Jun 10, 2014

የዲ/ን ዳንኤል ክብረት እይታዋች ምነው የጎንደሩን ንስር ሽልማት ማየት ተሳናቸው ……?

(((ጀሮ ዳባ ሲለብስ)))
የዲ/ን ዳንኤል ክብረት እይታዋች ምነው የጎንደሩን ንስር ሽልማት ማየት ተሳናቸው ……?


‹‹‹‹‹‹‹ተስፋ በላይነህ›››››››
ኢትዮጵያ ውስጥ የምታስገርመኝ ነገር አለች፡፡ ጆሮ ዳባ ስትለብስ! ዳባ  ግን ምን ማለት ነው? ከቆዳ የሚሰራ የሚከናነቡት ነው አሉ፡፡ ያንን የተከናነበ ሰው የሚሰማው ነገር የለውም!! ጀሮ ዳባ ሲለብስ ልብንም የሚያደነድን አቅም ሊኖረው ይችላል፡፡ ጀሮ ዳባ ሲለብስ ከባድ ነገር ነው….!

በጀሮዎቻችን ላይ ብቻም ሳይሆን ልባችንንም፣ አይኖቻችንንም ጨምሮ ዳባ ስናለብሳቸው፤ ሁሉም ነገር አይታየንም፡፡ 

አገራዊ መግባባትም ሆነ አገራዊ አንድነት በዳባ ተሸፋፍኖ ሲታለፍ ከተመለከትን ዓመታት ነጎዱ…፡፡ በታሪክ በርካታ ልዩነቶች፣ ክስተቶች፣ እውነታዎች ዳባ ለብሰዋል፡፡ ዳባ መልበሳቸው በአንድ ኩታ እንደሰበሰባቸው አይነት ቢሆን ጥሩ ነበር፡፡ ነገር ግን መተያዬት፣ መደማመጥ፣ መግባባትን አልፈጠረልንም፡፡

“አሸናፊዎች ታሪክን ይጽፋሉ!” እንዲባል፤ አሁን አሁንም ጆሮ ዳባ እየለበሰ፣ መናገር ያለባቸው ሰዎች እየተናገሩ የዳባው ‹‹ሳውንድ ፕሩፊንጉ›› ስላየለ፤ የሚያዳምጥ ጠፋ፡፡ ውሾች ይጮሃሉ… ግመሎቹ… ዓይነት ዘይቤ መሆኑ ነው!!

የዲ/ን ዳንኤል ክብረት እይታዋች ምነው የጎንደሩን ንስር ሽልማት ማየት ተሳናቸው ……?

 በዲያቆን ዳንኤል ፊት አውራሪነት የሚመራው የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት፤ መመለስ የሚገባቸው ጥያቄዎች እንዳሉ ይሰማኛል፡፡ ‹‹ጀሮ ዳባ ልበስ›› አይነት ነገር ከሆነ ያስተዛዝባል!!!!

‹‹የበጎ ሰው ሽልማት›› አላማውን ሆነ ጅማሮውን እንዲሁም ቀጣይ ተግባሩን የሚያጣጥል ሐሳብ አልያዝኩም፡፡ በፍጹም፡፡ በእጅጉ የሚደገፍ እና የሚበረታታም ነው፡፡ በዚህ ቅሬታ የለኝም!!

ሆኖም ይሕ የሽልማት ድርጅት ባለፈው ዓመት ሲቋቋም ‹‹ንስር የሽልማት ድርጅት›› ከሚባል ተቋም ጋር ያለውን መጠጋጋት፣ የሐሳብ መወራረስ፣ እንዲሁም እውቅና ሳይሰጥበት መቋቋሙ ፍተሻ የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው ባይ ነኝ!!

‹‹የንስር ሽልማት ድርጅት›› ከተቋቋመ 5 ዓመታትን እንዳሳለፈ ሁሉ፤ አሁን የዲያቆን ዳንኤል ክብረት ‹‹በጎ ሰው ሽልማት ድርጅት›› ለእጩነት ያቀረባቸውን የመወዳደሪያ መስፈርቶች /የውድድር ጽንሰ ሐሳብ አለው ብዬ አላምንም/ ከንስር የሽልማት ድርጅት የተቀዱ ናቸው ብዬ ለመሟገት ያስገድደኛል፡፡ ይሕንንም ለማለት የንስር ሽልማት ድርጅትን አነሳስ፣አላማ፣ ግብ  እና ራዕይ መመልከት በቂ ይመስለኛል፡፡ ያው እንደዘመኑ ‹‹ዳርዊናዊ ማሕበረሰብ›› አኪያሄድ እየተሳለጥን ካልሆነ በቀር….!!! ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ዳርዊናዊ ማሕበረሰብ ፍልስፍና ይከተላል ብዬ ማሰብ ስለሚያዳግተኝ..!!

የመናገሪያ ልሳን እና ድምጽ አንድን ነገር ለመግለጽ እና ለማስተዋወቅ ቁልፍ መሰረት እንደሆነ ዘመኑ በሚገባ እየነገረን ነው፡፡ የመረጃ ዘመንን አድበስብሰው አያልፉትም፡፡ ለጀሮ ዳባ ባሕል ግን አሳልፎ ሲሰጠን አሁንም ያስተዛዝባል..!

የሚዲያ ሰዎችን መያዝ፣ ታዋቂ ድርጅቶችን መጠጋት፣ ስመ- ጥር መሆን በአሁኑ ሰዓት ራስን የመግለጽ ቁልፍ ግብዓቶች ናቸው፡፡ ሰው ያስፈልግሃል!! ሰው ከሌለህ የሚሰማህ የለም!! ከላይ እስከ ታች ሰው ለ ሰው ሆኗል!! ሰው የሌላቸው ሰዎችስ ምን ይሁኑ??

የዲያቆን ዳንኤል ሽልማት ድርጅት ከባለፈው ዓመት በሰፊው  በተጠናከረ እና በተደራጀ እየተንቀሳቀስ እንደሆነ አይተናል፤ ራሱም በኢቢኤስ አርአያ ሰብ ዝግጅት ላይ ተናግሮታል፡፡
የኔ የመጀመሪያ ጥያቄም ይሕ ነው፡፡ አንድ ድርጅት ሐሳቡን፣ አላማውን እና ራዕዩን ይዞ ሲንቀሳሰቅ እና ወደ ስራ ሲገባ፡- የመጀመሪያውን ስራ ማሰብ ያለበት አላማውን ግምት ውስጥ በማስገባት፣ የሐሳቡን ጭብጥ እና አጠቃላይ ይዘት ወደ ተግባር ማስገባት በሚችልበት አቅሙ ሲገኝ ነው፡፡ ይሕም ማለት ሐሳቡ ሰፊ፣ ጭብጡ መሬት የሚይዝ፣ ራዕዩ ጥልቅ ሆኖ ወደ ስራ ሲገባ፤ የአቅም ማነስ ጉዳይ የሚያጋጥመው ከምን አንጻር ነው? ሆኖም ካለፈው ት/ት ወስዶ ተሸሽሎ ሲገኝ ያስመሰግነዋል፣ በርታ ያስብለዋል!!  በመንገድ ላይ እየተራመደ እየተቋቋመ ያለ ድርጅት መሆኑን ግን ልብ ይሏል፡፡ የኔም አባባል ይኸው ነው… አነሳሱ ላይ ተጠናክሮ ያልታዬበት ጉዳይ፡- ሳይጠናከር ለምን መጀመር አስፈለገ? ሳይተናከር እንዲጀምርስ ምን አስገደደው? ምን ገፋፋፈው? ማን ነገረው?

 የዲያቆን ዳንኤል በጎ ሰው ሽልማት ድርጅት እንደ ድርጅት ሲቋቋም በኢትዮጵያ ውስጥ እንደዚህ አይነት መሰል ድርጅት አለ ወይንስ የለም ብሎ መፈለግ፣ መጠየቅስ እንዴት አቃተው?? የዲያቆን ዳንኤል እይታዎች የጎንደሩን ንስር ሽልማት እንዴት ሳያስተውለው ቀረ? ለቀረበለት ጥያቄስ መልስ ለመስጠት ጆሮን ዳባ ማለት ለምን አስፈለገ? ጆሮ ዳባ ልበስ ያስተዛዝባል!! አሁንም ወደ ሚቀጥለው ፍተሻ እና ጥየቃ መቀጠላችን አይቀርም፡፡ እውነትን ለማውጣት!!
 ብዙ ማለት ይቻላል፡፡ ብዙ ሐሳብ ማቅረብም ቀላል ነው፡፡ ነገሩን ቀለል እናድርገው፤ ለዲያቆን ዳንኤል ክብረት የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅትን በርታ ከማለት ግን አንቆጠብም፡፡ ዋናው የስራው አላማ በጎ ሰዎችን ያብዛልን፣ በጎ ሰዎችን ትውልድ ይወቃቸው፣ የሚተጉ፣ የሚሰሩ ሰዎች ይሸለሙ፣ ይበረታቱ ነው፡፡ ….
የገቢ ምንጭነቱ እምብዛም አልታየኝምም፡ ምናልባትም የንስር ሽልማት ድርጅትንም ሆነ የዲያቆን ዳንኤልን በጎ ሰው ሽልማት ድርጅት ሁለቱንም የማቀርብላቸው ነገር ቢኖርም፡- ይሕ አይነት ድርጅት ሲቋቋም በግለሰብ ደረጃ የግለሰባዊነት ዕውቅናን እንዳያስፋፋ፣ የተወሰኑ ግለሰቦችን ለገቢ ምንጭነት ብቻ እንዳያሳድግ ነው፡፡ ዘመኑ ከባድ ነው!! እከከኝ ልከክክ አይነት ቀመር፡፡….

ማስታወቂያ ስራዎች፣ ድርጅቶች፣ አዳዲስ ተቋሞች ረብጣ ብር እየገበሩ ራሳቸውን እያስተዋወቁ ድርጅት ያሳብጣሉ፡፡ ይሕ የዘመኑ ቀመር ነው!!! ዓላማ እየላቸው፣ ራዕይ አንግበው ረብጣ ብር ጋር መደራደር ካልቻሉ ይደፈጠጣሉ….!!! ይሕ የዘመኑ ቀመር ነው!!!
ንስር የሽልማት ድርጅት ከተቋቋመ 5 ዓመታትን አስቆጥሯል
የሚገርመው ዶ/ር በላይ አበጋዝ/ በልብ ህሙማን ህክምና/ ፍቅረ ስላሴ የቱሪዝም አባት እና ዶ/ር በርናንድ አንደረስንን መሸለሙ ብቻ ሳይሆን ከላይ የቀረቡት ሁለቱ በዳንኤል ክብረት በጎ ሽልማት ድርጅት በዕጩነት መቅረባቸው ሲሆን ዶ/ር በርናንድ አንደርሰን ደግሞ በንስር ሽልማት ድርጅት ከተሸለመ በኋላ በጎንደር ህክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ/ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ/ በ60ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ ክብረ በዓሉ ላይ በልዩ ሽልማት መሸለሙ ነው፡፡ ይሕ ለንስር ሽልማት ድርጅት ድርብ ድል ሆኖ ሊቆጠርለት ይችላል፡፡ የንስር አይን አስቀድሞ ሰዎቹን ጎብኝቷቸዋልና!!! የስራ ዓላማው ጅምሩ ጽንሰ ሐሳቡ ከስንር ሽልማት ለማየት ይቻላል! https://www.facebook.com/niser.awarde?fref=ts መጎበኘት ይቻላል!!

ሆኖም የሽልማት ድርጅቶች የግለሰብ መጠቀሚያ ሆነው ሲቀጥሉ ያስተዛዝባል፤ ተሸላሚ ሰዎችንም እያነጣጠሩ፤ ከፖለቲካ ፍራቻ፣ ከመንግስት፣ ከአለም አቀፋዊ ተጽኖዎች ተለይተን በጎ ሰዎችን እንድንፈልግ እና እንድንሸልም፤ የጀሮ ዳባ ማልበስን ባሕልን አሽንጥሮ ፤ ኩክ የሚጠርግ  ጸሎት እንዲያበዛልን… እግዚአብሔር ይርዳን!! ሌላ ምን ይባላል?


No comments: