Jul 18, 2014

ቅኝት ባሕርዳር- ዋጋ ካስከፈሉኝ መጽሐፍት ጋር

24 ሰዓታት ‹‹ከአብርሃ ድስታ›› ጋር ¡ ¡ ¡
የምታነቧቸውን መጽሐፍት በእርግጥ ልብ ብለዋቸኋቸው ያውቃሉ? ዋጋ የሚያስከፍሉት መጽፍሐት ለምሳሌ፡-
‹‹እኛ እና አብዮቱ››፤ ‹‹አቤቶ ኢያሱ አነሳስና አወዳደቅ››፤ ‹‹ኃይለ ማርያምን ፍለጋ››፤ ‹‹የትግራይ ህዝቦች ወያኔዎቹና ሽፍቶች››፤‹‹ዶ/ር አሸብር››፤ ‹‹ኡመተ ፈናን ኡመተ ቀሽቲ ድሬዳዋ››፤ ‹‹ያ ትውልድ››፤ ‹‹ከደርግ ማህደር››፤ ‹‹የአሲምባ ፍቅር››፤ ‹‹የካድሬው ማስታወሻ››፤ ‹‹ህዝብና ነጻነት››፤ ‹‹101 የሰላማዊ ትግል መንገዶች›› ፤ ‹‹ያልተሄደበት መንገድ››……… ዋጋ ያስከፈሉኝ መጽሐፍት…..¡¡¡¡¡¡¡¡¡¡¡

‹‹ቅኝት ባሕርዳር- ዋጋ ካስከፈሉኝ መጽሐፍት ጋር¡¡¡¡¡¡››
‹‹‹‹‹‹‹ተስፋ በላይነህ›››››››
……
‹‹አባዱላው›› ወደ ባሕር ዳር የያዛቸውን ሰዎች ይዞ፤ አንድ የቀረው እያለ ሲጣራ፤ አንደኛው እኔ ነበርኩ፡፡ ተያይዘን ጉዞ ወደ ጣና ዳር፡፡ የክረምቱን ዝናብ እያቆራረጥን፣ አረንጓዴዋን ኢትዮጵያ እያማተርን፤ የለመለመውን መስክ እየሸኘን የጣና ዳርን ከተማ ጸሐይ ስትሸሻት- እኛ ስንደርስ እኩል ተገጣጠምን…! ‹‹ተገጣጠሙ›› የሚለው ሙዚቃ በረዥሙ ይሰማም ነበር፡፡
በጉዞ ላይ ባለ ‹‹አምስት›› ወይንም ባለ ‹‹አራት ኮከብ›› ሆቴሎችን መዳሰስ አይመቸኝም፡፡ ለምን አይመቸኝም?  ራሳችሁ ናችሁ የምታውቁት፡፡ ለኔ ግን አይመቹኝም…..-፡፡
ይልቁንስ “couch surfing” የሚባል ድህረ ገጽ አለ፡፡ መንገደኞች ዓለምን ሲዞሩ የሚገለገሉበት ነው፡፡ ምናልባትም ኢትዮጵያዊ መንገደኞች/ tourists/ አባል የሚሆኑበት እና አንድ ሰው ወደ አንድ አገር/ከተማ መንገድ ሲያስብ አስቀድሞ በዛ አገር ውስጥ አሊያም ከተማ የ “couch surfing” አባል የሆነን ግለሰብ መልዕክት ይልክለታል፡፡
ለምሳሌ እኔ፡-
ወደ ባህር ዳር ጉዞ ሳቀና አስቀድሜ ባህር ዳር ለሚኖር አንድ የ couch surfing አባል መልዕክት መላክ ይጠበቅብኛል፡፡
“ታዲያስ አበበ- እኔ ሐምሌ 11 እንደ ኢትዮጵያን አቆጣጠር ወደ ባሕር ዳር እመጣለሁ፡፡ የምቆየው ሁለት ቀናት ብቻ ሲሆን አንተ ቤት ላርፍ ዘንድ በእንግድነት ብትቀበለኝ ምን ይመስልሃል? የማይመችህ ከሆነ ሌላ አማራጭ ልጠቀም፡፡ እጅግ አድርጌ አመሰግንሃለሁ፡፡ ያንተው፡፡” የሚል፡፡
ይህንን ያነነበበ ሰውም እንደ ፈቃደኝነቱ እና እንደ ጊዜው ሁኔታ እሺታውን አሊያም የማይመቸው መሆኑን ይገልጻል፡፡ ሁሉም በኢንተርኔት ነው ግንኙነቱ፡፡ አንተዋወቅም….-፡፡
ለዛሬ አልተሳካልኝም፡፡ የዛሬው የ “couch surfing” አባል ሌሎች እንግዶችን ስለሚያስተናግድ እንደማይመቸው ‹‹በኢሜሌ› ደረሰኝ፡፡ ያለው አማራጭ ሌላ የ couch surfing አባል መፈለግ አሊያም ዘመድ ጋ መደወል፡፡ ‹‹ባለ አምስት ኮከብ›› ሆቴል ማፈላለግ ጠፍቶኝ እንዳይመስላችሁ፡፡…. አይደለም፡፡ ጭራሽ አ.ይ.መ.ቸ.ኝ…..ም!!! ሃሃሃሃሃ
ዘመድ ጋር ስደውል እሺታው በአንዴ ነበር የተገኘው፡፡
“የመሸበት እንግዳ ትቀበላላችሁ?” ከዘመናዊው ከውች ሰርፊንግ ባሕላዊው የእንግድነት ጥየቃ ተሳካ፡፡
“የመሸበት እንገዳ ትቀበላላችሁ?”
ዘመዴ እንዲህ መለሰች፡፡ “ተገኝቶን ነው…!!”
ባጃጅ ኩንትራት ወደ ‹‹አየር ሓይል›› ሰፈር፡፡ ቦታው ወደ ባሕር ዳር ኤርፖርት ወደ ሚወስደው መንገድ ስለሆነ አንድ ምስኪን የባጃጅ ሾፌር እንዲወስደኝ ጠይኩት፡፡ በነገራችን ላይ ባጃጅ ኩንትራት ስትጠይቁ ሾፌሩ የገጠር ሰው ከሆነ ታድላቹሃል፡፡
እዋራችሁ… የልብ የልቡን እያጫወታችሁ… ትጓጓላችሁ… አይሰለቻችሁም፡፡ መንገድ ላይ አቁሞም..
“አየህ ወደ ዘመድ ቤት ሲኬድ ባዶ እጅ አይገባም፡፡ በቆሎ.. ሙዝ አሊያም ብርቱካን ተይዞ ነው የሚኬደው!!” ብሎ የዘመድ ጥየቃ ደንቡን በግልጽ ያማክሮታል፡፡ እንዲህ ያለ የባጃጅ ሾፌር ከወዴት ይገኛል…?
እየመሸ ስለሆነ መንገድ ዳር ከሚገኝ ትልቅ ገበያ/ super market/ ጎራ ብዬ፤ ትንሽ ነገር  አንጠልጥዬ፤ ጎዟችን ቀጠልን፡፡ ወደ አየር ኃይል መንደር፡፡
ዋናውን የኤርፖርት መንገድ ሳንጨርስ፤ ወደ ቀኝ ‹‹ፒስታ›› መንገድ ታጥፈን ትንሽ እንደገባን፤ የአየር ኃይል መንደር የመጀመሪያው መግቢያ በር ላይ ቆሜ ስልክ ወደልኩ፡፡ ጸጥ ያለ በከፍተኛ ቁጥጥር የሚጠበቅ መንደር ነው፡፡ ጸጥታውን ወደድኩት….!
ዘመዶቼ መጡ፡፡
በር ላይ የመሸጉት የመከላከያ ልብስ የለበሱ ሶስት ወንዶች እና ሁለት ሴቶች ለፍተሻ ተባበሩን ተባለ፡፡
ጥሎብኝ የመከላከያ ሰዎችን እግባባቸዋለሁ፡፡ ሊፈትሱኝ ሲቀርቡ… ላፕቶፔን እንዲህ እቀልዳቸዋለሁ፡፡
“አይ ትንሽ ቢጤ ቦንብ ናት….¡” እላቸዋለሁ
ብዙዎቹ ይስቃሉ፡፡
መታወቂያ ተጠየኩ፡፡
አሳየሁ፡፡
በጀርባዬ ያዘልኩትን እንዳወርድ ተጠየኩ፡፡
አሳየሁ፡፡
ላፕቶፕ ነው…፡፡ /ቦንብ ነው ማለት አይቻልም፡፡/ ሁልጊዜ ሲቀለድ አይኖርም!!!! ጠንቀቅ ነው አንዳንዴ፡፡
ቀጥሎም በእጄ የያዝኩት ጓዝ እንዲፈተሽ ተጠየኩ፡፡
ተከፈተ፡፡
መጽሐፍ እንደበዛ ተመለከቱ፡፡
“አንባቢ ነህ ባክህi?” አለኝ፡፡
“ያው ምን ስራ አለ ብለህ ነው…?” አልኩት፡፡
የመጽሐፍቶቹን አርዕስት መመልከት ቀጠለ፡፡
‹‹እኛ እና አብዮቱ››
‹‹አቤቶ ኢያሱ አነሳስና አወዳደቅ››
‹‹ኃይለ ማርያምን ፍለጋ››
‹‹የትግራይ ህዝቦች ወያኔዎቹና ሽፍቶች››
‹‹ዶ/ር አሸብር›› ደሞ እቺ ምንድናት? እያለ ማንበብ ቀጠለ፡፡
‹‹ኡመተ ፈናን ኡመተ ቀሽቲ ድሬዳዋ››፡፡ ምን ማለት ነው? ብሎ ጠየቀኝ ወደ ርዕሱ እየጠቆመ… “አይ …” ብዬ ሳልጨርስ ወደሌላው ቀጠለ፡፡
‹‹ያ ትውልድ››
‹‹ከደርግ ማህደር››
‹‹የአሲምባ ፍቅር››
‹‹የካድሬው ማስታወሻ››
‹‹ህዝብና ነጻነት››
‹‹101 የሰላማዊ ትግል መንገዶች›› ብሎ ካነበበ በኋላ በታላቅ ጥርጣሬ አይን ተመለከተኝ/ ገላመጠኝ/ ብል አልተሳሳትኩም፡፡.. ኩም ብዬ ቀረሁ…
‹‹ያልተሄደበት መንገድ›› ላይ ሲደርስ ሙሉ በሙሉ አቆመ፡፡
“ወደ የት ነው የምትሄደው አንተ?” ብሎ ጠየቀኝ፡፡
“አይ…” እንዳልኩ አሁንም ሊያስጨርሰኝ አልቻለም፡፡
ወዲያዉኑ ያዘውን ሬድዮ/ ወኪቶኪ/ ከጀርባው መዥለጥ  አድርጎ፡፡ የኮድ ቁር ነካ፡፡
“ጥቁር በሬ” ብሎ ሲናገር ብቻ ሰምቸዋለሁ፡፡
ከዛ ወደ አራት የሚደርሱ ጥቋቁር ቪ ስምንት/V-8/ ‹‹ኮብራ›› መኪናዎች ከጀርባዬ ከበቡኝ፡፡ አራቱም በእኩል ፍጥነት ተከፈቱ፡፡
የያዝኩትን ላፕቶፕ እና መጽሐፍቶቹ እንዱሁም እኔ ለምርመራ እንደምፈለግ ነግረውኝ ወደ መሃከለኛዋ ‹‹ኮብራ›› መኪና እንደገባ ጠየቁኝ፡፡……. ከብዙ መንገድ በኋላ….
የት እንዳለሁ ኣላውቅም፡፡… ጭለማ ክፍል ውስጥ ነኝ፡፡
የአንድ ሰው ድምጽ ሰማሁ፡፡
ስሙን ሲነግረኝ ለማመን አልቻልኩም፡፡ አብርሃ ደ..ስ……ታ!!!!!!!????? እባላለሁ የሚል ድመጽ ሰማሁ…..
ይቀጥላል፡፡
ቀጣዩን ክፍል ለማንበብ ይህንን ጠቅ ያድርጉ…
…….
ቀን ቀን በብስክሌት ማታ በ ‹‹ኮብራ›› 

….ወደ አየር ኃይል መንደር የወሰደኝ የባጃጅ ሾፌር ዋጋ ጠየኩት…
“ደስ ያለህን ስጠኝ” ብሎ ፈገግ አሳኘኝ፡፡
20 ብር አልኩት፡፡ እሺ ብሎ ልቤን ነካው…
“50 ብር መስጠት ነበር….” ብዬ አሰብኩና 30 ብር ሰጠሁት፡፡ በጣም ተደሰተ…. ይህን ዐይነት አባባል ያገኘሁት ከኮሜዲያን ልጅ ያሬድ ነበር፡፡ ልጅ ያሬድ ማታውን  ዮሴፍ በቤት ውስጥ ትዕይንት///‹‹በጆሲ ኢን ዘሐውስ ሾ››/// ሲያዝናናን ነበርና….!
ወደ መጀመሪያው መግቢያ በር ስደርስ፤ ስልክ ደወልኩ፡፡ ዘመዴ መጣች፡፡ ከባለቤቷ ጋር፡፡
መታወቂያ ተጠየኩ፡፡
አሳየሁ፡፡ ስሜ ተመዘገበ፡፡ ያለምንም ፍተሻ እንድገባ ተጠየኩ፡፡
ፍተሻውን ሳስበው ከበድ ያለ እንደሚሆን በመገመት ብቻ በሃሳቤ ብዙ ርቀት ተጓዝኩ፡፡ ያ ሁሉ ፍተሻ፣ ያ ሁሉ ‹‹የኮብራ›› መኪና ጋጋታ የሐሳብ የተፈጠረ የሆሊውድ ፊልም ጋጋት ነበር……..
እነ ዛ መጽሐፍት ግን ዋጋ አስከፍለውኛል ያልኩት፤ የገዛሁበትን ዋጋ ሳሰላስል ስለነበር ነው፡፡ ከአንድ ባለ አምስት ኮከብ አሊያም አራት ኮከብ ሆቴል ከማደር እነዚህን መሰል መጽሐፍት መግዛት አይሻልም ትላላችሁ…???¡¡¡
የውቢቷ ባህር ዳር “አዳር እና ውሎዬ” ግሩም ነበር፡፡ ዘመዴ ሁለት ልጆች አሏት አቤል እና ዳዊት ይባላሉ፡፡ /ስማቸው ለዚህ ጽፍ ሲባል የተየረ/
ዳዊት የ3 ዓመት ሕጻን ሲሆን፤ አቤል ደግሞ የ3ኛ ክፍል ህጻን ነው፡፡ እንዴት የሚያማምሩ ህጻናት መሰሏችሁ!!
ዳዊት ከዚህ በፊት አያውቀኝም፡፡ ስሜ በር ላይ ሲመዘገብ ብቻ ግን ሰምቷል፡፡ እቤት ከገባሁ በኋላ ሙሉ ስሜን ሲጠራው ተደነቅሁ፡፡
“ማን ነገረህ?” ስለው
“ክ..ክ…ድም ሰምቼ ነዋ!” አለኝ፡፡ እቅፍ አድርጌ ሳምኩት፡፡
እግሬን ስታጠብ ተከትሎኝ መታጠቢያ ቤት ገባ፡፡ “ሻሙና ላ..ንጣልህ” ብሎኝ “አዎ…” ከማለቴ በፊት ሮጦ ሄዶ ሳሙና አመጣልኝ፡፡
ወደጅ አግኝቷል፡፡
“ማነው ስምህ አልኩት…?”
`ዳ..ዳ..ዊት….
“ስንተኛ ክፍል ነህ?”
“አምሽት…!” /ሃሃ እድሜው 3 ክፍሉ አምስት!!/
ገና ጡጦውን እኮ አልጣለም፡፡ ግን አምስተኛ ክፍል ነው፡፡
“የት ነው የምትማረው- ጠየኩት፡፡”
“አካዳሚ////”
“የት አካዳሚ” ጠየኩት፡፡ “አካዳሚ ነዋ አ..አታውቀውም እንዴ..” ጠየቀኝ መልሶ…
//ባሕር ዳር አካዳሚ ታዋቂ ት/ቤት ነው፡፡ የእጅጋየሁ ሽባባው እህት የት/ቤቱ ባለቤት እንደሆነች ከዚህ በፊትም አውቅ ነበር፡፡
ጎረቤቱ ተሰብስቦ ቡና እየተጠጣ፣ በቆሎ እየተጠበሰ እኔም አንጠልጥያት የሄድኳት ደረቅ ብስኩት እየተጎረደመች/ በጣም አስቸጋሪ ነበር/ ስለ ት/ቤቶች ይወራ ነበር፡፡
“ባህር ዳር አካዳሚ እንደ ድሮው አይደለችም” በጣም ተቀዛቅዟል እየተባባሉ ሲያወሩ እሰማ ነበር፡፡
የዳዊት ታላቅ ወንድም ወደ ኔ መጣ፡፡ የቴሌቭዚኑን ሪሞት ኮንትሮል ይዞ፡፡
ቀኑን በሙሉ ቲቪ ላይ አፍጥጦ እንደሚውል አባቱ ነገረኝ፡፡ ያው ክረምት ስለሆነ ቤት ውስጥ ብቻውን ሲውል ይሕንን ‹‹የአረብ ዲሽ›› ይኮመኩማል፡፡
አቤል ሪሞቱን ሰጠኝ፡፡ ቀኑ ሐሙስ ስለሆነ ‹‹ኢ.ቢ.ኤስ›› ላይ የምከታተለው / የነ Habtamu Seyoum ‹‹የብራና ልጆች›› የተሰኘ ዝግጅት እንዳለ ነግሬው ሪሞቱን ተቀብሎ ቀየረልኝ፡፡
አብረን ተመለከትን፡፡ በጣም ወደዱት፡፡ ከዚህ በፊት አይተውት እንደማያውቁ ነገሩኝ፡፡ ከጀመረ ብዙም እንዳልቆየ እና ሁልጊዜ ሐሙስ ሐሙስ ከ2 ሰዓት ጀምሮ እንዲከታተሉ አስተዋውቄያቸው ወደ ሌላኛው ወሬ እና የቴሌቪዥን ዝግጅት ተሸጋገርን፡፡
አቤል የት ነው የምትማረው ብዬ ጠየኩት፡፡
“ኃይሌ” አለኝ፡፡ ----  እንዴት ነው ት/ቤቱ አልኩት፡፡ /የኃይሌ ገ.ስላሴ ት/ቤት ነው/
አቤል ለመመለስ ሲያመነታ አባቱ መለሰልኝ፡፡
“ባክህ እንደ ስሙ እና እንደሚጠበቀው አይደለም” ሲል መለሰልኝ አባት፡፤
“ምነው አልኩት…?”
“ያው ኃይሌ ሲጀመር በዓመት አንዴ ነው ብቅ ሚለው፡፡ ወላጅ ያለበትን ቅሬታ ሲያናግረውም”  ብሎ ጠለ፡-
“ዌል እንግዲህ ትምህርት ቤቱ የሁላችንም ነው.. በጋራ ተረባርበን ነው የምንገነባው… ችግሩቹንም የምንፈታው…..” ከማለት ውጭ ሌላ መፍትኄ ሲያመጣ አላየንም ብለው ስሞታቸውን ነገሩኝ፡፡ / ከመስማት ውጭ ምን እናደርጋለን- አንደንዴ የምሳማውን የምጽፈው ቢያንስ የሰውን ድምጽ ያስተጋባሁ አየመሰለኝ ነው፡፡/
ቀጠለ ወሪያችን፡፡ አንዱን አንዱን ስናወራ፡፡ እየመሸ መጣ፡፡ አቤል እና ዳዊት ዛሬ እንቅልፍ የላቸውም፡፡ አዲስ እንግዳ መጥቷልና፡፡
‹‹ጆሲ ኢን ዘሐውስ ሾ›› ጀመረ፡፡/ለምን በእንግሊዝኛ እንደሚጠራ አልገባኝም/፡፡
የዛሬው የትዕይንቱ ተጋባዥ እንግዳ ልጅ ያሬድ ነው፡፡
ሁላችንም አብረን ተከታተልነው፡፡ አቤል እና ዳዊትን ሳናያቸው አምልጠውን ወደ ክፍላቸው ሄደዋል፡፡ አቤል የልጅ ያሬድን ‹‹ስታይል›› ነው የምከተል ብሎ ጠጉሩነ ላይ የቦሎውን ጭራ ነስንሶ መጣ
ዳዊት ደግሞ የጆሲን ‹‹ስታይል›› አስመስሎ ጠጉሩን እንደ አውራ ዶሮ ቆብ ሰበጥሮ መጣ፡፡ የጆሲ ኢን ዘ ሀውስ ሾ ለሕጻናት የሚፈድ ነው… በተለይ የልጅ ያሬድ እንግድነት ህጣናት የማይደርሱበት ቦታ ተብሎ መለጠፍ ነበረበት… ዘንዶ ጋር ይተኛ ነበር… ጫካ ውስጥ ይኖር ነበርና… እኔም ፈርቼ ነበርና…!
ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚተላለፉ መሰል ዝግጅቶች የሚደርሰውን ተጽዕኖ ማን ነው ኃላፊነቱን የሚወስደው? ቤተሰብ? የጥበብ ሰዎች? መንግስት?......
ከመጣነው መንገድ ይልቅ የምንጓዘው ያሳስበኛል… እናንተንስ?
መሸ… ተኛን… ብለሜ ለ24 ሰዓታት ከአብርሃ ደስታ ጋር እንደታገትኩ ተመለከትኩ… ያ ሁሉ ህልም ነበር፡፡ ሃሰቡን ተጋራሁት!! የማለዳ ወፍ በጥዋት ቀሰከሰችን//// የማለዳ ወፍ!!
ቁርስ ቆረስን… ለመዋያ የሚያገለግለኝን ቁልፍ ተረከብኩ… ዋው….!!!!! ባህር ዳርን በብስክሌት---- እንዴት ታምራለች!!!
ብዙ መንገድ ተጓዝኩ…. ከመጣሁት ይልቅ የምጓዘው ረዥሙ እንደሆነ  እየተሰማኝ ነው… እናንተስ?
Bahir Dar









No comments: