Jan 6, 2014

ብርሃነ ልደቱ እንጂ x-mas ስትሉኝ እናደዳለሁ፡፡

ብርሃነ ልደቱ እንጂ x-mas ስትሉኝ እናደዳለሁ፡፡ ታላቅ በዓል ነው! በምድር ሆነን ነገስታትን የምናስብበት፡፡ የፈጣሪያችንን ገዥነት፣ አለቃነት፣ የፍቅር መገለጫውን እና ስጦታውን የምናበስበት ታላቅ በዓል፡፡ በልባችን ብርሃን ይብራ! 
“Sorry the operation is failed, Good bye” የሚል መልክዕክት ከ*804# ቢደርሰንም ከዛሬ 2006 ዓመታት በፊት የተወለደው ክርስቶስ  “አፐሬሽኑ” ስለማይወድቅ/ፌል ስለማያደርግ/ በርሱ እንጽናናለን፡፡ ይብላኝ ለህዳሴ አቀንቃኞቹ እና ለባራዕዮቹ፡፡ የኛም ችግር ደግሞ ይህ ይመስለኛል፡፡ የምደር ነገስታትን እንደ ሰማያዎያኑ ወይ አግዝፎ የማየት አሊያም እንደነሱ እንዲሆኑልን መጣር፡፡ የምድር ነገስታት ችግርም ይህ ይመስለኛል፡፡ እንደ ሰማያዊያን ነገስታት ራሳቸውን ዘለአለማዊ ማድረግ፤ አሊያም እንደ ሰማያዊያን ነገስታት ተደርገው እንዲቆጠሩ መጣር፡፡
ውልደት ትንሳኤ ነው፡፡ ውልደት የህያዊነት መነሻ ነው፡፡ “ኦፐሬሽኑ ፌል” የሚያደርግ ሰርዓት የያዘ ንጉስ ውልደት የለውም፣ ትንሳኤም እንደዚሁ፡፡ ዛሬ የተወለደው ንጉስ ግን ትንሳኤም ህይወትም ነው! የውልደቱ ምክንያት በየቀኑ በልባችን ይወለድ! ክርስቶስ በየቀኑ አይወለድም፡፡ የተወለደበት አላማ እና ምክንያት ግን በየጊዜው ይወለድ! ክርስቶስ ተወልዶልናል! እንኳ ደስ ያለን!! 

1 ነገር ግን ተጨንቃ ለነበረች ጨለማ አይሆንም። በመጀመሪያው ዘመን የዛብሎንንና የንፍታሌምን ምድር አቃለለ በኋለኛው ዘመን ግን በዮርዳኖስ ማዶ በባሕር መንገድ ያለውን የአሕዛብን ገሊላ ያከብራል።
2
በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃን አየ በሞት ጥላ አገርም ለኖሩ ብርሃን ወጣላቸው።
3
ሕዝብን አብዝተሃል፥ ደስታንም ጨምረህላቸዋል በመከር ደስ እንደሚላቸው፥ ሰዎችም ምርኮን ሲካፈሉ ደስ እንደሚላቸው በፊትህ ደስ ይላቸዋል።
4
በምድያም ጊዜ እንደ ሆነ የሸክሙን ቀንበር የጫንቃውንም በትር የአስጨናቂውንም ዘንግ ሰብረሃል።
5
የሚረግጡ የሰልፈኞች ጫማ ሁሉ፥ በደምም የተለወሰ ልብስ ለቃጠሎ ይሆናል፥ እንደ እሳት ማቃጠያም ሆኖ ይቃጠላል።
6
ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።
7
ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ በዳዊት ዙፋንና በመንግሥቱ ላይ አለቅነቱ ይበዛል፥ ለሰላሙም ፍፃሜ የለውም። የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል። ኢሳ 9

No comments: