እኔና ቤቴ
ተስፋ በላይነህ
እርግጠኛ ነኝ በአሁን ዘመን
ያለው ትውልድ የራሱን አሻራ ለመተው፤ የራሱን አሻራ እየተወ ነው….
በተለይ በፊልሙ ደረጃ ዐለም ላይ ያለውን የፊልም ኢንደስትሪ ጋር በሚደረገው
የዝሆን እና የውሻ ቡችላ አይነት ግብግብ በመፍጠር እየተጣጣሩ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ፊልም አለ ወይንስ የለም የሚለው ክርክር ላይ በተደጋጋሚ
ተሳትፌያለሁ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ፊልም የለም ከሚሉት ወገን ለመሆን የተገደድኩበት ጊዜም ነበር፡፡ አሁንም…
አሁንም ወደ ፊልሙ ‹‹ኢንደስትሪ›› ለመግባት የተጨነቅን የዘመን ትውልዶች
እኛው ነን፡፡ ብዙ ጋሬጣዎች ተደቅነውብናል፡፡ አንድን ፊልም ፊልም ከሚያሰኙ ዋና ዋና ግብአቶች ውስጥ
ታሪክ፣ ‹‹ካሜራ››፣ ፍሰት፣ ጭብጥ፣ ቀረጻ፣ ገጸ-ባሕርያት መረጣ እና ተዋንያን
አመዳደብ እንዲሁም ‹‹ኤዲትንግ›› በዋነኝነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ሌሎችን የተማሩት ይጨምሩበት…
ዛሬ እኔን ቤቴ የተሰኘ ፊልም ለማዬት ብሔራዊ ቲያትር ተገኘን…
የተለመደውን ኢትዮጵያ ውስጥ ፊልም አለ ወይንስ ፊልም ለም የሚለውን
ክርክር ይዘን ገባን፡፡ እኔና እኔ፡፡
ተጀመረ…
በቤር ፉት ፊልምስ የተዘጋጀው ፊልም የተለመወደውን አይነት ፊልም ላለመስራት
የተጨነቀ ይመስላል፡፡ እንዲህ ነው ማደግ የምንችለው፡፡ የተለመደውን ነገር ላለመስራት ስንጣጣር እና የተለመደውን በአይን እና በጀሮ
የሚሰማ እውነተኛ ታሪክ ላይ መስራት በእጅጉ የፊልምን አላማ ያሳካል፡፡ ፊልሙ እውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት፡፡
የገጸ ባሕርይው ትንተናን ሳያስፈልገን… በጀሮ የምንሰማውን ዜና በጨርቅ ብርሃን ላይ ለማሳየት ተሞክሯል፡፡ ውብ አቀራረጽ፣ ውብ
ምልከታ…. እውነታ…
ሙሉ በሙሉ ኢትዮጰያ ውስጥ ፊልም የለም የሚባልለት ፊልም እንዳልሆነ
ግን ልናገር እወዳለሁ… ነገር ግን አያያዙን አይተው እንዲሉ… የሚያጠግብ እንጀራ ከምምጣዱ እንዲሉ… በእጅጉም አያያዛቸውን ልመለከት
ተችሎኛል… በርቱ…
ወጣቶች ናቸው የሰሩት፡፡ ያለ ማንም እገዛ፡፡ በራሳቸው ተነሳሽት….
ምናልባትመ በአሁኑ ሰዓት በሰፊው የተለመወደውን ተደራሲውን ለማሳቅ እና ለማንከትከት የማይችል ፊልም ይሆናል፡፡ ነገር ግን ተደራሲውን/
Audiences/ ለማሳቅ ብቻ የሚሰሩ ሸቀጣ ሸቀጦችን በጣጥሶ ለዚህ አይነት ክብር መጣር የሚያስጨበጭብ ነው፡፡….
ለወደፊት ታሪክ ላይ ብናተኩር፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ያልተነኩ አርዕስት፤
ያልተነኩ እይታዎች እንዳሉ እተማመናለሁ፡፡ አደራ ወደ ሸቀጡ ነፋስ እንደሰንወሰድ…አደራ!!
ዋናው ቁም ነገሩ ወደ ዐለም አቀፉ የፊልም ‹‹ኢንደስትሪ›› ለመጋባት መጣር፣
ሙያውን ማዳበር፣ መመካከር፣ መማር እና ማንበብ አለብን፡፡ ተስፋ አለን…
ካሜራው ከተለመደው የካሜራ አይነት የተሻለ ሆኖ ታይቷል፤ ይሄ አንግሊንግ
እና እይታ የሚሉትንመ ነገር ልብ እያልነው ይመስለኛል፡፡ ሆኖም ለቀሪው ጊዜ የሚታየኝ ተስፋ ነው…
እኔና ቤቴን ጋብዣለሁ…!!
No comments:
Post a Comment