Oct 31, 2013

ስህተት ከውድቀት አያድንም፡፡ ካልተማርንበት!


  በመንግስታቶቻችን የተፈጸሙ ስህተቶች ብዙ ናቸው! ኢትዮጵያ ውስጥ መንግስት ማለት ትርጉሙን ቀይሮ “ስርዓት” ሳይሆን የግለሰቦች ወይም የቡድኖች ስብስብ ነው፡፡ ስለዚህ ሰው ስለሚሳሳት መንግስትም ይሳሳታል፡፡ አጼ ቴዎድሮስ ከእንግሊዝ ጋር የገባው ውዝግብ፣ ከሰሜን/ በዝብዝ ካሳ/፣ ከላስታ/ዋግሹም ጎበዜ/ እና ከሌሎች መኳንንቶች ጋር የነበረው ሽኩቻ ለውድቀቱ መንስኤ ነው ይባላል፡፡ ስህተቱም ለውድቀቱ ምክንያት ነው ይሉናል፡፡  ስህተቱ የተሰራው ለምንድን ነው? አንድም ለስልጣን ወይንም ለኢትዮጵያ አንድነት! አንድነቱ የአንበሳውን ድርሻ ይወስድብኛል፡፡
   አጼ ዮሐንስስ? አጼ ዮሀንስ ስህተታቸው ምንድን ነው? ከእንግሊዝ ጋር የመሰረቱት ቁርኝት? የሚኒልክ ከጣልያን ጋር ያደረጉት ውስጣዊ ግንኙነት፣ የጎንደርን መጥፋት ሰምተው ወደ መተማ መዝመታቸው? ስህተታቸው ምኑ ላይ ነው? ስህተቱስ የተሰራው ለምንድነው? ለአገር፣ ለድንበር፣ ለሃይመኖት ወይንስ ለግል ክብር? አገር ትርጉም አላት!
  ሚኒልክ “በመረብ ምላሽ” እና በጅቡቲ ላይ የወሰደው እርምጃ ስህተት ነው ይሉናል፡፡ ለልማት እና ለሰላም ተብሎ የሚወሰደውን አማራጭ ያሁኖችም “ነገስታት” ሲስማሙበት አይተናል!
ስህተት ይሰ’ራል፡፡ አይሰራም አይባል:: በርካታ ስህተቶች ተሰርተዋል፡፡ ዋናው ቁም ነገሩ ከስህተት ምን ተማርን? የሚለው ነው፡፡
  አጼ ሐይለ ሥላሴ ስልጣናቸውን ለልጅ እና ለተማረው ክፍል ቢያስማሙት ህዝቡን ቢያረጋጉት እና ጥያቄዎች መለስ ቢያገኙ የኢትዮጵያ ጥንታዊው የዘውድ ስርዓት እንደዛ አወዳደቁ የከፋ ይሆን ነበር?
  ደርግ ስልጣን ሲይዝ ያለፈውን ስርዓት ለማጥፋት ብቻ ይመስል ሁሉንም በዘመነኛው “አብዮት” ስያወናብደው እና የውይይት መድረኮችን የጦር ሜዳ ባያስመስላቸው፤ የሰሜኑን ችግርም በሰላማዊ መፍትኄዎች ቢፈተሹ፤ ያን የመሰለ ጦር ይወድቅ ነበር? የታሪክ ትልቁ ጥቅም ከስህተት የሚማር ትውልድን ለመፍጠር እና ከትላንት የተሻለ ለመሆን ነው፡፡
  ጠ/ሚ መለስ ስለስህተት እንዲህ አሉ መላዕክቶች ብቻ ናቸው ስሕተት አንሰራም የሚሉት፤ ባለፉት ዓመታት ብዙ የተሰሩ ስሕተቶች ስለመኖራቸው እርግጠኛ ነኝ፤ የሰራኋቸው ስሕተቶች ቢኖሩም እነዚህ ስህተቶች የተፈጸሙት በመልካም ፈቀድ እጦት ምክንያት ሳይሆን በችሎታ ማጣት ሊሆን ይችላል፡፡

ሪፖርተር - ከአልጄዚራ ቴሌቪዥን `ዴቪድ ፍሮስት` ዝግጅት ላይ፡፡ አገቱኒ ገጽ 142፡፡
ታዲያ መሪዎቻችን የማያውቁትን እና የማይነዘቡትን፤ ስህተት እንዳይሰራ ይወያዩ፣ ይመካከሩ ነበር? እውቀት ከስህተት እንድንማር እና እንድንቆጠብ ይረዳናል!
እንወያይ፣ እንማማር፣ ከስህተት እንማር ከውድቀት እንጠበቅ! በአሁኑ መንግስት ስንት አይነት ስህተቶች ተፈጽመዋል…?
በኔ ትውልድ ያየሑት ስህተት ብዙ ነው! እንደዚህኛው የከነከነኝ እና እንቅልፍ የነሳኝ ግን የለም!
When the PM was dead, this picture was posted more than a week

The Ethiopian Muslims has been/ is asking peacefully, God knows the end

ስህተት ከውድቀት አያድንም፡፡ ካልፈተሸነው! ካልተማርንበት!

No comments: