Nov 17, 2014

O.i.L on EBS

ይሕ ጽሑፍ ረዘም ስለሚል በትዕግስት እና በጽሞና እንዲያነቡት ተጋብዘዋል፡፡ በቅን ልቦና ተጽፏልና በቅን ልቦና ይነበብ፡፡

O.i.L on EBS {ዋንስ እን ኤ ላይፍ ኦን ኢቢኤስ}
“በሶስት ብር አባይን እንገድባለን! በሶስት ገጽስ ስንቱን ተማርን- ብልሕ ደግሞ በአንድ ቀን ብዙ ይማራል፡፡”

ተስፋ በላይነህ
    ይሕንን ስም እየሰማነው ነው፡፡ “ዋንስ ኢን ኤ ላይፍ ኦን ኢ.ቢ.ኤስ” እያሉ እድሜያቸው ከ20 የማይበልጡ ታዳጊ ኢትዮጵያዊያን በምትሐተ መስኮት ገጽ መታየት ጀምረዋል፡፡ ያው አዲስ ዝግጅት ከመሆኑ አንጻር እስኪ ትንሽ እንባባል፡፡ ምልክታችንንም እናስተላልፍ፡፡ በሚሰሩ ሰዎች ላይ ተቃርኖ በማቅረብ የሚያድጉ ልጆችን በአጭሩ ለመቅጨት አይደለም፡፡  ጨለምተኛ ለመሆንም ከቶ አይደለም፡፡ “ጌጃ” “ፋራ” ሆነንን አይደለም፡፡ /ከተባልንም መቀበል ነው/፡፡
    ምልከታ በጎ ነገር ነው፡፡ ሰው የታየውን የተሰማውን እና ያሰበውን ሲያከፍል፤ ስንማመር ሐሳብ ስንለዋወጥ ለውጥ ይመጣል፡፡ መግባባት ላይ ይደረሳል፡፡ ወደ ተሻሻለ ማንነት እርከን ከፍ  እንላለን፡፡ እናድጋለን….የጎደለውን እንሞላለን፡፡
ትውልድ፡-
    አንዲት አገር በአንድ መቶ አመታት ውስጥ 5 ትውልዶችን ታስተናግዳለች፡፡ አንድ ትውልድ 20 ዓመታትን ይወክላል ወይም 20 ዓመታት አንድ ትውልድን ያካትታል፡፡
    ኢትዮጵያ ከ1900-2000 ዓ.ም ያሳለፈቻቸውን አምስት ትውልዶች ስንመለከት፤ ከ1800 ጀምሮ የመጣውን በአድዋ ድል ታጅቦ የመጣው ትውልድ 1900 ዓ.ም ላይ ብቅ አለ፡፡ ኩራት አለው፡፡ ክብር ነበረው፡፡ ማንነት ነበረው፡፡ ልዕልና አለው፡፡ አገር አለው፡፡ ባሕል ነበረው፡፡ ግን ገና ሥልጣኔውን አልጨበጠም፡፡ የጎደለችው ኢትዮጵያ ገና አልሞላችም ነበር፡፡ በመገንባት ላይ ነበረች…፡፡
1-  ቀጣዩ ትውልድ ከ1900-1920 የኖረው ያለፈውን ኩሩ ኢትዮጵያዊ ማንነት ይዞ፣ ወደ ዓለም ስልጣኔው ጎራ ለመቀላቀል ደፋ ቀና ሲል የነበረ ነው፡፡ ከምኒልክ ወደ እያሱ እና ወደ ንግስተ ነገስታት ዘውዲቱ ከዚያም ከ1920 ጀምሮ ተፈሪ መኮንንን መሪ አድርጎ አድጓል፡፡ ሁለት ትውልዶች (ከ1880-1900እና ከ1900- 1920) ውስጥ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን አስከፊውን ዘመን ለመቀላቀል በባሕል እና ሥልጣኔ መወዛዘዝ ውስጥ በማዕበል ይንገዳገዱ ነበር፡፡
2-  ቀጣዩ ትውልድ ከ1920 እስከ 1940 ውስጥ ያለው ትውልድ ደግሞ ኢትዮጵያ በአስከፊው የጣልያን ወረራ ስር ቅኝ የወደቀችበትን 5 ዓመታት የግፍ ጽዋ የቀመሰ ነው፡፡ እድለኛ አልነበረም፡፡ የአድዋው ትውልድ በብዛት የአራዊት እራት፣ የጫካ ባይተዋርነት ፈጀው፡፡ ኢትዮጵያን አላስነካም ብሎ ታገለ፡፡ የቻለው ተረፈ፤ ብዙሃኑ ግን አለቀ፡፡ በአንድ ቀን ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያኖች ያልቁ ነበር፡፡ አሁን ላይ ያለነው (እኛ) የቆምነው በእነዚህ ኢትዮጵያኖች አጥንት ላይ ነው፡፡
    ኢትዮጵያ ወደ ሥልጣኔ ደረጃ ለመግባት በምትታገልበት ጊዜ ከአድዋ የተረፈው እና ክብር ይሰማው የነበረው ትውልድ አሁን ሌላ ገጽታ ውስጥ ተገኘ፡፡ ከ928-1933 ዓ.ም የመከራ ጊዜ ሆኖ አለፈ፡፡ ኢትዮጵያ የዲያቢሎስን መሳሪያዎች(መርዝ፣ ታንክ፣ ጠበንጃ፣ የጦር አውሮፕላኖችን) ማምረት ስላልቻለች፤ አልሰለጠነችም ተብላ በዲያቢሎስ መሪነት በሚጋለቡ ፈረሶች (ወራሪ መንግስታት) ተወረረች፡፡
3-  ቀጣዩ ትውልድ ከ1940 እስከ 1960 የሚሆነው ደግሞ አባቶቹ አርበኞች አሊያም ባንዶች ሆነው ጣልያን ጥላው በሄደችው ባዕዳን አስተሳሰብ (ቅልቅል ማንነት) ሲጋራ ማጤስ እንደ እውቀት፣ ሱፍ መልበስ እንደ ዘመናዊነት፣ በቡጊ መሰልጠን እንደ እድገት ለመቁጠር በሚያኮበኩብበት ሰዓት ላይ “ትኩስ” የሚባል ኃይል ነበር፡፡ የአድዋው፣ የማይጨው እና የጣልያን ድምር ውጤቶች በሚሆን ማንነት ላይ ሆኖ ኢትዮጵያን ተቀብሎ ነበር፡፡ ለ1960ዎቹ ዓመታት ለእርድ የቀረበ ሙክት ይመስልም ነበር፡፡ መስሎም አልቀረ-ሆነም፡፡ መምሰል መከራ ነው፡፡ ጣጣ አለው፡፡
    የ1940ዎቹ ትውልድ እንደ ጊዜው አጠራር ያ ትውልድ ተብሎ፤ ኢትዮጵያ ዓለምን ባናወዘው “ሶሻሊዝም”፣ “ኮሚኒዝም”፣ “ማርክሲስም”፣ “ሌኒኒዝም”፣  “ኢምፔሪያሊዝም” “ካፒታሊዝም”… ግብ ግብ ውስጥ ገብቶ- ላለመግባባት መግባባት፣ ለመግባባት አለመግባባት… ተፈርዶበት ተላለቀ፡፡
    በወቅቱ የነበረው ዓለም አቀፋዊ ስርዓት ችግር፣ አጸፋ፣ መፍትኄ በሚለው ስውር ፍስልፍና (ሴራ) ውስጥ ሆኖ ያልገባው እና ሊገባውም ያልፈለገው ትውልድ ፤ከወንድሙ ጋር መግባባት ሲቀለው ያልገባውን ስርዓት “ገባኝ” ብሎ የገዛ ወንድሙን ደም ሜዳ ላይ አፈሰሰው፡፡
አንድ ትውልድ ኪሳራ ላይ ወደቀ፡፡ የቀናው ቤቱ ውስጥ መሽጎ ይሕንን የመከራ እና የግፍ ዓመት አለፈ፡፡ የቀረው ተሰደደ፡፡ የተረፈውም የዘመኑ ተሟጋች ሆኖ አለፈ፡፡ አብዛኛው ሞተ፡፡
4-  1960 እስከ 1980 ደግሞ በጥይት ጩኸት ሙዚቃ፣ በሰልፍ ዜማ እና በአብዮት ቅዳሴ “አድጎ” ኢትዮጵያን በልቡ አስሮ፣ ወደ የት እንደሚሄድ ግን ሳያውቅ በድንግዝግዝም፣ በክብርም፣ በውርደትም፣ በመከራም፣ በፍቅርም፣ በባይተዋርነትም ዝብርቅርቅ ባለ ስሜት አደገ፡፡ ፓለቲካ የማይጠቅም ልብስ፣ የተለየ ፈጠራ እና ሐሳብ ሚያስጠይቅ ጥሪት ነበርና አገሩን ማሰቡም ስለሚያስጠይቀው ወይንም በድትድርና መግለጽ ስለነበረበት እድሜው በፈጣሪ ግዴታ (ዘመን ሲለዋወጥ) አደገ፡፡
5-  1980 እስከ 2000 ያለው ትውልድ አገሩ ወደሌላኛው ምዕራፍ የተዘዋወረችበት ጊዜ ነበር፡፡ “መብቴ ነው” በሚል አስተሳሰብ፤ ዲሞክራሲን እንደ ወተት ሳይሆን እንደ አጥንት እየጠጣ(ጋጠ) አደገ፡፡ 1990ዎቹ ላይ ወደ ዓለም አቀፋዊው ስርዓት እየተማገደ ነበር፡፡ የ1997ቱን ታሪካዊ ማዕበል እንደ 60ዎቹ ባይሆንም በአብዮትነት አስተናገደው፡፡ የጊዜው መዘውር ግን የሚመራው በ60ዎቹ ትውልድ ጭንቅላት ነበር፡፡ ትውልዱ ምንም ሳያይ- የድሮ 60ቹ አሁንም ሳይግባቡ፤ ይሕንን ትውልድ አቀዘቀዙት፡፡ አገር ማለት በውይይት የሚገነቡዋት፣ በሰላም የሚመሯት፣ በመግባባት እና በይቅር ባይነት የሚያስረክቧት አልነበረችምና ይሕ ትውልድ በእውነትም ተስፋው ያለው በሩቅ ምድር፤ ባሕሉ ያለው በውጭው ዓለም እነደሆነ(ያደገውም በዚህ ተስፋ ስለነበር) የውስጥ ዓይኑን አሳውሮ የውጭውን ዓይን ወደ ውጩ አደረገ፡፡ ታሪክ የለውም፡፡ ባሕል፣ ማንነት እና ልዕልና አልተሰበከለትም፡፡ የለውም፡፡
ብዙ ሰዎች “ባሕል ይሻሻላል፡፡ ያድጋል፡፡ ይሞታልም!” ከሚለው ከእውነተኛው ቃል ጋር በማዛመድ የውጭ ባሕል መቀበልን እንደ ሥልጣኔ ሲወስዱት ይታያሉ፡፡
    በእርግጥ ባሕል የሚሻሻል የሚያድግ እና ወደ ከበረ ስብዕና ሊወስደን የሚገባ በእጅ የማይዳሰስ ቁሳዊ ያልሆነ እሴት ነው፡፡ አዎ ባሕል ማደግ አለበት፡፡ መሻሻል አለበት፡፡ ማሕበረሰቡንም ወደ በለጸገ ጤናማ እና ወደተረጋጋ ደረጃ ማድረስም አለበት፡፡
የውጭውን እንዳለ አስመስሎ መቀበል፡፡ መውረስ (ከነጥበቱ ከነስፋቱ) / ከነንፍጡ / (አዳም ረታ በ “መረቅ” መጽሐፉ “ልጅን ሲወዱ ከነንፍጡ” ብሎ ይገልጸወዋል)፣ ያልገባንን ከነተደናበረው (ተንሸዋረረው) ትርጓሜ መቀበል አብሮ መደናበር ነው፡፡ ወደ ጥልቁ መውረድ ነው፡፡ መመለሻውን እንጃ! ለ60ዎቹ ትውልድ ያንን ዘመነኛ ስርዓት መስጠት ለምን እንዳስፈለገ አሁን ላይ መገመት እንችላለን፡፡
    “ፈጣን መኪና ይነዳሉ ነገር ግን የትም አይደርሱም” ስትል አንዲት የምዕራባዊያን ዘፋኝ ስታቀነቅን ሰማኋት፡፡ ደስታን ለመግዛትም ሆነ ለመሸጥ ወደ ገበያ ይሄዳሉ፡፡ የሚገዙት ግን ኪሳራን ነው፡፡
    ይሕን አልተረዳነም፡፡ ያሁኑ ትውልድ ይሕንን አልተገነዘበም፡፡ ይሮጣል አይደርስም፡፡ ያልማል በምርቃና ነው፡፡ ያድጋል በቁመት ነው፡፡ ያውቃል በእባብነት ነው፡፡
    አሜሪካኖች ለውጭው ዓለምም ሆነ ለራሳቸው የሚሰጡት በእጥፍ አድርገው ለመቀበል ነው፡፡ “አይፎን ስሪጂ” ሲሰጡን አይፎን 4ጂን ለመሸጥ ነው፡፡ አይፎን 4 ለአይፎን 5 እና 6 እንዲሁም 7 …ለሌላም ስያሜ እያስተናገዱን ነው፡፡ ሸቀጥ ነው፡፡  ሥልጣኔ የሚወቀስ ነገር አይደለም፡፡ ሥልጣኔ እውቀትን ካላወረሰ፣ ክብርን ካልሸለመ፣ መሻሻልን ካላረጋገጠ፣ ቅድስናን ውበትን፣ ማንነትን ደስታን፣ ጤናን እና መረጋጋትን ካላስቀጠለ ወደየት ነው የምንሄደው?... የት ለመድረስ ነው፡፡ ያውም ሁሉ ነገር በተሟላበት ሰዓት፡፡ እውቀት በተረጨበት ሰዓት፡፡ ወደየትም እንሄዳለን ከኋኛውም የለንበት፤ ከፊተኛውም አልቻልንም ዛሬንም አልያዝንም፡፡
    አሜሪካ እንኩ የምትለን ያለ የሌለንን እንድናስረክባት ነው፡፡ “ኤም ቲቪን” በነጻ የምትሰጠን ምናችንን ለመንጠቅ ነው? የመኪና ፋብሪካ አሰራር እውቀቷን በገንዘብ እንኳ ማስተማር ስትችል “ኤምቲቪን” በነጻ ለአፍሪካ ሕዝብ ማደሏ ለምን ይመስለናል?
    ዓለም በየአገሩ ረጋ ብሎ፣ ውስብስብ ሕይወቱን ለማቅለል እና ዘላቂ ብልጽግናን፣ የራስ ማንነትን፣ መንፈሳዊነትንና ፈጠራን፣ ተፈጥሮአዊ ጤናማነትን በነጻ መስጠት ሲቻል፤ ለምን በሚብረቀረቁ አብለጭላጭ ንዋያት ይነድፉናል? “15 ዓመት ሲሞላን ‘ሬንጅ ሮቨር’ ካልተሰጠኝ የሕይወት ስኬታማነቱ ያከትማል” በሚል ድብቅ ፍልስፍና ስለምን ይሰልቡናል?
    አፍሪካ በኢቦላ፣ በምግብ እጥረት፣ በስደት፣ በጦርነት፣ በእርስበርስ ጥላቻ እና በሥጋዊ ስልጣኔ ከዓለም ዘቅጣ ተቀምጣ መደነስን እንደ እውቀት፤ ሽቱ መቀባትን እንደ ውበት፤ አልባሳት መቀያየርን እንደ ተዓምራት፤ በጢስ መስከርን እንደ ቅድስና፤ በመጠጥ መናወዝን እንደ “እርፍና” ስለምን በምትሐተ መስኮቶቿ ታሰክረናለች? ሥለ ምን አሜሪካን መምሰል የባሕል ሥልጣኔ መገለጫ ተብሎ ከቁርዓን እና ከቅዱስ መጽሐፍት በላይ ተሰበከልን?
    ማጌጥ፣ መልበስ፣ መቀባባት፣ መዘነጥ፣ ፈጣን መኪና መንዳት፣ “ቴክኖሎጂ” ያመረታቸውን ቀፎዎች መነካካት እርኩሰት ነው እያልን አይደለም፡፡
    ኢትዮጵያ ገና ተገንብታ አልተጨረሰችም፡፡ ኢትዮጵያ ወደ ቀናው መንገድ መጓዝ አልጀመረችም፡፡ ትሮጣለች ነገር ግን እዛው ላይ ቆማ ነው፡፡ ያውም ወደኋለኛው ልመለስ እያለች በምትኳትንበት በአሁኑ ሰዓት ፤ የተትረፈረፈውን እና በሰፊው ልበሱ በተባልነው “የባሕል ልኬት” ውስጥ ገብተን መወዛወዝ፤ የሚያየንም የለም፡፡ ሲያዩንም አያምርብንም፡፡ እንዲያው ቢያዩንም ይስቁብናል ይሳለቁብናል፡፡ መመስል ውርደት ነውና!! መምሰል ጣጣ አለበትና፡፡
    ቅድሚያ ሥልጣኔ ነው፡፡ ቅድሚያ ውበት! ቅድሚያ የማይወዛወዝ ጥሪት ሐብት ማካበት ነው፡፡ ቅድሚያ ጥበብ፡፡ በመጀመሪያ ትላንትን ማጤን፣ ዛሬን መጨበጥ ነገን ማሻሻል ነው፡፡ መሰረቱ ሳይገነባ 40ኛው ፎቅ ላይ ብንንጠለጠል ትርፉ(ኪሳራው) ከመሬት ጋር መጋጨት ነው፡፡ ገና ነን፡፡
    በ 20ኛው እድሜያችን ፈጣን መኪና ነድተን መደሰት፤ በእናት ሆድ ውስጥ ያሉ ጨቅላዎችን ማስጨንገፍ ነው፡፡ መደነስን እውቀት አድርገን ማጉራት፤ ሚሚየን ለውቃቤ መናፍስት አምልኮ ማሰናዳት ነው፡፡ ለከባድ ሽቱዎች፣ “ለትርፍርፈ ምግቦች”(“ጀንክ ፉድስ”) ስግደት ነገ ለመሞት መቸገር ነው፡፡ እነሱ እንኳ “ጀንክ ፉድ”፣ “ትኩስ ውሻ” ፣“ሶዳ” ምናምን ብለው በሰዓት ሶስት ጊዜ የሚበሉ የሚጠጡት አሁን ውፍረታቸውን ለማስቀነስ እንባቸውን ወደ ሰማይ እያስረጫቸው ነው፡፡ እኛ እንባን ለመርጨት ባሕል አድርገን ሌት ተቀን እንንቦጫረቃለን፡፡ ሥልጣኔ መስሎን ለመምሰል እንሯሯጣለን፡፡
ለዋንስ ኢን ኤ ላይፍ {oil} አዘጋጆች፡-
    ጥረታችሁ እና ትጋታችሁ በጎ ነው፡፡ መሞከራችሁ አያስኮንናችሁም፡፡ ያላችሁት አድዋን እና ማይጨውን ያሳለፈ፤ ጠላትን ያሳፈረ፤ ታሪክ በሰራ ትውልድ አጥንት ላይ ነው፡፡ የእነርሱ አጥንት እና ደም ተሰባብሮ የፈሰሰው፤ ኢትዮጵያ ባሕል፣ ማንነቷን፣ ታሪኳን እና ስሟን አስጠብቃ ተከብራ እንድትኖር ነው፡፡ መጽሐፍቶቿ ተገልጠው ምስጢራቱ ተመልሰው ጤናማ፣ የበለጸገ አምላክን የፈራ ማሕበረሰብ እንዲፈጠርላት ነው፡፡ ከሺህ አመታት በፊት የተጻፉ የነገስታት ደብዳቤዎችን ብንመለከት ሥልጣኔ እና ጥበብ በዚህች አገር እንድትተከል እና ብርሃን በአገሩ እንዲበራ ነበር፡፡ አይደለም የተጣለ ውራጅ ማንነትን ለመሸከም፡፡ አይደለም ቧልት፣ ብስናት፣ ስካር፣ “ዳንስ” ብቻቸውን እንዲገዙን፡፡ እንድናወድሳቸው፡፡ እንድንኮራባቸው፡፡ አይደለም..፡፡
    ያማረ መኪናን ስናይ ለማምለክ ልንሽዳደም አልነበረም፡፡ ስብን ለሚያሰፋ ምግብ ለመጎምጀት አልነበረም፡፡ ያማረ መኪናን ብረት አቅልጦ፣ ቀጥቅጦ አሳምሮ ለመጠቀም እንጂ…! እኔ ስበላ ዘመድ አዝማድ ጎረቤቱም በልቶ እንዲያድር እንጂ፡፡
    ውራጅ ባሕል ተሸከማችሁ ተብሎ አይደለም ይሕ ሁሉ ውርጅብኝ- አንዴ ማስተዋል እና በጥበብ ማሰብ እድሜ ዘመንን በሙሉ ስለሚያሳምር እንጂ፡፡
    ስንፈጠር ጎዶሎዋች ሆነን ነው፤ ለመሙላት ግን ማደግ አለብን፡፡ celebrating life time once doesn’t make whole life sustainable, rather worry how to be smart and wise then be the reason for the change of own and a nation! Fill the emptiness of our empty brain. Because we are created empty but we grow to be full.  Don’t be fool. Ask, create, be yourself and Brighten the darkness; find a straight way for the wrong turn that our ancestors made. Grow full!
  ይሕኛው ቋንቋ የሚከብዳችሁ አይመስለኝም፡፡ ይሕኛው ትውልድ ይሕንን ቋንቋ እውቀት አድርጎታልና፡፡ ይልቁንስ ከ400 ዓመታት በፊት የነበረ ዘርዓ ያዕቆብ የተባለ ኢትዮጵያዊ ፈላስፋ የተናገረውን ላስታውሳችሁ፡፡ ዋናው ዓላማው “የጎደለውን መሙላት” ነው፡፡ በግዕዙ እንዲህ ይላል “እምተክህሎ ለእግዚአብሔር ይፍጥረነ ፍጹማነ ወይረስየነ ብፁዓነ ዲበ ምድር፡፡ ወባሕቱ ኢፈቀደ ይፍጥረነ ከማሁ፡፡ ወፈጠረነ ድልዋነ ለተፈጽሞትነ”
    መምሰል መሆን አይደለም፡፡ መሆንም መምሰልን መምሰል የለበትም፡፡ ለመሟላት እንደግ፤ የጎደለውን ለመሙላት ሽቁር ለመክደን እንትጋ፡፡ የሚጠቅመውን እንመልከት፤ የሚበጀውን እንመስርት ዛሬንም ነገንም እንሞላለን፡፡ “ዋንስ ኢን ኤላይፍ” ተዘፈነ፤ ተበላ፣ ተጠጣ፣ ተዘነጠ ጥሩ ነው// -ነገስ?
በሶስት ብር አባይን እንገነባለን! በሶስት ገጽስ ስንቱን ተማርን- ብልሕ ደግሞ በአንድ ቀን ብዙ ይማራል፡፡

ይሕ ጽሑፍ ረዘም ስለሚል በትዕግስት እና በጽሞና እንዲያነቡት ተጋብዘዋል፡፡ በቅን ልቦና ተጽፏልና በቅን ልቦና ይነበብ፡፡
O.i.L on EBS {ዋንስ እን ኤ ላይፍ ኦን ኢቢኤስ}
“በሶስት ብር አባይን እንገነባለን! በሶስት ገጽስ ስንቱን ተማርን- ብልሕ ደግሞ በአንድ ቀን ብዙ ይማራል፡፡”

No comments: