ኑ! “ቤት” እናፍርስ…
Tesfa B.
እንጉርጉሮ- ሽለላ እና ፉከራ ተሰማ፡፡ ከራማ የነፍሳት ጩኸት እንደተባለው… ከዚህም ከዚያም ዝምታ ተሰማ፡፡ ከራማ ለተሰማው ጩኸት ነጻ-ውጪ ተሰየመ፡፡ ስለምን የአጋዚያን/ነጸ-አውጭዎች/ መልክ ተቀየረ? እነዚያ ህጸናት ሲጨፈጨፉ እነዚያ የሰማይ መላዕክት የት ነበሩ? ለካስ አጋንንት የሰለጠኑበት የፍዳ ዘመን ምስክር ነበር!
እንጉርጉሮ- ሽለላ እና ፉከራ ተሰማ፡፡ ከራማ የነፍሳት ጩኸት እንደተባለው… ከዚህም ከዚያም ዝምታ ተሰማ፡፡ ከራማ ለተሰማው ጩኸት ነጻ-ውጪ ተሰየመ፡፡ ስለምን የአጋዚያን/ነጸ-አውጭዎች/ መልክ ተቀየረ? እነዚያ ህጸናት ሲጨፈጨፉ እነዚያ የሰማይ መላዕክት የት ነበሩ? ለካስ አጋንንት የሰለጠኑበት የፍዳ ዘመን ምስክር ነበር!
ግጥሞች ተገጥመዋል፡፡ ቤት መትተዋል፡፡
የኛ ጥያቄ “ግጥሞቹ ሲገጠሙ የት ነበራችሁ?” የሚለው ይሆናል፡፡ ሐሳቦች ሲታለሙ- ድርሰት-ቲያትር ሲሆኑ የት ነበራችሁ? አሁን
እንዴት “ትወናውን አቁሙ! አፍርሱ!” ትሉናላችሁ? ትላንትናም አይደል እኒያ ሁለት የአንድ እናት ማሕጸን ክፍዮች- የአንድ አፈር
ብቃዮች ቃታ ተሳስበው እጃቸው ሳይፈታተል ለአገናነዝ ሳይመቻቹ ወደ ግብዓተ መሬታቸው ያሸለቡት-የተቀበሩት-የሞቱት? በአንድነታቸው
መሬት ላይ ተጨካከኑበት!!
ቤቶች ይሰራሉ፡፡ ቤቶቹ ሲሰሩ
የት ነበራችሁ? ስንትና ስንት ባድማ እና ቀዬ አልፈን ካሳ የተመዳደብንበትን መንደር፤ ደቦ የተለጋገስንበት ሰፈር፤ ጥል ያፈረስንበት
ቅጥር፤ ጉማ የበላንበትን አድባር ጥለን መጥተን፤ መንደር ስንመሰርት የት ነበራችሁ? ከ3 እና ካራት እንዲሁም ካስር በመቶም የሚመለስ
ቤትም ሆኖ በሆነ… በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶችን ስንገነባ፣ እንጨት ስንለቃቅም፣ እሳት ስናቀጣጥል፣ እራት ስንበላ፣ ብርሃን ስንከራይ፣
ደቦ ስንመላለስ፣ ጥል ስናበርድ፣ አድባር ስንመሰርት የት ቆያችሁን? ለምንስ እያላያችሁ አያችሁን? እያያችሁ አላያችሁን? ስለምን
አፍርሱ አላችሁነ? እኛ ነነ ጥፋተኛ? ምን አረግነ? ምንስ በደልነ?
ገንፎን አስቀምጠን- ገንፎን
ተቀምተን ምን ልንውጥ እንስማማለን? ገንፎውን በቅቤ እንዳናቦካው ከብቶታችንን ሸጠን ቆርቆሮ ገዛነ-መሬቶቻችንን ለልማት ተውነ-
ማገር አቆምነ ጭቃ አቦካነ-ደማችን አቦካው “ገንፎ ቁጭ” ብለን ስም ሰጠነ…. ስለምን አፍርሱ አላችሁነ?
ካህናቱ መሳሪያ ሲገዙ ተመለከትን፣
አሙሃይ እልፍኟን ሰፍራ መቃብር ምሳ አዘጋጀች፣ ነግቶ የሚመሻሸው ነገር እንዳይወልድ ህጻናት በት/ቤት መዝሙራቸው ዝማሬ ያሰሙን
ከጀመሩ ሰነባበቱ፤ መንግስት እና ህዝብ “ቲካ ቲካ” “የእንቁልልጭ” ሒሳብ ከተወራረዱ መሬቱን ደም ለቀለቀው! አፈሩን ስጋው አበከተው!
አገሩን ቁራ አበላሸው…
ቁራነት፣ቂምነት፣ቂልነት አገሩን
እንዳያበላሸው ባገሩ ባህል እና ወግ ቢሸመጋገሉ መልካም ነው፡፡ ሰባት ቤት ገንብቶ ገንፎ ቁጭ የተቀመጠ ካለ ስለ ሰላሙ አምላክ
ብሎ ሰላምን ይመዝን፡፡ በኋላ በራሱ ባያገኘው በልጁ አያጣውም! ለልጆቻችን ቁልቁለት አናውርሳቸው!!
በጥበብ ካልተፈታ የታሰረው ገመድ
ውሉም አይገኝ፡፡ የ44ሺ ነፍሳት ጩኸት ዕዳ አበሳ ነው፡፡ መሸናነፍ ጨዋታውን አይመልሰውም፡፡ “መንግስት
ተሸንፎ ለምርጫ አሳብቦ ማረን” ቢባል፤ “ህዝብ ህገወጥ ሆኗል አፍርሱ!” ተብሎ ለማሸነፍ ቢነሳ ማንም አይጠቀምም፤ በቀዳዳው ሾልከው
የሚነጉዱት ሸክሞች የትየለሌ ይሆናሉ!!
ጥበበኛ መሪ መፍትኄ አያጣም… ፍቅር ጥበብ አለው -ጥበብ መፍትኄ…
መፍትኄው ሰላም “ገንፎ-ቁጭ”
“የብሔር ብሔረሰብ” ነጋሪት
ከተጎሰመ ጀምሮ- አመጸኛው የሰው ልጅ ከበጎው ክፉን፤ ከክፉውም በጎውን እየወሰደ ሰው ከሰውነቱ በላይ ጎሳን እያጎነ፣ እያገነነ
እኩል ነን ሲል ተደመጠ፡፡ እኩልነቱንማ ፈጣሪ መች ነፈገው? ሰው በፈጠረው ወሰን ተለያይቶ ተነካከሰ እንጂ! አሁን “ቅማንት-አማራ”
በሚል መስመር ህገ-መንግስታዊ ጥያቄ ተነስቶ መልስም የለም ጥያቄም አላቆመም፡፡ በፍቅር አልተመላለስንም፡፡ ማንም ከማንም አይበልጥም-አያንስምም፡፡
ባልተረጋገጠ ሃሳብ አመጽ ሲወለድ-ዱላ እና ብረት ስልጣን ያገኛሉ፡፡ ደም ይፈላል… ሜዳ ላይ ይፈሳል… አጥንት ይዝላል… ስጋ ይተላል፡፡
ዛሬ ይለጠጣል፤ነገ ይጠፋል፡፡
ፍቅር ግን ያሸንፋል፡፡ ፍቅርን አልጨበጥናትም… አንድነትን አልሰበክናትም…
ኢትዮጵያን አልከፈልናትም…..!
ተጻፈ፡- በጎንደር ከተማ በተልምዶ
“ገንፎ ቁጭ” ተብሎ በሚጠራ ሰፈር “የጨረቃ ቤቶች” ይፍረሱ-አይፍረሱ በሚል መጉረምረም ለተነሳ ሃሳብ…
በአማካይ ከ 40 ሺ በላይ ነዋሪዎች
10 አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ተሰርተዋል፡፡ “እስካሁን ይሕ ሁሉ
ህገ-ወጥ ቤት ሲሰራ ማን አይዟችሁ አሏቸው?” ትልቁ የህዝብ ጥያቄ ሲሆን፤ “በህገወጥ
መንገድ ቤት ሰርቶ መኖር” ደግሞ ህግ አልባነት መንግስትን ስለሚያስወቅሰው ይሕ ደግሞ ሌላኛው ችግር ነው፡፡
የቅማንት ሕዝብ የማንነት ጥያቄ
በፍቅር ይፈታ ዘንድ እንማጸናለን፡፡ ዝምታው ሰላም አይመስልም፡፡ ክፉ ዝምታ ሰላም አይመልስም፡፡ ረመጥ፡፡ ለልጆቻችን የመቆራረጥ
እና የመተላለቅ ታሪክ አናውርሳቸው… አንድነታችንን ስበኩልን… የትላንትና ታሪክ “የድካም ስህተቶች” ዛሬ እንዳያሳውሩን… ከትላንት
እንሻል! ዛሬ እንለወጥ ነገን ብሩህ እናድርግ…
“የአኖሌው ሐውልት” ከሩቁ ይጣራል…
እንደ እፉኝት ልጆች ስብዕናችን ለመቀየሩ መስካሪ ሆኖ ተገንብቷል፡፡ ለግንብማ ማን እንደ ባቢሎን?? !
በጥበብ ጫፍ፣ በሰላም ሰልፍ፣
በፍቅር ክንፍ በርሮ መጥቶ የጭለማውን ርጋታ በበትር መትሮ የሚለያይልን ወደ ብርሃኑ የሚያሸግርልን “ሙሴ” ያስፈልገናል፡፡
ጥበበኛ መሪ ያሻናል!! ፍቅር
ይሳሳናል…ጩኸቱ እንዲህ ይላል “ሰላም!!” በናንተስ?
ቅጅ
v ለተከበሩ ካሳ ተ/ብርሃን
v ለፐ/ር መስፍን ወ/ማርያም
v ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ
v ለአብርሃ ደስታ
v ለከንቲባ
v ለአፈንዲ ሙተቂ
v ለአምባሳደር ዘመነ ካሰኝ
No comments:
Post a Comment