መቅድም
የያ ትውልድ ንስሃ
ከትውልድ ሁሉ “ያ!”፡፡ በታሪክ
ውስጥ “ያ” ተብሎ የሚጠራው ያ ትውልድ፡፡ ለዘመናት ሲወራረስ የተለመደውን ቅብብሎሽ ዱላ አልቀበልም ያለ ያ ትውልድ፡፡
ታሪክ ባለድርሻ ብሎ እጣውን
ወደ ትውልድ ሲበትን ፤ እጁን ወደ ፊት አድርጎ እጣ ያነሳ ፤ ትከሻውን አጎንብሶ ለሸክም የተዘጋጀ፣ ደረቱን ግልጦ ለጥይት የሰጠ
አይኑንም ጨፍኖ የዘመኑን እጣ የተቀበለው የ1960ዎቹ ትውልድ ነበር፡፡
ተወልደው ያደጉት፣ እትብት ከርስት ጋር የተቆራኘበትን እጣ ፈንታ ኢትዮጵያን ወደ ቅያስ መስመር እንድትቀለበስ እና ላልታሰበ ወጥመድ እንደትዘጋጅ የታሪክ ፍርድ የሆነ- ያ ትውልድ!፡፡
ስለ 1966ቱ አብዮት ብዙ ተብሏል፤
ከትውልዱ አባላት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሃሳብ ተሰጥቶበት በጽሑፍ እና በምስል መረጃዎች እንዲቀሩ ሆነዋል፡፡
አብዛኛዎቹ በአብዮቱ ቀጥተኛ
ተሳታፊዎች/ የፓርቲ አባላት፣ በጦር ሰራዊቱ ውስጥ፣ በት/ቤቶች ውስጥ ፣ በመንግስት መስሪያ ቤቶች በነበሩ እና መሰል ተሳታፊዎች
ያቀረቡዋቸውን ምልከታዎች አንብበናል፡፡
በተለይ ለ “በያ ትውልድ ስም
መጠሪያነት በመጽሐፉ ያስነበበን ክፍሉ ታደሰ፤ ተስፋዬ መኮነንን ይድረስ ባለታሪኩ እና የተለያዩ የጽሑፍ ስራዎች በበሰለ አጻጻፍ፣
ከሀቅ ጋር የተዋደዱ፣ ከቀናነት ጋር የተጣበቁ እንዱሁም ለመጪው ትውልድ አስተማሪዎች ሆነው እንዲቀመጡ ቢደረግ የሚገኘው ጥቅም ዘመን
ተሸጋሪ ከመሆኑም አንጻር ከትውልድ መማማርን አይነት ትልቅ ስልጣኔ ለማውረስ አቅጣጫ ያስይዘናል፡፡
ሥለዚህ ይህንን ግምት ውስጥ
በማስገባት፤ በ1960ዎቹ በንቃት የነበሩ የኢትዮጵያ ልጆች፣ ከተራው ሰርቶ አደር እስከ ማዕከላዊ ኮመቴ አባላት ድረስ እያንዳንዱ
ስለ ዚዘጌው የተሰማውን እና ያጋጠመውን፤ ምን አይነት ለውጥ እንደ ነበር፤ ምን አይነት ስህተት፣ ምን ምን እንደተከናወነ በሃሳብ
ባህር ውስጥ ሆነን በትረካ መልክ ብንሰማ ጥቅም ሊያስገኝ መቻሉን የምንጠራጠርበት ግንዛቤ ሊፈጥር አይችልም፡፡
ይህም ማለት የግድ በ1940ዎቹ
ተወልደው በ1960ዎቹ የነበረውን ትውልድ ገጠመኝ እና ምልከታ ብቻ የምንዘግብበት ድርሳን ሳይሆን፣ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል
ግለሰብ፣ በዘመኑ የተጓዘውን መንገድ፣ የወጣ የወረደውን ጎዳና፣ ምስቅልቅል ፤ በአይኑ ያየየውን እውነተኛ ድርጊት የሚዘግብበት የሚሆን
ነው፡፡
በ1966 የስንት ዓመት እድሜ
ነበሩ?
በምን ሁኔታ ላይ ይገኙ ነበር?
በት/ት? በስራ? የት ቦታ…? ምን ያስቡ ነበር?
በምን አይነት የለውጥ እንቅስቃሴ
ውስጥ ተሳትፈዋል?
ምን አይነት ገጠመኝ አጋጠመዎት?
እንዴት አላፈ? እንዴት አሳለፉት?
ምን አይነት ዋጋ አስከፈለዎት?
ከለውጡ በኋላ በምን አይነት
ስራ ውስጥ ገቡ?
70ዎቹ እንዴት አለፈ?
ምን አይነት መሻሻል ወይንም
ውድቀት ለማስተዋል በቁ?
80ዎቹ እና ሌላኛው የመንግስት
ለውጥ እንዴት አለፈ በምን? ስራ/ቦታ ላይ ነበሩ?
ምንም እንኳ ለንጽጽር መቅረብ
የማይችሉ መንግስታት ቢሆኑም የሶስቱን መንግስታት ሂደት ንጽጽር እንዴት ይመለከቱታል?
ኢትዮጵያ ከ1966ቱ ለውጥ ምን
አገኘች? ምንስ አጣች ለውጡ አስፈላጊ ነበርን….?የግል አመለካከትዎትን ያስቀምጡ፡፡
አሁን ኢትዮጵያን እንዴት ይመለከቷታል?
የነገዋ ኢትዮጵያ ምን ልትመስል
ትችላለች ምን እንድትሆንስ ይመኛሉ…..?
እነዚህን እና መሰል ጥያቄዎችን
በልቦናዎ ይዘው እያሰላሰሉ ያሳልፉትን ታሪክ ያስቀምጡ፡፡ በአጠቃላይ የሕይወት ጉዙዎትን ለትውልድ የምናስቀምጥበት ቅረስ ነው፡፡
“የያ ትውልድ ንስሃ” በሚል የቀረበው ስራም ይህንን ለማሰናዳት
ተብሎ የታሰበ፤ ከልበ ቀናነት በመነጨ መነሳሳት የተሰናዳ ስራ ነው፡፡ በጽሑፍም በቃለ መጠይቅም ታግዞ ተዘጋጅቷል፡፡
ከትውልድ የሚገኝ ልምድ፣ የሚተላለፍ
ትምህርት/ እውቀት መጪውን ትውልድ የመለወጥ እና ተሸሻሎ እንዲቀርብ የሚያስችል ስጦታ እናገኛለን፡፡ ስምዎ ቢጠቀስ በጎ ነው፡፡
ሆኖም ግን ግዴታ አይደለም፡፡ ከንጹሕ ልብና ከበጎ ሕሊና ግብዝነትም ከሌለበት እምነት በሚወጣ ፍቅር ተመስርቶ የሚቀመጥ ድርሳን
እንዲሆን አዘጋጁ አጥብቆ ይማጸናል፡፡ ይህ የትዕዛዝ ፍጻሜ ነውና፡፡*
ምንም አይነት ስልጣን፣ ስራ፣
ብሔር፣ ሃይማኖት እንዲኖርብዎት አይጠበቁም ሁላችንንም ኢትዮጵያዊ
ማንነት ያስተሳስረናል፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ተወልድን የነገዋን ኢትዮጵያ ትንሳኤ የምንናፍቅ ዜጎቿ ነን፡፡ እኩል ነን- አንድም
ነን!!
አዘጋጁ፡፡
*ጢሞ 1፡5
ያግኙን tesfabelayneh@gmail.com
tes_bel@yahoo.com
1 comment:
man i can't wait to c the end! well in 60s i wasn't part of it but i am desperate to hear the story as i believe so much scarification was paid we real have something to learn so as to do our part for the next generation. but my view at the moment of that generation is clever, brave and conscious and who never got the reward that deserve after so much fight "the regime" take over which wasn't the type of change they hope for and my thought for the 70s is the same "woyane" takes over the change which leads into chaos but both 60s and 70s have fought bravely for freedom, better system and improvement and my expectation of the book is to clearly state the strengths and weakness of that generation straggle and why that kind of straggle couldn't bring the change it fights for but only succeeding in changing the system only.
and that's were we start as a new generation to fight and change our reality and bring the system we needed!! respect man!!
Post a Comment