May 12, 2013

Lucy’s Legacy: The Hidden Treasures of Ethiopia,



ኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ሉሲ ምንህ ነች?
Lucy’s Legacy: The Hidden Treasures of Ethiopia,
እውን ሉሲ የሰው ዘር መነሻ ናትን?
ተስፋ በላይነህ
የዛሬ ፴፱ ዓመት ገደማ በወርሃ ህዳር የኢትዮጲያ የ፲፱፻፷፮ቱ አብዮት በተበሰረ ወቅት ፤ አብዮቱም ኢትዮጵያለሺዘመናት አይታውና ሰምታው የማታውቀውን እንግዳ አገዛዝ ተሳሰረች። ወቅቱ ለዘመናት ፈጠሪን ሲማጸንና ሲለምን ለነበረ ህዝብ «የዲያቢሎስ ቁራጭ ገዥ» ብሎ ቢያስብም አያስኮንነም። የ፫ሺ ዘመን ባለታሪክ እና በስዩመ እግዚአብሔር የዘውድ አገዛዝ ስርዓት በወታደራዊ ማህበረሰባዊና ሃይማኖትን እንደ ሸቀጥ የሚቆጥር ስርዓት፤ ዳቦን እንደ መሰረታዊ የህይወት ህልውና የቆጠረ ስርዓት ብቅ ሲል ይህች አገር ወደ ህመሙ ዓለም ተላከች። ህመሟም ብዙ ዋጋ አስከፈለ። ልጆቿ ከምንጊዜውም በተለየ ስደትንና ባርነትን ተጋፈጡ። ታዲህ በዚህ ሰርዓት መባቻ ከወደ አፋር ስዩ ሰሙ ሃዳር አንድ አስደናቂ ዜና ተሰማ። አለማዊያን ተመራማሪዎች፣ የቅሪተ አካል አጥኝዎች፣ ምዕራባዊያን የዝግመተ ለውጥ ተሟጋቾች ለሚፈልጉት እልቆቢስ የህይወት አጀማመር ኑፋቄ ለአለም ህዝብ የሚያበስሩት የምሰስራች ተሰማ። በዶናልድ ጆሃንሰን መሪነት ከ፩ መቶ በላይ የሚቆጠሩ ፍርስራሽ አጥንቶች፤ ፵ በመቶ /40%/ የሚወክል የሰውነት ክፍል፤  የሰውዘርን የዝግመተ ለውጥ አመጣጥ ሂደቱን መገናኛና ለባለሁለት ዘመናዊው የሰው ልጅ መነሻ ሽግግር/ missing link/ ሆን ዘንድ በቁመት ፩ሜትር ከ፩ ሴ ሜ በጾታ ሴት በቅሪተ አካል መጠሪያ AL 288-1 በተሰኘ ስያሜ ኢትዮጵያ «የሰው ዘር መገኛ» እንድትባል አደረገ። የተለምዶ ስሟንም Lucy/ሉሲ/ ሲሏት በአገርኛ ድንቅነሽ ተብላለች።
 ይህ ስድሳ ስድስት ዓ/ም ሁለት ተቀራራቢ የታሪክ ክስተቶችን አስረከበን። በፈጣሪ የማያምንን መንግስትና ለህዝብ፤ በፈጣሪ ለሚያምን ህዝብ ሰው ከጦጣ መሰል ዝርያ መጣ በሚል ኢትዮጵያን ወደ ሶስት ሺ ሳይኾን ወደ ሶስት ሚልዮን ሁለት መቶ ሺ ዓመት ባለታሪክ አደረጋት። በፈጣሪ ለሚያምን ህዝብ ሚልዮን ምኑ ነው? ፈጣሪ እንደሆን በፊቱ አንድ ቀን እንደ ሺ ዓመት፤ ሺ ዓመትም እንደ አንድ ቀን ነች። ዋናው ግን የ፯ሺ ዘመንን የአዳም ታሪክ በሃይል አሽቀንጥሮ ገደል የቀበረ ነው። ሉሲ ያላት የራስቅል፣ የጥርስ፣ አንገት እና የአገጭ አቀማመጧ ወደ ጎሬላ ዝርያ እንጂ ወደ ሰው የማይቀላቅሉት ተመራማሪዎችም እንዳሉ መዘንጋት የለብንም። የእጅና እግር ጣት አቀማመጥ ለዛፍ መንጠላጠያነት የሚመች እንደሆነና በዛፍ ላይ ትኖር እንደነበር ኢንዲሁም አትክልት በል ኢንደነበረች የጠቆሙ ተመራማሪዎችም አልጠፉም። የጦጣ መሰል ዝርያዎች ቅርርብ የያዘች ነገር ግን ለየት ያለ ዘርያና ከጠፉ የጦጣ ዝርያዎች ውስጥ የምትመደብ መሆኗም አብሮ የሚነገር ነው።የሴትነት ጾታዋንም የማይስማሙበት አሉ።

ከዚህ ሁሉ ታሪክ ጀርባ የሚስበኝ ግን አንድ ተራ ሊባል የሚችል ሃሳብ አለ። የእንግሊዝ ፈርጦቹ ዘ ቢትልስ እኤአ በ፲፱፻፷፯ ዓ/ም ባወጡት  "Lucy in the Sky with Diamonds እና በዶናሌድ ጆሃንሰን የታተመው Lucy: the Beginnings of Humankind (1981)/ሉሲ የሰው ልጅ መጀመሪያ/ የተባለው መጽሐፍን በይበልጥ እታዘባቸዋለሁ። ሁልጊዜም በቀጥታ የሚነገረኝን መረጃ ከተለያዬ ማዕዘን መመልከትን እመርጣለሁ። ይህ ቢኾንስ ብሎ ማሰብ ሰብዓዊ ነትም ነው። ሁሌጊዜ በአንድ መንገድ ወደፊት የሚባል «ፈረስ» እንደሆነ አያለሁ። ከጀርባ ያለውን ሃሳብ ለመረዳት የምጀምረው ሉሲ የሚለውን ሴያሜ በማንሳት ነው። መላምቴን እንደ ሃሳብ ይወሰድልኝ። ሉሲ/Lucy / የሚለው ስያሜ ተደራራቢና ተቀራራቢ ባዕድ ሃሳቦች ሊያስከትል እንደሚችል እንገንዘብና ወደ ዋናው የጽሑፌ ማጠናከሪያ ሃሳብ የማመራው the Beatles'  "Lucy in the Sky with Diamonds የሚለውን ሙዚቃ በማየት ይኾናል።
  የአገረ እንግሊዝ ዝነኞቹ ዘቢትልስ የሮክ ዘፈን ቡድን  በSgt. Pepper's Lonely Hearts Club Band የሙዚቃ እትም እኤአ ፲፱፻፷፯ /1967/ዓ/ም ሲወጣ "Lucy in the Sky with Diamonds የሚለው ሙዚቃ በእትሙ ተካትቶ ነበር። ቢቢሲ ሬድዮ ከልክሎት እንደነበርም የቀረበ መረጃ አለ። ለምን ከለከለው ብንልም የስልሳዎቹ ፈርጦች በብዛት ከሚታወቁበትና ከሚታሙበት የባዕድ አምልኮና የአደገኛ ዕጽ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ነበር። በተለይ "Lucy in the Sky with Diamonds የሚለውን ሃረግ የመጀሪያ ሆሄያት ብንወስድ LSD የሚል እናገኛለን። ይህ ደግሞ Lysergic acid diethylamide የተባለ በተለምዶ አጠራሩ Acid /አሲድ/እየተባለ የሚጠሩትን አደገኛ እጽ ይወክላል በማለት ነበር።  የቡድን አባሉና ሙዚቃውን እንደጻፈው የሚነገርለት ጆን ሌነን ግን የአራት አመት ልጁ ባሳየው አስገራሚ ስዕል ተመልክቶ እንደጻፈው ገልጿል። በህጻንነቱ የነOscar Wilde የ Dylan Thomas አሊያም የዜነኛውን ሆላንዳዊ Vincent van Gogh የሚገለጽ መጽሐፍት ነበር የሚያነበው። እነዚህ ሰዎቸ በህይወታቸው ለየት ያለ ርዕይ በማየታቸው በህብረተሰቡ ዘንድ የነበራቸውን ቦታ እና መገለል ሲያስበው ራሱን በብቸኛ አለም ውስጥ እንዲሰውር መንገድ ከፋች ነበር ለጆን ሌነን።
