ኢትዮጵያ ወስጥ የነበሩ መኳንንቶች እና ነገስታት የየራሳቸው ፈረስ እና የፈረስ ስም ነበራቸው፡፡ አንዳንዴማ ስማቸው ይመስለን ዘንድ አብረን እንጠራቸዋልን፡፡ ለምሳሌ ባልቻ አባ ነፍሶ /ባልቻ ሳፎ/፣ አሉላ አባ ነጋ /አሉላ እንግዳ/ ፣ አባ ታጠቅ/፣ አባ በዝብዝ እያልን…
አንዳንድ ነገስታት እና የፈረስ ስሞቻቸውን እንመልከት፡፡
ዐጼ ትዎድሮስ- አባ ታጠቅ
ዐጼ ዮሐንስ- አባ በዝብዝ
ዐጸ ሚኒልክ- አባ ዳኜው
ዐጼ ሃይለ ሥላሴ- አባ ጠቅል
ማህተመ ስላሴ ወልደ መስቀል የፈረስ ስም አሰጣጥን ከባለፈረሱ የግል ስብዕና ማለትም ካለው የአስተዳደር እና የፍትህ አሰጣጥ፣ የጀግንነት፣ የሩሩህነት፣
የታጋሽነት እና በፈረሱ ቀለም በመንተራስ ሊሠጥ እንደሚችል አስገንዝበውናል፡፡
በተክለ ጻድቅ መኩርያ አጼ ሚኒሊክ እና
የኢትዮጵያ አንድነት መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሱ አንዳንድ
የፈረስ ስሞችም አሉ፡፡
ለምሳሌ ያክል፡ ራስ ዳርጌ ሳሕለ ሥላሴ
የፈረስ ስማቸው- አባ ግርሻ
ራስ ጎበና ዳጬ
የፈረስ ስም- አባ ጥጉ
ደጃዝማች ናደው
የፈረስ ስማቸው- አባ ባሕር
ደጃዝማች ወልደ ሚካኤል ጉዲሳ
የፈረስ ስም- አባ ጉራች
ደጅዝማች ገርማሜ
የፈረስ ስም- አባ መላ/አንዳኔዴ ለፊታ ሀብተጊዮርጊስ ሲሰጥ እሰማለሁ/
ደጃዝማች ወልደ ገብርኤል
የፈረስ ስም- አባ ሰይጣን
ራስ መሌ ብጡል
የፈረስ ስም- አባ ጠጣው
ንጉስ ወልደ ጊዮርጊስ አቦዬ
የፈረስ ስም- አባ ሰጉድ
ራስ ቢቶድድ ተሰማ ናደው
የፈረስ ስም አባ ቀማው
አዛዥ ወልደ ጽድቅ
የፈረስ ስም አባ መንዝር
ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ
የፈረስ ስም- አባ መቻል
እያለ ይቀጥላል፡፡
አባ
ዴንሳ፣ አባ ጅፋር፣ አባ ጋሪ.፣ አባ ፌቶን፣ አባ ጉርጋ፣ አባ ዳገት፣ አባ ዳምጠው፣አባ ሻውል፣ አባ መንሱር፣ አባ ቦቃ… በጣም
የሚገርመው በሰሜን፣ በደቡብ እና በመሀል ኢትዮጵያ መሪዎች የሚጠቀሙት የፈረስ ስም “አባ” መባሉ ነው፡፡
“ቃኘው” የተባለው ፈረስም አልነበር በአድዋ ጦርነት ጣልያኖችን ቁም ስቅል ያሳያቸው?
ኢትዮጵያዊነት እንዲህ ነው!
ለንባብ፡-
ተክለጻድቅ መኩርያ፡ አጼ ሚኒልክ እና የኢትዮጵየ አንድነት
ማሕተመ ስላሴ ወልደ መስቀል፡ ዝክረ ነገር
No comments:
Post a Comment