‹‹መረቅ››
ጦማሪ- ተስፋ በላይነህ
“አገሬ በብልጥ ጠላት እየተመዘመዘች
ነው” መረቅ ገጽ 429
የሆነ ከእናቱ ማኅጸን ለወራት ተኮራምቶ/ተቆራምዶ… የቆየ፤ በገመድ ሆዱን
ሽቅብ ቁልቁል አስረው እጆቹና እግሮቹ ተሳስረው፤ አይኖቹ ተጨፋፍነው/ተጨነቡዋቡሰው… የምድር እምብርት ሆዱ ላይ ተጠምጥሞ በሚገኝ
አሁንም ገመድ፤ ከእናቱ ደም እየጠጣ… ታስሯል! ነገር ግን ከተወለደ በኋላ ከሚያጋጥመው ባርነት የተሻለ አይደለም በፍጹም….!
ከዚህ አይነት ስሜት ጋር ነኝ! አልተፈጠርኩም፣ አልተጸነስኩም፣ አልተረገዝኩም፣
አልተወለድኩም፡፡ በስጋም በነፍስም አልተገረዝኩም…፡፡ አገሩ ሁሉ “ነጻነት” መነሻው እና መዳረሻ ደብተራው ሆና ሳለች… በእጅጉ
ተተብትበናል፡፡
እንዳንተነፍስ፣ እንዳንናገር፣ እንዳንጽፍ ከእናት ማኅጸን ከነበርንበት
“ጠባብ” ምድር በላይ ዐለም ጠባኛለች፤ በእናቴ ማኅጸን ውስጥ በነበርኩበት ሶስት የበጋ የጸደይ እና የጥቢ ወቅታት የእጅ፣ እግር፣
ልሳን እና ዓይን ልግመት በእጅጉ በከፋ አይነት እስራት እንደሆንኩ አይነት ስሜት ይሰማኛል፡፡ ያውም በዘመነ “ግሎባላይዜሽን” በዘመነ
“ዴሞክራሲ” .. /“ማናክልድ- manacled” አሰፋ አለሙ/ እንደተመለከተው፤ እግሮቹ በገመድ እንደታሰሩበት፣ በአረንጓዴ አይነት
የተንጣለለ መስክ ቆሞ እንደሚታይ ፈረስ፡፡
ፈረሱን ለምን
ፈጠሩት? ፈጥረውስ ለምን የእግሩን ክንፍ ቀሙት ? ቀምተውስ ለምን “የተንጣለለ አረንጓዴ መስክ ላይ አስቀመጡት? ምን የሚሉት ለበጣ
ነው? ሰፊ ሰበጥራ ዘርግቶ ቆሎ ዝገን አይነት ፖለቲካ-!! ሊዘግኑ ሲሉ ለማሰር! ----ሰፊው ሰበጥራ እኮ ምንም አይነት የሚቆረጠምም፣
የሚቃምም የሚታይም፣ ቆሎ የለውም፡፡ አገሬ እንዲህ ሆናብኛለች፡፡
ሲባል የምንሰማው ሁሉ በአይን
እየሰማን በጆሮም እያየነው ነው እኛ ግን በአይን ማየትም በጆሮ መስማትም እንኳ አልተስተካከልንም፡፡
"ኡፍ….! ይሄ ደግሞ መጣበት
የሚጽፈው ሁሉ የማይገባኝ!" አይነት ስሜት(ሐ) ይሰማኛል፡፡ ስሜቱ አይከለከልም፡፡ ሐሜት እየሆነ ነው እንጂ…!
“ሰይጣን መች ይህችን አገር
ጎዳት” አለ አዳም ረታ… ይሕቺህን አገር የጎዳት ወሬ እንጂ… መረቅ ገጽ/ረስቸዋለሁ/፡፡
አዳም ረታ በ2007 ዓመት ረዥም ልብ ወለድ አስነበበን፡፡ ለልብ ወለድ
በቂ ጊዜና በቂ ቦታ /ፍላጎትም ተጨምሮበት/ ስለሌለኝ ጆሮዬን አልሰጥም፡፡ አዳም ረታ ግን ከልብ ወለድ ጸሐፊዎች የሚለየው ልብ
ወለድ ጸሐፊ ብቻ አይደለም፡፡ ታሪካዊ ልብ ወለድ አይነት ጸሐፊም አይደለም፡፡ ነገር ግን ባልነበሩበት ዘመን ወደ ኋላ አሻግሮ(ታይም
ሜሽን እንደሚሉት) ዘመንን እንድንመለከት፣ እንድሰማ፣ ብሎም- እንድናስብ ብሎም እንድናሸት የሚጋብዘን ጸሐፊ ነው፡፡ ያለፈ ዘመንን
ማሽተት…/በአጭር ቃል የጸሐፊነቱን ስያሜ መስጠት አልፈለኩም!/
አዲሳባ ተቆርቁራ ግንድ እንደሚቆረቁሩ ግንደ ቆርቁር አይነት ማሕበረሰብ
ወካዮች እስኪፈሉባት ድረስ፤ ያለውን ዘመን ለማንበብ፣ ለማየት እና በአካል እንደነበርን ሆነን እስኪሰማን ድረስ፤ ዘመንን መግለጽ…
የጻፈ… የዘመኑ ትሩፋት ሆኖብኛል፡፡ ደራሲው፡፡
ደራሲው ገጸባሕርያትን ሳይሆን ህያው ሰዎችን በቀለም እና “በእንጀራ”
አድርጎ መስራት ችሏል፡፡ ከከዋክብቱ መካከል ተቀምጦ ጉንዳን የሚመስለውን የሰው ልጅ ከላይ ወደታች እንደመመልከት፡፡ አቤት ፓናሮማ…!
[አገሬ] ‹‹ሁልጊዜ ድንግል
ናት፡፡ ሁልጊዜ ትደፈራለች፣ ግን ሁልጊዜ አዲስ ናት፡፡ እየወደቀች መነሳት›› ገጽ 715፡፡
.
.
.
ብቻ አንብቡት እና የተሰማችሁን
ተሰሙት፡፡ ስሙት፡፡
.
.
.
ስለ ጥንቆላ አገላለጽ መዝጊያ አድርጎ የጠቀሰውን “እምነት ሳይውጣችሁ
ተጫወቱበት..” የሚለውን ክፍል አስቀርቼ፤ አንዳንድ መሰል እንጀራ አገላለጥ መተቶችን አሊያም ድግምቶችን ወይንም ጥንቆላዎችን ከእምነቴም
ከአዕምሮ ልቤም አርቄ አነበብኳቸው፡፡
አደራ፡- ታሪክ ሲጽፉ ከሃይማኖተኝነት
ልማም ተላቅቀው መሆን አለበት፡፡ የማሕበረሰብን ሂደት ሲጽፉ /ከነእድፉ፣ ከነጉድፉ/ የነበረ፣ የተደረገ፣ የተወራ፣ የታሰበ፣ “የተፈሳ”
የ.ራ ይጻፋል…. በእንጀራ፡፡ ዘመንን ማጥናት፣ መመልከት የሚፈልጉ ይሕ አይነት አጻጻፍ ይጠቅማቸዋል፡፡ አዳም ረታ ይሕ አይነት
አጻጻፍ ተጠቅሞ ጽፏል፡፡ ጠቅሞኛል፡፡ ሕያው ሰዎች (ገጸ ባሕርያት) ደራሲያን ሲሆኑ፣ የራሳቸውን ራስ ሲቀቡ… ምናባቸውን በሸራ
(ብራና) ላይ ሲጽፉ ትመለከታላችሁ… ብዙ ነው… “እንደ”… አድማስ ባሻገር፡፡
“አድማስን ለመያዝ አይሮጡም፡፡ አድማስን ለመያዝ ከሮጥን የምንደርሰው ከጀመርንበት
ነው(አለም እኮ ክብ ናት)፡፡ ቆም ብዬ ጥቅስ ተበድሬ እንዲህ ካልኩ አነሰኝ? ‹‹ፀሐይዋ ጠልቃ ቀኑ እስኪጨልም ድረስ፡ ነገም ሌላ
ቀን ነው›› ከአድማስ ባሻገር(በዓሉ ግርማ) ፡፡ ሲል አዳም መረቅን ይዘጋል፡፡
አነጣጣሪ
ልቡና፣ አመዛዛኝ ሕሊና ጥንቁቅ አርታዒ ሆነው እንዲያነቡ ተጋብዘዋል፡፡ ከአበውም፣ ከአዳምም ከኔ ከገልቱውም!!
*ይሕ ጽሑፍ ማስታወሻነቱ በእስር ለሚገኙ ጸሐፊያን ይሁንልኝ!
No comments:
Post a Comment