ በባሪያ ንግድ አስወጋጅ ቡድኖች ዘንድ ከለላ ለማግኘት ብትጠየቅም በምርጫዋ እንደመጣች እንደመሰከረች ታሪኩን ያቀረቡልን ዘጋቢዎች ለመጥቀስ ሞክረዋል፡፡ የባርያ ንግድ ስርዓትን በማስመልከት በወጣ አዋጅ መሰረት በፍርድ ቤት ሊታይ ቢሞከርም ሳራ ብርትመን እያገኘች ከነበረው ጊዜያዊ የገንዘብ ጥቅም አንጻር ያለችበት ሁኔታ የባርነት እንዳልሆነ መመስከሯ ተዘግቧል …….

ደንሎፕ ሲሞት ወደ ፓሪስ አቀናች፡፡ እጅግ ኢ-ሰብዓዊነት የጎደለው ተግባርም የሚቀጥለው በፈረንሳይ ፓሪስ ነው፡፡ ሳራ በርትመንን የነበራትን የሰውነት ቅርጽ ሰዎች አየከፈሉ እንዲመለከቱት ተደርጓል፡፡በመቀመጫዋ/ በቂጧ/ ያለው የስብ መጠን በመብዛቱ እና የሴት ብልት ክፍሏ ሽንት መሽኛ ቆዳ መሰል ክፍል ረዘም ያለ በመሆኑ  በእንግሊዝኛ አጠራሩ Labia minora  /ላቢያ ሚኖራ/ ከነጭ ሴቶች በተለየበመሆኑ ይህ የተፈጥሮ ጉዳይ ወደ ወሲባዊ ማማለያ ተዓምር እንዲወሰድ ሆነ፡፡ ወደ ምርምሩም ሂደት በመግባት “የዝግመተ ለውጥ ሂደታቸውን ያላጠናቀቁ አጥቢ እንስሳት የመራቢያ ክፍሎቻቸው ላይ ተጽእኖ እንደሚኖር ያላቸውም ቅርጽ እንደሚለወጥ” የሚል የሳይንስ መላምት እንዲቀርብ ተደርጓ፡፡ ይህም ሰዎች እንዲመለከቱት፣እንዲነኩት እና ለወሲብ ግልጋሎት እንዲውል መደረጉ ሳራ ባርትመንን ወደ ስጋን ሽጦ ማደር ንግድ አመራት እንጂ የፈየደላት አንዳችም ፋይዳ አልነበረም፡፡ ሞቷንም አራዘመመው፡፡ እ.ኤ.አ በ1815 ዓ.ም ሞተች፡፡

ሰዎች ሙሉ የሰውነት ክፍሎቿን ለመመልከት ገንዘብ ይከፍሉ ነበር፡፡ የመራቢያ ብልቷንም ጭምር ለመመልከት ሲደረግ ፈቃደኛ ያልነበረችባቸው ጊዜያት ቢኖሩም ገንዘብ ሁሉን ያደርጋልና በሙለው መርዘኛ አገዛዝ ውስጥ በመሆኗ ገንዘብ መከፈል ሲጀምር ግን ከማሳየት አልተቆጠበችም፡፡ ስጋን ቸርችሮ መኖርም የህይወት እጣ ፈንታ ሆነባት፡፡ በመጨረሻዎቹ የሕወት ዘመኖቿ በጣም ተጎሳቁላ እን ተንገላታ በድህነት እንደሞተችም ታውቋል፡፡ የሞቷ መንስኤም ከግብረስጋ ግንኙነት ጋር በተያያዘ  በሽታ መሆኑንን ምንጮች ይጠቁማሉ፡፡
steatopygia በመቀመጫ አካባቢ የስብ ክምችት ሲበዛ ስቲቶፊጊያ ብለው ይጠሩታል፡፡ ይህንን በከፍተኛ ሁኔታ ለወሲቡ ኢንደስተትሪ ሸቀጥ የዋለ ሲሆን አፍሪካዊቷ ሳራ በርትማን ለዚህ ተግባር የዋለች የመጀመሪያዋ ሴት ነች፡፡ የበነራትን የተፈጥሮ ቅርጽ ከካውካሲያን ሴቶች ጋር በማነጻጸር ኖርማል እንዳልሆነ ለመፈረጅ ከልካለይ እና አቤት ባይ አልነበረም፡፡ ከዛም አልፎ ለተለያዩ የስነጽሁፍ ስራዎችም መነሻ ሊሆን ቻለ፡፡ Hottentot Venus ሆቴንቶት ቬነስ የሚል ግጥም እና መሰል የስነጽሑፍ ስራዎችም የተሰሩት የሳራ ባርትመንን ሁኔታ በማመላከት ነው፡፡ ሆቴንቶት ሳራ ባርትመን ትውልድ ስፍራ መጠሪያ ሲሆን ቬነስ ደግሞ በግሪክ አፈ-ታሪክ ውስጥ “የፍቅር አምላክ” መጠሪያ ስም ነው፡፡ አፍሪካዊቷ ይቅር አምላክ ሰዎችን የፍቅር ጥም ለማርካት ለሸቀጥ የቀረበች ሴት ውክልናን የያዘች መሆኗን የሚያመላክት ስራ ሆኖ ቀርቧል፡፡ 

በጣም የሚያሳዝነው ታሪክ ሳራ ባርትመን ለዚህ አይነት አሰቃቂ ኢ-ሰብኣዊ ተግባር ሰለባ መሆኗ ብቻ አይደለም፤ የዘረኝነት በደሉም ብቻ አይደለም ኪሳራው፤ የሰውን ልጅ ዋጋ በቁም ማሳጣቱም ብቻ አይደለም አሰቃቂነቱ፤ ሳራ ባርትመን ስትሞት ሰውነቷ ተቆራርጦ ለጥናት እና ምርምር ውሏል፡፡ የጭንቅላቷ ቅርጽ/የአንጎል ክፍል/ ተወስዷል፡፡ መላ አካላቷም ተከፍሎ አጥንቷ ተለይቶ እስከ 1980ዎቹ ድረስ በፓሪስ ሙዚየም ለህዝብ እይታ ክፍት ነበር፡፡
በቁም እያለች ሰዎች እየከፈሉ ከማየታቸው ባሻገር ሞታም የሰውነት ክፍሏ ለችርቻሮ ቀርቦ ነበር፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ሊነሳ የሚችለው ታሪክ የሰውን ልጅ እንደ እንሰሳ ቆጥሮ ለመመልከት ብቻ የተደረገው በደል ነው፡፡ ኦታ ቤንጋ ልክ እንደ እንስሳት ማጎሪያ ጣቢያ/ዙ/ የሰው ዙ /human zoo/ መሞከሪያ ፍቱር ተደርጎ የነበረ ነው፡፡



ሳራ ባርተመን ከሞተች በኋላ እና የሰውነት ክፍሏ ተቆራርጦ ለዓመታት ስትጎበኝ ከቆየች በኋላ ማንዴላ ለስልጣን ሲበቃ በተደረገ ስምምነት ወደ ትውልድ አገሯ ተመልሳ እንደትቀበር ሆኗል ፡፡ በ Diana Ferrus /ዲያና ፌረስ/ “ወደ ቤትሽ ልደስድሽ መጣሁ” የተሰኘ ግጥም የተጀመረው ጥረት በስቴፈን ጀይ ገውልድ ‹‹ሆቴንቶት ቬነስ›› የሚለው ጽሑፉ አለም አቀፋዊ ሽፋን በማግኘቱ ማንዴላ በአፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ ፓርቲው ሲመረጥ ከፈረንሳይ መንግስት ጋር በመነጋገር ወደ አፈር ቦታዋ እንድትመለስ ሆኗል፡፡ የዲያና ፌረስ "I've come to take you home" በሚለው ግጥሟ ታጅቦ አሁንም በስፍራው ይገኛል፡፡
በጥቁሮች ማህበረሰብ ዘንድ መቀመጫን እንደ ወሲባዊ ማነቃቂያ ክብር ኩራት አድርጎ መውሰድ በተለይ በሆሊውድ ራፕ እና ሂፕ ሆፕ ሙዚቃ ኢንደስትሪ ዘንድ ከተለመደ ሰነባብቷል፡፡ ከሁሉም በላይ ሴት እህቶቻችን መቀመጫን እንደ ትልቅ የውበት መሳቢያ  አድርጎ መውሰድ “ፋሽን” ሆኖ ከተቆጠረ ዓመታት ተቆጠሩ፡፡



ታዋቂዎቹ እነ ቢዮንሴ፣ ሊለ ኪም፣ ሚኪ ሚናጅ እንዲሁም በርካታ ሴት ጥቁር  ‹‹ፈርጦች›› መቀመጫዎቻቸው ለወሲብ ነክ ጋዜጦች እና ሚዲያ ሽፋኖች በቀዳሚነት የሚብረቀረቁ መገለጫዎች ሆነው ከተለማመድናቸው ቆየን፡፡ ሳራ ባርተመን በቀደመው ጊዜ በባርነት ግዞት በተገኘቸው መጠነኛ አመታዊ ሳንቲም ተሰቃይታ እንደሞተች እና ብዙሃኑን ለወሲብ ንግድ ማርኪያነት ግልጋለሎት እንደዋለች ታሪኳ መስካሪ ነው፡፡ 
አሁን ዘመናዊውን ባርነት ሳንገደድ እና ሳንስለመለም የዚህ ድብቅ ሴራ አላማ "ኢላማ" ሆነናል፡፡ ሱሪ መልበስ እናት/አባቶቻችን/ አስጠንቅቀውን ከደከማቸው በኋላ አሁን በሙዚቃው ኢንደስትሪ ሱሪን አውልቆ ሙሉ በሙሉ መቀመጫን ማሳየት ዘመናዊ እብደት መሆኑን ከተለመከትን ከራርመናል፡፡ ወደ ዘመነኞች ሚዲያ መመልከተት መመስክር ነው፡፡ ‹‹ትልልቅ›› መቀመጫዎች ለንግዱ አለም ክብር ናቸው፡፡ የጥቁር ህዝብ በገዛ ፈቃዱ ያሰለጠነው ጭቆና አነሳሱ እንዲያ በስጋ ነበር፤ አሁን ተጥለቅልቋል፡፡ 



ሌት ተቀን የሚንከባለለው ለባርነት እና ጭቆና፤ ታሪክ እና ክብርን ለመቅበር ፤ ማንነትን ለማርከስ ለቅኝ ግዞት ነው!! ሁሉንም የፈጣሪ ስጦታ የሆነው መንፈሳችን ሊመረምረው፤ ጠሊቅ አዕምሯችን ሊተይቀው ይገባል፡፡ ይህ ካልሆነ እንስሳ ናቸው የሚለውን እንስሳነታቸውን ማስመስከሪያ ክፉ ባርነት ነው፡፡ ከጭቆና እንላቀቅ! እንጠይቅ!! በፈቃዳችን አርነት እንውጣ!!!

No comments: