Oct 29, 2013

አለማወቅ ምንድነው? ሃጥያትስ-የተሸፋፈነው እውነት?



 

እኔ ደግሞ ከክርስቶስ አስተምህሮቶች የሚገርመኝ አለ ይሔውም መንገስተ ሰማያት ለእንደነዚህ ላሉ ህጻናት ናት የሚለው፡፡ አስባችሁታል? ህጻናት እኮ ነው ያለው፡፡ ህጻናት ምን ያውቃሉ እና ነው? ዳግመኛ መወለድ የሚለውም ከዚህ ጋር የተያዘ ሆኖ ሌላ ትርጉምም እንዳለው ይነገራል፡፡ ነገር ግን ምንም አለማወቅ ደግሞ መንግስተ ሰማያት ያስገባል፡፡ ካወቅህ ግን ትሳሳታለህ- አለማወቅ ደግሞ ጽድቅ? ነገር ግን ደግሞ The ignorance off law is no excuse ይሉናል፡፡ ignorance is bliss?
  በኔ በኩል ወደ አንድ ድምዳሜ አድርሶኛል፡፡ ማወቅህ ማጠራጠር የለበትም፣ ማወቅህ ማሳሳት የለበትም፣ ማወቅህ ማዘናጋት የለበትም፣ ማወቅህ ወደ ጽድቅ ሊወስድህ ይገባል-
  እንደ እባብ ልባሞች፣ እንደ እርግብ የዋህ  ሁኑ ለምን ተባለ? ስለዚህ ህጻናት ስንሆን የንጹህ ልቦና ባለቤት፣ ማወቃችን በምንም አለማወቅ ያልተበረዘ/ ያልቋቋሸሸ/ ንጹህ የሆነ ማወቅ መሆን አለበት፡፡
  ገነት የት መሆኗን ሳናውቅ ልንገባባት አንችልም! መንፈስ ምን እንደሚነግረን ሳናውቅ ገነትን ልናይ አንችልም! እግዚአብሔርን ሳናውቅ መጽደቅ አንችልም፣ እርስ በርሳችን መዋደድን ሳናውቅ ከሃጥያት ውጪ መሆን አንችልም፡፡
  ማወቅን በ “ሀ” እን በ “ለ” ወይም በ A B C D እውቀት እንዳንገምተው- We are not talking about knowledge intermes of gathered information, but the inert wisdom that we born with. እንዳተባለው፡፡ እነዚህ የአለም እውቀቶች ሞኝነቶች ናቸው እንዲል መጽሐፉ! ማወቅ ማለት እግዚአብሔርን ማየት/ በጥበብ/  መሆን ማለት ነው! ማወቅ ማለት የዋህ መሆን፣ በመንፈስ መሆን፣ በፍቅር መኖር ማለት ነው!  የሚያየውን ወንድሙን ሳይወድ የማያየውን እግዚአብሔርን አውቀዋለሁ ቢል ምን ትርጉም አለው? እንዲል መጽሐፉ!
  አለማወቅ ማለት ደግሞ የነዚህ ተቃራኒ መሆን ማለት ነው፡፡ አመጸኛ መሆን፣ ከእግዚአብሔር ውጭ መሆን፣ ከፍቅር ውጪ መሆን፣ ልክ ወንድሜ ሜልት እንዳልከው በህገ ልቦናችን ያለውን ህግ መተግበር ማለት ነው፡፡ ካልተገበርክ ግን አላወቅክም ማለት አይደለም- ታውቀዋለህ ግን አመጸኛ ነህ ማለት ነው፡፡ ጓደኛዬ ሜልትየሃጥያት ሥረ መሠረቱ አለማወቅ ነው ከማለት ይልቅ ሐጥያት አለማወቅ ሳይሆን አለመታዘዝ ማለት ነው ቢባል ይቀላል፡፡ አንድ ሰው ይመኛል፣ ይሳሳታል፣ ሐጥያት ይሰራል፣ ይሞታል! አየህ አንድ ሰው ሳያውቅ እንዴት ይመኛል? ስለዚህ ማወቅም ሐጥያት የሚሆንበት ጊዜ አለ! ሐጥያት ማለት አመጸኛነት፣ አመጻ ደግሞ አለመታዘዝ ደግሞ ሐጥያት፡፡ አዳም እና ሔዋን ሳያውቁ ቀርተው ነው ሐጥያት የሰሩት? ግጥም አድርገው ነው እንጂ የሚያውቁት፡፡ ነገር ግን ያወቁትን አልታዘዙም/ አልተገበሩም/፡፡
ግን ተፈጥር ስለእግዚአብሔር ልታሳውቀን ሌት ተቀን ትሯሯጣለች፡፡ በጠዋት ጸሐይ፣ በማታ ጨረቃ፣ በሌሊት ከዋከብት እና በእልፍ አዕላፍት ድንቃድንቆች ተሞሽራለች፡፡ አሁንም በሰፊው ህግ ሊሰበክ ሰዓቱ ነው! እንዲህ እንዲፈጸም ትንቢቱ!
ትንቢተ ኤርሚያስ እና እብራዊያን 8 ላይ እንዲህ ይላል

ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፥ እኔም አምላክ እሆንላቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑልኛል። 
11  
እያንዳንዱም  ጐረቤቱን እያንዳንዱም ወንድሙን። ጌታን እወቅ ብሎ አያስተምርም ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና። 
12
ዓመፃቸውን እምራቸዋለሁና፥ ኃጢአታቸውንም ደግሜ አላስብም። 



  አይህ እግዚአብሔርን ማወቅ ማለት ነው ጽድቅ፣ ህግን በልቡና መያዝ ነው ድድቅ፣ ጽድቅ ማለት እውነት ማለት ነው፡፡ እውነት ማለት እግዚአሔር ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ፍቅር!

No comments: