“የተራራ ግዛት!”
ያን ትልቅ ተራራ
አገር የሚያስጠራ
ህዝብን የሚያኮራ
ተብሎ ቢሆን ጋራ
የፍቅር የሰላም የመንግስት አደራ
ያ ተራራ!
ቢሆን አድባር ደብር
የአገር አለኝታ የኩራት የክብር!
ያንድነት የሰላም ለአለሙም ፍቅር…
አልገፋም አለ ተራራ ነኝ ብሎ
ልቡን የተራራ ያክል በግፍ ሰቅሎ
የህዝብን አንድነት ስሜት ወኔን ገሎ
እምነታችን ጠፍቶ ባህር ዘንድ ተጥሎ
ተራራው ብቻውን ወገነ ገነነ
አደገም ጀገነ……
ተራራው ተስፋፋ
ገፊ ሰውም ጠፋ
አልገፋም አለ
መብዛቱን መግዛቱን መጠንቀር ቀጠለ!
ህዝቡም በስንፍና
ወኔውም ጠፋና
ሀሞቱም ፈሰሰ አይገፋምና
ተደግፈን እንሙት ብለው መረጡና
ተራራውን ናዱት ገባ ወደ ጣና
ተራራውን ናዱት ገባ ወደ ጣና
ለመግፋት የጣሩት በግፍ ተሰቃይተው ከላይ ተጣሉና
በ“ደጋፊ” ብዛት በድካም ሲጸና
ወትሮም “ደጋፊዎች” አልነበሩምና
ተራራው ተናደ ይናደልም ገና!
ደግፈው የጣሉት ታጋይ ሆኑ ጀግና
ገፍተው የተጣሉት በስር ቤት ፈተና
ያገር ጠላት ሆኑ ለደጋፊ ዝና
ታሪካቸው መና
“ደጋፊዎች” ጸኑ
ሊክቡ ሊያቆሙ “ተ.ራ.ራ” እንደገና !”
ምንጭ፡- “አልገፋም ያለን ተራራ
ከምትታገል ተደገፈው” ለሚል “ዘመነኛ” አባባል የተገጠመ፡፡
No comments:
Post a Comment