“አገር አለኝ ማለት?”
አገር አለኝ ብዬ- ሳነብ ስ’ላገሬ
ታሪክ አለኝ ብዬ- ስጠይቅ በወሬ
ስሟ ብቻ ገኖ ተዘርቶ በጥሬ
እኔም ጥሬ
ግሬ - ምን አገኘኹ ጭሬ?
“ይህ” ጥሬ “ያ!-ም” ጥሬ
ሁሉም ጥራጥሬ!!
ዘመናት አለፉ አዲስ አመት ጠባ
ቀን ባተ ቀን ባተ- መሪዎች ተተኩ ተቀየረም ካባ
አልጋውን ወረሱት ወንበሩም ተዛባ!
ታሪክ አይሻሻል -ጊዜ አይለወጥ -በለስ የለው ፍሬ…
ሁሉ ጥሬ!
ወይ ሞቶ አይበቅል ተዘርቶ ለፍሬ
ከቶም አይነሳ “በትንሳኤ” ዛሬ
ወይም አይታኘክ “ደም” አይሆን ለዘሬ!
አይ አገሬ!
ለኢትዮጵያ ትንሳኤን ናፋቂዎች፡፡
ከተስፋ
በላይነህ
No comments:
Post a Comment