Aug 22, 2014

አለቃ ታዬ ገብረ ማርያም

የአለቃ ታዬ 90ኛ ዓመት የሙት መታሰቢያ ቀን
ነሐሴ 15 2006 ዓ.ም

አለቃ ታዬ ገብረ ማርያም ህዳር 18 ቀን 1853 ዓ.ም በአፄ ቴዎድሮስ ከነገሱ 7 ዓመት በኋላ በደቡብ ጎንደር ይፋግ ተወለዱ፡፡
  ይህ አባባላቸው ለዘመናት ሲዘከር የሚኖር እና ለኢትዮጵያ ባለውለታ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው፡፡
«...እኛ ሀበሾች በመንፈሳዊና በሥጋዊ ጥበብ ወደፊት የማንገፋበት ምክንያት ምን ይሆን? ብሎ ለሚጠይቅ ሕዝቡ ሁሉ ባይማርና ወንጌል ስብከት በብዙው ባይሰማ እውነተኛ እውቀትና አፍቅሮ-ቢስ ትህትና ቢጠፋ ነው .....ባገራችን ጥቂት ዕውቀት ያላቸው ሰዎች በመከበር ፈንታ ስለሚሰደቡና ስለሚዋረዱ ስለሚጠቁም የሚያውቁትን ጠቃሚ የጥበብ ሥራ ትተው በቦዘን መኖርን መረጡ።»
«የአዳምን ልጆች ሁሉ የፈጠረ አድልዎ የሌለበት አንድ ልዑል እግዚአብሔር ነው። ላንዱ ወገን ሕዝብ ሙሉ ላንዱ ጎደሎ ልብ አልፈጠረም .....እንዲህ ከሆነ ስለምን ያውሮፓና እስያ ልጆች ካፍሪካ ክፍልም ጥቂቶች ብልሀተኞች ሲሆኑ ....እኛ ሀበሾች መፅሐፍ ቢማሩ፣ 'ኮቸሮ ለቃሚ' ብር እና ወርቅ ቢሠሩ፣ 'ቀጥቃጭ፣ ቡዳ' እንጨት ቢሠራ፣ 'አናጢ፣ እንጨት ቆርቋሪ' ቆዳ ቢፍቅ 'ጥንበ-በላ፣ ፋቂ' እየተባለ ስም እየተሰጠው ስለሚሰደብ የጥበብ ሥራ ጠፋ። ስለዚህ ጉዳይ ጃንሆይ አስበው እንዲህ ያለው ነገር በአዋጅ እንዲከለከል፣ ሰዎች እንዲከበሩ ቢያደርጉ በሌላ መንግሥት ስምና መልክ በተቀረጸ ገንዘብ (ማሪያ ተሬዛ ብር ማለታቸው ነው) ከመገበያየት በጃንሆይ መልክና ስም ገንዘብ እንዲወጣ ቢያደርጉ ነፃ መንግሥትም ራሱን የቻለና የተምዋላም ይሆናል።»
ይህ ደብዳቤ ከተፃፈ ከአራት ወር በኋላ ጥር 17 ቀን 1900 /«ሠራተኛን በሥራው የምትሰድብ ተወኝ» የሚለውን አስደንጋጭና ብርቱ አዋጅ አፄ ምኒልክ የትምህርትን አስፈላጊነትና የሥራን ክቡርነት አካቶ የያዘውን ታሪካዊ አዋጅ አወጁ።
አለቃ ታዬ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ሲሉ ምጽዋ ላይ አርፈው በዛው ትምሕርታቸውን ተማሩ፡፡ ወደ ትውልድ መንደራቸው በመመለስ የግዕዝ ትምህርትን ተማሩ፡፡ የመጀመሪያ መጽሐፋቸውንም በ1882 ዓ.ም ጻፉ፡፡ የመጽሐፉ ርዕስም መጽሐፈ ሰዋሰው፤ የግዕዝ          ቋንቋ መማርያ የመጽሐፍ መግለጫ የሚሆን›› ይሰኛል፡፡
አለቃ ታዬን ለየት የሚያደርጋቸው በበርሊን ዩኒቨርሲቲ የግዕዝ መምህር ሆነው ማገልገላቸው ሲሆን የ44 ዓመት ጎልማሳ እና ለአገራቸው ስልጣኔ እድገት እና መሻሻል ቀናኢ የነበሩ የ19ኛው እና የ20ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ ምሁር ነበሩ፡፡
የሞቱት ነሐሴ 15 1916 ዓ.ም ሲሆን፤ ከቤተክርስትያን አለቆች ጋር በተደጋሚ አለመግባባት ተከቶባቸው እንደነበር ተጠቅሷል፡፡ የተማሩበት ት/ቤት እምኩሉ በምጽዋ የሚገኘው የሚስዮናዊን ትምህርት ይስበት ስለነበር የነበራቸው የሀይማኖት አስተሳሰብ ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ውጭ ናቸው በማለት ለክስ ቀርበዋል፡፡
አፄ ምኒሊክ ከሞቱ በኋላም የተተካው የልጅ እያሱ መንግስት ስር ከተሰማ ናደው ፊት ወርበው እንደተከሰሱ እና ወደ እስርም እንደሄዱ በታሪካቸው ተጠቅሷል፡፡
ራስ ተፈሪ እንደራሴ በነበሩበት በንግስተ ነስት ዘውዲቱ ዘመንም እንደገባ ደሞዛቸው እና ክብራቸው ተመልሶ የኢትዮጵያ ህዝብ ታሪክ የተሰኘውን መጽሐፋቸውን እንዲጨርሱ ተደርጓል፡፡ ከላይ በተጠቀሰው ዓ.ም በ64ኛ ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በስጋ ተለዩ፡፡

የውጭውን አለም ትምህርት እና ስርዓት ቀሰሙ ዜጎች በአብዛኛው ለኢትዮጰያ ህዝብ ተሸለ እና የነቃ አስተሳሰብ እንዲመጣ ይመኙ እንደነበር ማየት እንችላለን፡፡ ምናልባትም ግን ከውጭው አገር ይዘውት የሚመጡትን የሃይማኖት ትምህርት ከተዋህዶ ሃይማኖት ጋር ባለመጣጣሙ የመገፋት እና ተደጋጋሚ ክስ ሲሰነዘርባቸው ይታያል፡፡ አለቃ ታዬም ይህ እጣ ፈንታ ደርሶባቸዋል፡፡
ለኢትዮጵያ ህዝብ ግን ባለውለታ ናቸው ብዬ አስባለሁ!!


No comments: