አሁን ዘላለማዊ ናት!!!
ለረቂቅ መሳፍንት ባዘዘው….
‹‹‹‹‹‹‹ተስፋ በላይነህ›››››››
በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ የፖለቲካ፣
የስልጣን እና የጥቅም ጥያቄ የለኝም፡፡ ነጻ ነኝ! ነጻነትን የምዘምረውም ለዚህ ነው፡፡ የታሪክ ተማሪም ሆነ አጥኚ/ተመራማሪም/
አይደለሁም፡፡ በተደጋጋሚ ስለ ታሪክ ነክ ጉዳዮች ስጽፍ ያለፈውን ናፋቂ… ከትላንት ብቻ ጋር ተጣባቂ… የአሁኑን እና የነገውን የረሳ
እንዳያስመስልብኝ እሰጋለሁ፤ ሰውም እንዲህ እንዳያስብብኝ እማጸናለሁ… በአሁን የማምን ፍጡር ነኝ!!
ኢትዮጵያዊነት ክፉ በሽታ የሚል
ረዘም ያለ ግጥም አለኝ… ትላንትን፣ ዛሬን፣ ነገን ስናስብ የሚያመን ጊዜ ጥቂት አይደለም! ኢትዮያዊነት የሚያም በሽታ አለው፡፡
ምናልባትም የሰው ልጅ ታሪክ በሙሉ አስታማሚ እና ታማሚ የሚታይበት ይመስለኛል፡፡ በተለይ የጥቁር ሕዝብ ታሪክ፡፡
የጥቁር ሕዝብን ታሪክ ስናስታውስ
የኢትዮጵያን ታሪክ መርሳት፣ መፋቅ እና አለመተረክ እንደማይቻለው ሁሉ፤ ሥለ ሰው ልጅ ነጻነት፣ ማንነት፣ ታሪክ፣ ዛሬን እና ነገን
ስናስብ ኢትዮጵያን አለማንሳታችን ስለማይቻለን ነው.. ተመልከቱት ሰንደቁን፣ ተመልከቱት አንበሳውን፣ ተመልከቱት ባሕሉን፣ ተመልከቱት
ስብጥሩን፣ ተመልከቱት ታሪኩን፣ ተመልከቱት ጭቆናውን፣ ተመልከቱት ቅድስናውን፣ተመልከቱት ዝማሜውን፣ ጥበቡን፣ ቁጭቱን፣ ስደቱን፣
ፖለቲካውን፣ ….፡፡
ታሪክ ያለውን ጥቅም ከተገነዘብን
ብቻ ነው ስለ ታሪክ ማውራት የሚገባን፡፡ ታሪክ ሬሳ መደብደብ አይደለም፡፡ ታሪክ ሙትን መውቀስ ብቻ አይደለም፡፡ ታሪክ የበቀል
መርፌ አይደለም፡፡ በቀል የእግዚአብሔር ነው!!!!!
ታሪክ ተረት ተረት አይደለም፡፡
ታሪክ አፈ ታሪክም አይደለም፡፡ ታሪክ ፋክት ነው፡፡ ታሪክ የዛሬንና የነገን ፍትህ፣ ልዕልና እና ህልውና የምናይበት ለሰው ልጅ
ብቻ የተሰጠ የፊት መስታውት ነው፡፡ ታሪክ ስፖኪዮ ነው ወዳጄ፡፡ መኪና የሚነዳ ሰው የፈቱን ሁልጊዜ እየተመለከተ ወንበር/ዛሬ/
ላይ ተቀምጦ በስፖኪዮ የኋላውን ማየት አለበት፡፡ ታሪክ እንዲህ ነው ዛሬን በጥንቃቄ መንዳት፣ የፊቱን አስተውሎ መመልከት፣ የትላንትናውን
ማስታወስ… የትላንትናው መስታውት ውስጥ ጽልመት ሊታየን ይችላል… ይሕ ደግሞ አሁንን ይገልብናል… ነገን ያጨልምብናል…
ሆኖም ትላንትን እያስታወስን
ትላንት ከፍ ያልንበት ጉዳይ ነበረን፤ አሁን ለምን ዝቅ አልንበት፡፡ ትላንት የወደቅንበት አስቀያሜ መንገድ አሁን ለምን እየደገምነው
እንገኛለን ብለን እንተይባለን፡፡ ትላንትን የያዘ ዛሬን እና ነገን መያዝ እንደሚችል ምሁራኑ ይነግሩናልና!!!
ዛሬን ስመለከት፤ ነገን ሳስብ
ትላንትን መለስ ብሎ ማዬት ግድ ሲሆንብኝ ታሪክ አገላብጣለሁ፡፡ በአሁን የማምን ሰው ነኝ!! አሁን የመዳን ቀን ነው.. አሁን አድርገው..
አሁን አሁን አሁን!!!! አሁን ትልቅ ስጦታ ነውና፡፡ በእጅ ላይ የተቀመጠ የንስሃ የይቅርታ ቀን…!!
አሁን ዘላለማዊ ነው!! አሁን
አልፎ አሁንን ሲተካ ያች ሰከንድ እና ደቂቃ ማለትም አሁን ዘላለማዊ ናት….!!
አሁን ላይ ቆሜ ዘላለማዊነቴን
ጤዛማ የሚያስመስሉብኝ፤ በየአሁኑ መሞት ለማንነቴ ሲደርሰኝ አዝናለሁ.. አሁንን ትቼ ትላንትን እንዳስብ እና በክፉ ጠኔ እንድመታ
ያደርገኛል…!! ሬሳ ደብዳቢ ከመሆን እንዲያድነኝ የጸለይኩት ጸሎት፣ ያስገባሁት ስእለት ደርሶልኛል!!
በታሪክ ውስጥ ከሬሳ ደብዳቢነት
ያውጣችሁ፤ ሞተው የተቀበሩትን ከመውቀስ፣ ከመደብደብ፣ ከመጥላት ይሰውራችሁ አሁን ላይ ታሪክ እንስራ!!!
አሁኔን እያጨናገፉ ያሉ ነገሮች
ጥቂት አይደሉም… ካስፈለገ መጥቀስ ይቻላል… ሆኖም አሁኔን/ ዘላለማዊነቴን/ እየገደሉ ያሉትን ነገሮች የማክምበት፣ የማድንበት የማስነሳበት
ኃይል በየአሁኑ እማጸናለሁ… ፈጣሪ እንደማይነፍገኝ በማመን በተስፋ እማጸናለሁ… በተስፋ መማጸን የሰው ልጅ እጣ ፈንታ ነውና…..!!
የተሰደደው በሰላም እንዲመለስ፣
የተጨቆነው ቀንበሩን እንዲያለዝብለት፣ የተገዳደሉ ህዝቦች እንዲዋሃዱ ይቅር እንዲባባሉ፣ ባቢሎን ግንብ በተጠነሰሰው፤ በበርሊን ግንብ
አምሳያ ለተራራቀው ህዝብ አንድነትን፣ ቦለቲከኞች አንድ መሆን ባይችሉ እንኳ ሁለት እንዳይሆኑ በመማጸን፣ የጠራች ኮከብ አልባ ሰንደቅ
ዓላማን እንዲመለስልን፣ አንድነታችንን በሰንደቅ ዓላመው አርማ ቃል ኪዳን የሚገባልንን ዘመን ስንጠባበቅ ይኼው ተጎንብሻለሁ… የሰው
ልጅ እጣ ፈንታ የሆነውን የመማጸን አዱኛ ለግሶናናልና…!!!
የፈሰሰው ደም ሁሉ በፍቅር እንባ
እንዲታፈስ፣ የተቆረጠው ማሕጸን ሁሉ በአሜኬላ እንዳይሞላ፣ የተዘራው ዘር ሁሉ በእሾህ ላይ እንዳይበቅል… የሚያጭዱት የዘሩትን እንዲያገኙ/
የዘሩት መልካም እንዲሆን በመመኘት…/ የተበታተነው ሁሉ ወደ እናት እቅፉ እንዲመለስ… በለመለመው መስክ እንዲቦርቅ… በዕረፍት ውሃ
ዘንድ እንዲሰማራ… ኢትዮጵያ ገነት እንድትሆን… ምደር ገነት እንድትሆን..የተለያዩት አባትና ልጅ እንዲሳሳሙ… አሁን ዘላለም እንድትሆን…
በተስፋ የምማጸን ምስኪን ተስፋ ነኝ!!! ክፉ ጊዜ በድንገት ወድቆብን እንደተጠመድን ግን ልቤ ያስባል… መጽሐፉ እንዲህ ይላል..
‹‹እኔም ተመለስኩ ከጸሐይ በታችም
ሩጫ ለፈጣኖች፣ ሰልፍም ለኃያላን፣ እንጀራም ለጠቢባን፣ ባለጠግነትም ለአስተዋዮች ሞገስም ለአዋቂዎች እንዳልሆነ አየሁ፡ ጊዜና እድል
ግን ሁሉን ያገናኛቸዋል፡፡›› መክብብ 9፡11
No comments:
Post a Comment