Mar 31, 2014

ልባችን ደከመው!

ልባችን ደከመው!
ልብ-ሳችን ለማጽዳት ገዝተናል ሳሙና
ቀኑ-ንም በሙሉ ስናጥብ ዋልንና
ቀኑም መሽቶ ነግቶ ብናጥበው በጸና
ልብሳችን አልጸዳም ከቶም አልተቃና፡፡

የማጠቡ ብሶት የማጠብ ጭቆና
ሚስጥር ገላጭመጥቶ ቢፈትሸው ግና

ልብሳችን ንጹህ ነው ከመታጠብ በቀር
በብዙ እጆች ስር ከግዞት ጭቆና
ልብሳችብ ንጹህ ነው አርነት አውጡና!!! 

የቆሸሸው ልብሱ ጭራሽ አልነበረም
ልብሱም እንዳይቆሽሽ እኛም እንዳንደክም
ሳሙናው ይታጠብ ሳሙናው ይለምልም
ልብ-ሳችን ደከመው ባንዱ ጥም ባንዱ ቂም..
ልባችን ደከመው በነዚያ- በነዚም!!

No comments: