May 10, 2014

የባፈሜት ሐውልት



    “ዝነኛው” ኤሊስተር ክራውሊ፤ ለሆሊውድ ዥነኞች አርዓያ የሆነው ይህ ሰው በ“ባፎሜት” ስም በመፈረም እንዲሁም በተለያዩ ቦታዎች በድብቅ ሲተላለፍ የነበረው ይህ ስም አሁን በገሃድ ወጥቷል፡፡ ባፈሜት “ታዋቂው”ኤልፋዝ ሌቪ በተባለ አስማተኛ ሁለት ጾታ ገጽታ ያለው፣ በፍየል ጭንቅላት አምሳያ እና በመላዕክት ክንፍ ተጣምሮ የተፈጠረ ምናባዊ ፍጥረት ነው፡፡ ባፎሜት በሰይጣኒዝም እምነት የሚመለክም ነው፡፡

በአሜሪካ ኦክልሃማ ግዛት በምክርቤቱ መሰብሰቢያ ቤተመንግስት የአስርቱ ትዕዛዛትን የሚያመላክት ሐውልት አለ፡፡ በአንድ የምክር ቤቱ አባል ተነሳሽነት የተሰራው ይህ ሐውልት በሰዎች ዘንድ ከፍተኛ ግምት የሚሰጠውን የሙሴ ህግ የሚያመላክት በመሆኑ “የክርስትያን አገር” ተብላ በምትጠራው አሜሪካን ውስጥ ለህዝቦች ከፍተኛ ዋጋ ያለውን ህግ ለማሳየት የቀረበ ነው፡፡ ሴኪውላር -ስጋዊ/አለማዊ በሆነ የህዝብ አስተዳደር ውስጥ ደግሞ የሁሉም እምነቶች እኩልነት ተፈጻሚነት ስለሚኖረው የሙሴን አስርቱን ህግጋት የሚያሳይ ሐውልት ከተቀመጠ የሌሎችን እምነት ተከታዮች መገለጫም የማያስቀምጡበት አንዳች እገዳ አይጣልም፡፡ Secularism::
በሳላፍነው የ2012 ዓመት የአስርቱ ትዕዛዛት ተቀርጸው በሐውልት መልክ ሲቀመጡ፤ የሰይጣኒዝም እምነት ተከታዮች በጓዳቸው የእነርሱን ሐውልት ቀርጾ ለማስቀመጥ ሽር ጉዳቸውን ተያያዙት፡፡ ምናልባትም የሙሴን ህግ ማስቀመጥ ለሌሎች እምነቶችም በበር ከፋቺነት መንገድ ጠራጊም ሆኖ ሊቀርብ እንደሚችል ማሰብ አያስኮንንም፡፡ የዚህ ማሳሰቢያ ቅድመ ጥንቃቄ የሌሎችን አገሮች ሴራ/ምስጢር እና የቀን በቀን ጡዘት ለማውራት አይደለም፡፡ እኛም ሴኪውላር መንግስት ነው ያለን…. ነገ ምን እንደሚሆን ለማመላከት እንጂ!!
የባፈሜት ሐውልትም ሕጻናት እንዲህ ሲመለከቱት ተቀርጾ በኦኮልሃማ ግዛት እንዲቀመጠ ጊዜው ደረሰ፡፡  

የሴኪውላሪዝም/ስጋዊ አለማዊ የመንግስት ስርዓት ይፋ በሚሆንበት ሰዓት አብረን መቀበል የሚኖርብን ደንብም የዝቅተኛ እና አስተዋሽ ያጡ የእምነት ቡድናትን በማስታወሰወ እና እኩል ቦታ ተሰጥቷቸው ከሌሎች ዝነኛ አስተሳሰቦች እና እምነቶች ጋር በመስመር እንዲቀመጥ የሚያደነግግ በመሆኑ አከራራሪነቱ አስቀድመን በገባንለት የሴኪውላሪዝም ማዕቀፍ የሚመለስ ይሆናል፡፡ መብታቸው ይከበርላቸዋል፡፡ እዚህ ላይ ግን የምንወስደው ሰብዓዊ ትንታኔ ቢኖር የሰውን ደም፣ ነፍስ ወይንስ ስጋ እንደ መስዋዕትነት የሚደነግግን አሊያም ህግወጥነት ቦታ ሊኖር በሚችልበት ሁኔታ የሚያምን እምነት ወደ ህብረተሰቡ ማምጣት በኋላ ለሚደርሰው የህግ ጥሰት ተጠያቂው አካል ማን እንደሚሆን ነው፡፡ Vandalsimየጥፋት እምነት በምን መዓዝን ይቶ ነው ለሐውልትነት የሚቀርበው፡፡የመሳሪያ ግዥ ህጋዊ በሆነበት አገር የሰዎች ጅምላ ጭፍጨፋ ቢስፋፋ ተጠያቂው ማን ነው…. ብዙ ማለት ይቻላል… ዘመኑ መዳረሱን ግን ከሚያመላክተን ጭብጥ በቀር ሌሎቹ ከንቱ ድካመ ናቸው፡፡ ሐሰተኛ ሊመጣ ግድ ነውና!!

No comments: