#እኛ እና #የዐለም ዋንጫ!
/እኛ እና የዐለም ዋንጫ? ሰው “እኛና አብዮቱን” ይጽፋል… እኛ ስለ ዐለም ዋንጫ እንጽፋለን….ህም!!/ “ቤቤቶ፣ የካሜሮኑ የወገብ በታች ውዝወዜ፣ ሮቤርቶ ቢያጆ……” ‹‹‹‹‹‹‹ተስፋ በላይነህ››››››› ያኔ ልጅ እያለን የዐለም ዋንጫን ለማዬት በመንደራችን የባለቀለማማ ቴሌቪዥን ከነበሩበት ከእነ እያዩ አብደላ ቤት እንሄድ ነበር፡፡ አሊያም ከእነ ገብረ አናንያ፣ አሊያም ከሃምሳ አለቃ ታረቀኝ፣ አሊያም ከጋሽ ዘወዱ፣ ወይንም ከጋሽ ተሻገር ቤት፣ ፣ ወይንም፣ ከእነ ጋሽ ተሾመ፣ ከእነ አለሙ ነጋ፣ ከሃምሳ አለቃ ይርጋ፣ ወረድ ካልንም ከአባ መሰለ ቪድዮ ቤት ወዘተረፈ…ወይንም ደግሞ ከነ እትዬ አማከለች ቤት!!!!! በእጅጉ አስደሳች ጊዜ እንደነበር አሁን ትውስታችን ድቅን እያለ የማይመለሰውን ትላንት እያስታወሰን “አይ ጊዜ!” እየተባባልን ነው፡፡ አሁን ሁሉም ተበታትኗል፡፡ መንደሩም ጭር ብሏል!!! ወደ ዘላለሙ ጸጥታ የሄዱም አሉ- ነፍሳቸውን ይማር….!!! ዝም!!!! አንዳንዴ ግርም እያለኝ ወጥቼ መሃል መንደር ላይ ቆሜ እመለከታለሁ፡፡ መንደሩ ጭር ብሏል!!! ታሪክ ያልሰራ፣ ጊዜ ያላሳለፈ ይመስላል….! አልፎ አልፎ ብቅ ብቅ የሚሉ አዳዲስ ፍጥረታት መንደሩን ለማሞቅ የሚጣጣሩ ይመስላሉ፡፡ አሊያም ተጋርዶብኛል፡፡ እየተጫወቱም፣ እየተሰባሰቡም ይሆናል፤ እንደዚያን ጊዜ ግን ሊሆንልኝ አልቻለም፡፡ ምናልባትም ሁሉም ነገር እንደ ድሮው ይሆናል ብለን መጠበቅ የዋህነት ነው ልትሉኝ ትችላላችሁ፡፡ ካልሆነም ወግ አጥባቂነት….!!! መንደሩ ግን ጭር ብሏል…. “ጭር ሲል አልወድም!” አለች እንግዳ ዘር ነጋ፡፡ የእነ እንግዳዘር ነጋ ቤትም አሁን እንደድሮው ቁጭ እንዳለ አለ….ቤቱ እንዳለ ነው፡፡ ኮብል ስቶን ግን ተነጥፎለታል!!!!!!!! ባልሳሳት 5 የዐለም ዋንጫዎችን ለማስተናገድ ችለናል፡፡ // በእኛ እድሜ ያለን ሰዎች በማየት// አፍሪካም የዐለም ዋንጫን ማስተናገድ የቻለችበትን ተራን ጨምሮም ለመመልከት ችለናል፡፡ እነ ‹‹ሮቤርቶ ቢያጆ›› “አሞራው በሰማይ ሲያይሽ ዋለ” ፤ እነ ‹‹ቤቤቶ›› ለልጁ ክንዱን እያወዛወዘ መልዕክቱን ሲየስተላለፍ፣ ሮማርዮ፣ ክሊንስ ማን፣ ስቶቲችኮቭ፣ እና መሰል ገጠመኞች በአዕምሮዬ ድቅን ይላሉ፡፡ ያኔ ልጅ እያለን… አልቅሰናል….! ያኔ ልጅ እያለን… ተቃቅፈናል…!. ያኔ ልጅ እያለን በሌሊት እየተቀሳቀስን መስዋዕት ከፍለናል….ያኔ ልጅ ነበርን!! ያኔ ልጅ እያለን ጨርቃችንን ቀድደናል….! ለናይጄሪያ አልቅሰናል…!! በእንግሊዝ ጭሰናል!!!! ያኔ ልጅ እያለን አፍሪካን ደግፈን አንብተናል…. ብራዚልን ከእነ ዘላለሙ እንድንጠላ ያደረገ ቁጭትም ተሰምቶናል…. ((ምናልባት አሁን ለአለም ዋንጫው ዝግጅት እተንጎራደደች ያለችው ብራዚል እንዲህ ሰላሟን ያጣቸው ሞሮኮ ላይ በሰራችው የያኔ ግፍ ይሆን እያልን እንድንመጻደቅም አድርጎናል….)) እነ ምስጦፋ ሃጂ ያነቡት እንባ እኛምን አስነብቶናል.. ማን ይረሳዋል?? ያኔ ሞሮኮዎች ምንም እንኳ በቆዳ ነጭ ቢመስሉም፣ በሀይማኖትም ከሞላ ጎደል እነ ሙስጤን ቢሆኑም በአፍሪካዊነት ስሜት ወደናቸዋል፣ ሐይማኖታቸውንም እንድናስታውስ ሆነን አላራቅናቸውም፡፡ በሐይማኖት ሳንቧደን አንድነታችንን አሳይተናል…! ወደናቸዋል…! ደግፈናቸዋል…! አንብተንላቸዋል….!!! አሁን ያ ልጅነት ተቀይሯል፡፡ ዘመን ተቀይሯል፡፡ እነ እማማ አማከለች፣ የሁላችንም እናት፣ የሁላችንም አሳዳጊ፣ ባለ በሌለ ማጀታቸው፣ ‹‹አቡ ወለድ›› ብስኩትን በሚያስንቅ ቂጣቸው አጥግበውናል /ቂጣ- ጠብቅ ብሎ ይነበብ/ ፡፡ እማማ አማከለች አብረውን ዘለዋል፡፡ በዛ በሚያምር በአማርኛ እና በትግርኛ ቅላጼቸው አስደስተውናል፡፡ የሚገርመው በርካታ ጊዜ የሚያወሩን በትግርኛ ነበር፡፡ ይገባን ነበር፡፡ በፍቅር እንወዳቸው ነበር፡፡ አብረውን ጨፍረዋል፤ አብረውን ደግፈዋል፡፡ የዐለም ዋንጫን በክፉ አንስተነው አናውቅም!!!! በአንዱ ዋንጫ ግን እትዬ አማከለችን እየተላቀስን ከነቤተሰባቸው ሸኘናቸው……. ከዛም ደም ተቃባን…..!!!!!! አሁን ግን ዘመን ተቀይሯል፡፡ ጉርብትናን የጨረቃ ያክል አርቆብናል፡፡ አሁን እማማ አማከለች ኤርትራ ባሕርን እየተመለከቱ፤ ቀይ ባሕርን እያማተሩ በብቸኝነት ቁዘማ አለም ዋንጫን ያስተናግዳሉ፤ ሊመለከቱ ይችላሉ፤ ወይንም ጭራሹኑ ሊመለከቱት አይችሉም!!!! ከዘመን ተኳርፈዋል!!!!!! አሊያም በሕይወት ሊኖሩ እይችሉም ይሆናል…፡፡ በጥቁር ድንበር በእሾህ ታጥረናል….. ዐለም ዋንጫ ያምመን ጀምሯል!! አሁን አድገናል… ዐለም ዋንጫ ያመመናል!! አሁን አድገናል… የዐለም መነሳት፣ የዐለም ከፍ ማለት፣ መጨፈር፣ መዝለል፣ መቆጨት፣ ማልቀስ፣ ማዘን…- ላይሰማን- ባይተዋር አድርጎናል፡፡ አገር በሚሉት ፍቅር ተሰውረናል፡፡ ዐለም ዋንጫ ያመን ጀምሯል!!! የአገራችንን ቁስል ትተን ስንጨፍር አይታየንም፣ የአገራችንን ልዩነቶች እየተመለከትን፣ እየዘነጋን በሌሊት እየተነሳን ኳስ አናይም፡፡ አሁን ኳስ ያምመናል…!!! ከድሮ ጓኞቻችን ግማሹ ባህር ማዶ ተንጠልጥሏል… ግማሹ በሱስ ተጠምዶ እየታረሰ ይገኛል…ግማሹም ኳስ ለማየት ብራዚል ይሄድ ይሆናል!! ኳስ ያመኛል!! እንደኔ በኳስ እግሩ ያልተገባበጠ ኢትዮጵዊ ያለ አይመስለኝም! በየአመቱ የሚነሳ፣ በበጋ የሚደርቅ ቁስል በጉልበቴ ላይ ነበረ፡፡ ክረምት ክረምት ሲመጣ ይገሸለጣል፣ ሶስት ቀን ይድናል፣ በአራተኛው ቀን ይነሳል…ይላጣል…ይደማል…. ነግ ግን ህመም አልባ ቁስል መሆኑ አሁን ይደንቀኛል!! ህመም አልባ የስጋ ቁስል…!!! አሁን ግን ቁስሉ ደርቆ ከእግር እና ከስጋ ላይ ተለይቶ፣ ጠባሳውን ብቻ ትቶ፣ በልብ ውስጥ ተቀምጧል!! የአለም ዋንጫ ያመኛል!! የአገሬ ፍቅር ክፉኛ በልቤ ውስጥ ተጠብሷል፡፡ ክረምትና በጋን ሳይለይ በየጸሐይ መግባት እና መውጣት ሳይሻር በልቤ ውስጥ ቆስሏል፡፡ የአገር ፖለቲካ፣ የማሕበራዊ ቀውስ፣ የባሕል መምታታት፣ የትውልድ መጥፋት፣ የጥበብ መክሰር፣ የጠቢባን ልሳን መዘጋት፣ የወጣቱ ግዞት እና ስደት፣ በተለይ ‹‹የመንደር ባዶነት›› እና የእማማ አማከለች እንባ በልብ ውስጥ ቆስሎ ታትሟል፡፡
የአለም ዋንጫ ያምመኛል!!!! የእግር እና የስጋ ቁስል በወቅቶች ሲድን፣ ህመሙም ሳይሰማ ሲቀር አይተናል፡፡ እድሜ ለዘመነኛ ቴክኖጂም “ጠባሳ እናጠፋለን” የሚል ህክምናም ተጀምሯልናል፡፡ የልብ ላይ ቁስል በምን ይፈወስ ይሆን….? የእማማ አማከለች እንባስ በምን ይታፈስ ይሆን??? የዐለም ዋንጫ ያመኝ ጀ.ም.ሯ.ል!!!!!!!!!! አሁን ብራዚላዊያን፣ ያውም የኳስ ጠበብቶች፣ ኳስ ባህላቸው፣ ኳስ ፊደላቸው፣ ኳስ ቁርሳቸው የሚባሉቱ “የኳስ ወጭው የተጋነነ ነው!” እያሉ ነው፡፡ እየተቃወሙ ነው- ሰልፍ እየወጡ ነው…………፡፡ እኛስ????? የኳስ “አደጋገፉ የተጋነነ” ወጭን ብንቃወም ምን እንባል ይሆን!!? ኳስ ካለው ስሜት አንጻር፣ ከስጋዊ እና ከውስጣዊ ሰላማዊ ጦርነቱ አንጻር ከምድረ ገጽ ይጥፋ የምንለው አይነት የምድር ትሩፋት አይደለም፡፡ ጠባሳችን ይፋረደናል… የእማማ አማከለች ጭፈራም ትውስ ይለናል…..!!!! ኳስ ልዩ ስሜት አለው…! ልዩ አገራዊ መስተጋብርን ሊያመጣም ይችላል… ግን እንደኔ በልብ ሕመም ውስጥ ለሚሰቃዩ ምስኪን ተራ ኢትዮጵያዊያን፤ ያውም እንደዛ ሙስጦፋ ሃጂን ላስለቀሰችብኝ አገር፡- ድጋፌን፣ ጊዜዬን፣ ገንዘቤን፣ ስሜቴን፣ እንዲሁም በሕሊና እስር ለሚሰቃዩ ታላላቅ ተምሳሌቶቼ እና የእድሜ እኩዮቼን ዘንግቼ…. ኳስ ልመልከት? ልጨፍር? ላልቅስ? ጨርቄን ልቅደድ? ወጥቼ መንደሬን በሙሉ ልቀውጥ?? ልውጣ ብል ዘመን ይረግመኛል!! ብወጣም መንደሬም “ባዶ ነኝ” ይለኛል…… ያልተጠናቀቀ የቤት ስራ አለብን….!!! ያኔስ ልጅ ነበርን……! አሁን ግን አድገናል….!!! የዐለም ዋንጫ ያ…መ…ና…ል!!!!!!!!!
እማማ አማከለች በአስመራ!!
|

No comments:
Post a Comment