Alice in Wonderland የተባለ ታዋቂ ስራ ላይ በተገኘ ሃሳብ የተወሰደ እንደሆንም ከጥቂት ዓመታት በኋላ ሲነገር ተሰምቷል። አሊስ ኢን ወንደርላንድ እኤአ 1865 የተጻፈ መጽሐፍ  ሲኾን በተከታታይ ፊልሞች ለዕይታ የቀረበ ምናባዊ አለም ነው። ሆኖም ዘፈኑ ከምንም አይነት አሲድ/እጽ/ ጋር እንደማይገናኝና በተለይ በልጁ በጁልያን አማክኝነት የተሳለው ስዕል ሃሳቡን እንዳመጣለት ሉሲ ማለትም የልጁ የክፍል ጓደኛ እንደሆነችና በሰማይ ላይ ከከዋክብት ጋር ተቀምጣ ያያትን ሃሳብ የሚደገፍ የወረቀት ስራ ነበር። ጆን ሌነንም የሚለው ይህች ምናባዊ ሴት ከሰማይ መጥታ እንደምታድነኝ አስብ ነበር እሷም ዮኮ ኦኖ/የጆን ሌነን/ ሚስት የሆነችውን ነው። የዘፈኑን ግጥም እንመልከት። ከተቻለ የምስሉን ይዘት ዘፈኑን «ዩ ቲዩብ» ይመልከቱ።
Picture yourself in a boat on a river
With tangerine trees and marmalade skies
Somebody calls you, you answer quite slowly
A girl with kaleidoscope eyes
Cellophane flowers of yellow and green
Towering over your head
Look for the girl with the sun in her eyes
And she's gone
Lucy in the sky with diamonds
Aaaaahhhhh...
Follow her down to a bridge by a fountain
Where rocking horse people eat marshmellow pies
Everyone smiles as you drift past the flowers
That grow so incredibly high
Newpaper taxis appear on the shore
Waiting to take you away
Climb in the back with your head in the clouds
And you're gone
Lucy in the sky with diamonds
Aaaaahhhhh...
Picture yourself on a train in a station
With plasticine porters with looking glass ties
Suddenly someone is there at the turnstyle
The girl with the kaleidoscope eyes
Aaaaahhhhh...
Lucy in the sky with diamond  [fade out]
በዚህ ሙዚቃ እትም/ Album/ ፊት ለፊት የቀረቡት የተለያዩ ዝነኛ ተብለው የቀረብ በርካታ ሰዎችን ምስል ይዞ እናገኛለን። ታዋቂዋ ማርሊን መኑር/Marliyn Monoroe/ Aliester Crowley, albert Einstein, carl jung, W.C Fields, Oscar wilde, Fred Astair, laurel/Hardy, Tommy handley, Diana dors, karl marx, እና ሌሎችንም ከሰማንያ በላይ ሰዎች ጋር በጋራ የተሰበሰቡበትን ምስል እናገኛለን። የሂትለርንና የክርስቶስን ምስል ለማስገባት እንደፈለጉና ሊደርስ የሚችለውን ጫና ስለተረዱት ሳያወጡት ቀርተዋል። የጋንዲ ምስልም በህንድ ያለውን ተቀባይነት ስለሚታወቅ ሳይወጣ ቀርቷል።  በተለይ ኤሊስተር ክራውሊ በይበልጥ የሚታወቀው በአስማት፣ በእጽ አጠቃቀም፣ ልቅ በሆነ የወሲብ ጥማት እና ለባዕድ አምልኮ ከፍተኛ ዝንባሌ የነበረው ሰው ነው። አልበርት አንስታይን ከሳይንሱ ዘርፍ ካርል ማርክስ ከፖለቲከኞች፣ የፊልም ተዋናንያን፣ አስቂኝ ተዋንያን/ኮሜዲያን/ የህንድ ጉሩ፣ ጸሐፊያን፣ የስነልቦና ባለሙያዎች የተካተቱበት ስብስብ ነበር ሰርጀንት ፔፐርስ። 
   
ከዚህ እትም ሙዚቃ ነው ለቅረተ አካል መጠሪያ ሆኖ የሚያገለግለው «ሉሲ» የተገኘችው። በቅሪተ አካሉ ፍለጋ ወቅት በመጠለያ ስፍራው በተደጋጋሚ ይሰማ እንደነር ተጠቁሟል። ይህን ኹሉ ስለ ዘፈናቸው የሚያወራ ሃተታ ያበዛኹት ሁልጊዜም ፈጣሪ የለም ተብሎ የሚደገፍ መልዕክት በእነዚህና መሰል ታዋቂ የአለማችን ፈርጦች በስልትና በሚስጥር ስለሚተላለፍ ፤ ይህንንም የያዙት እና ‹‹ከኛዋ ሉሲ›› ጋር ስለሚተሳሰር፤ የሰው ልጅ የተገኛው ከፈጣሪ /ሃይማኖቱ በሚነገረን/ ሃሳብ ጋር ስለሚዋደደው ሁለቱም ስለሚስማሙ/ ዘፋኞቹም ኾነ በዝግመተ ለውጥ ለሚያምኑት/ ሉሲ ዋነኛ መሳሪያቸው ኾና ተገኘች፡፡
በቅርቡ የሆሊውድ ፈርጧ ሪሃና «ሻይን ላይክ ዲያመንድ» የሚለው ዘፈኗ ተወዳጅ ሆኖላታል። «እንደ አልማዝ እናብራ» የሚለው ይህ ዘፈን ሙሉ በሙሉ ዲያመንድ/ አልማዝ/ ተብሎ የቀረበው አደንዛዥ እጽ እንደኾነ ከዘፈኑና ለዘፈኑ ከቀረበው ምስል/ video clip/ መመልከት እንችላለን።
የቅሪተ አካሉ ግኝት አርባ በመቶ ሲገኝ ሙሉውን አካል በፈረንሳይ ዋናው ጋር በማመሳሰል የተሰራ ነው። ጉልበቷም የተገኘው የመጀመሪያው ቅሪተ አካል በተገኘ ዘግየት ብሎና ከቦታውም ርቆ ነው። የሉሲ መኾኑንን የተረጋገጠው ሰውነት ክፍል መመሳሰል / anatomical similarities/ እንደሆነ ተገልጿል። እንደ ስነ-ህይወት ተመራማሪዎችየሚሴማሙት ግን ውሻና ድብ እንኳ ተመሳሳይ የኾነ የአካል ክፍል መመሳሰል /Anatomical similarities /እንዳላቸው ነው።
እንደ እኔ መላምት ደግሞ ሉሲ የሚለው ስም ሉሲፈር የሚለውን ስያሜ የሚወክል ሊኾን እንደሚችል አስባለሁ። ሉሲፈር ሰይጣንን ወይንም ዲያቢሎስን አክብረው ሲጠሩትና የብርሃን አመንጪ እያሉ የሚያምኑት አካላት የሰጡት ስያሜ ነው። የብርሃንም ብቻ ሳይኾን የህይወት መጀመሪያ አድርገው ይቀበሉታል /የመጀመሪያው የመፈንቅለ መንግስት አለቃ እንዲሉ/። ልብ በሉ የህይወት መጀመሪያ ነው የሚለው። ዶናልድ ጆሃንሰንም ያለ ምክንያት አይመስለኝም «ሉሲ፡ ዘ ቢግኒንግ ኦፍ ሂዉመንካይንድ»በማለት እኤአ በሺ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ አንድ መጽሐፍ ያሳተመው። ዘ ቢትልስ የዲያቢሎስ ተከታይ መኾናቸውን አልጠራጠርም። ይህንን ለማረጋገጥ ይከተሉት የነበረውን እምነት፣ ስራ፣ ንግግር፣ ዘፈኖችና የምንጊዜም ተወዳጅ ሰዎች ብለው ያቀረቧቸውን ሰዎች ማንነት መመልከት በቂ ነው። ይህ በራሱ ሌላ ሀተታና ማስረጃ የሚያስፈልገው ጉዳይ በመኾኑ በሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ።
  ዋናው ቁምነገሩ ሰዎችን ለማጣጣል፤ የዚህእምነት ተከታይ የዛ እምነት ተከታይ ነበር ብሎ ለማውራት አይደለም። ይህ የሰው ልጅ የግል ፍላጎቱና ነጻ ፈቃዱ ነውና። ነገረ ግን እንደ አንድ ኢትዮጵያዊና እንደ ክርስትና ሃይማኖት ተከታይነቴ የሰው ልጅ የመጣው ከጦጣ መሰል ፍጡር ነው ተብሎ ለሚነገር መላምትና የዚህም መላምት ሳይንሳዊ ግኝት በዚህች አገር ተገኘ ተብሎ ከመመዝገብ ባሻገር የሶስት ነጥብ ሁለት ሚልዮን እድሜ ባለቤት ስንኾን እንደ ማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር ጥያቄ ስለሚያጭርብኝ ነው። አዳምና ሄዋን ከተፈጠሩ እንኳ ፰ሺ ዓመታትን ሳያስቆጥሩ የሰው ልጅ በሚልዮን አመት እድሜ ባለቤት ነው ተብሎ ሲነገረን በምን አግባብ እንደምናስማማው ለማንኛውም ሰው የሚከብድ ነው። ኢትዮጵያስ «የመቶ አመት ባለታሪክ» አገር ስትባል እየሰማን ሚልየን እድሜ ስታስቆጥርልን ወደየት እንውሰደው? «አይ ሰው መኾን አለች»።አንድ ተወዳጅ ሰባኪን አግኝተን ይህንን ጥያቄ አቀረብንለት። “በሉሲ እንመን ወይንስ በሄዋን?” ፈገግ እያለ “ት/ቤት ውስጥ ስትጠየቁ ሉሲ በሉ ቤተክርስትያን ስትመጡ ደግሞ ሄዋን በሉ” ብሎ እኛንም አሳቀን። ሁለት የማይገናኙ ነገሮች። እኛ ህይወትን የምንፈልገው ከሰማይ እነርሱ ህይወትን የሚፈልጉት ከምድር በቁፋሮ። እነርሱ ህይወት መጣ ብለው የሚያምኑት በዝግመተ ለውጥ እኛ ህይወት መጣ ብለን የምናምነው በእስትንፋስ በአርአያ በአምሳያ… ልዩነታችን የሰማይና የምድር ነው።
  ሆኖም ሉሲ/ ድንቅ ነሽ «የሰው ዘር ቀደምት የሰው ዘር መነሻ » ኢትዮጵያ «የሰው ዘር መገኛ» እየተባለ ሲነገረን ከጀርባ ያለውን አንድምታ እንቀብረዋለን። ሉሲ ተቆፍራ ስትወጣና ስትነግስ እውነት ግን በቦታው ተቀበረች። የኢትዮጵያ ህዘብ ሆይ ሉሲ ምንህ ነች? ተብሎ ቢጠየቅ እናታችን ሊል ይችል ይኾናል። “ከጦጣ መሰል ዝርያ ነው የመጣኸው” ሲባል ግን የሚበረግግ ህዝብ ብዙ ነው። ስለዚህ በየትኛው እንመን?
እንደ አንዳንድ ሰዎች ዘገባ ደግሞ ሉሲ/ድንቅ  ነሽ/ ኢትዮጵያን እንደ ገነት አድርገው በመውሰድ የመጀመሪያው ፍጥረት በኢትዮጵያ ነበር ብለው ይጠቁማሉ። አሃ ሄዋን ዛፍ ላይ ትንጠላጠል ነበርና ሉሲም በዛፍ ላይ ትኖር ስለነበር ገነት በኢትዮጵያ ምድር ነበረች ተብሎ ይደመደማል። ሉሲ ማነች?
  እንግዲህ በሉሲ ውስጥ ብዙ ጥያቄዎች ሊነሱ እንደሚችሉ መገመት አያዳግትም። በሉሲ ስም በርካታ ገንዘብ ወጥቷል። ሉሲም የዛሬ ስድስት አመት አገሯን ወደ ምድረ አማሪካ ስታቀና እንደ አምባሳደር ነበረች።Lucy’s Legacy: The Hidden Treasures of Ethiopia,/ የሉስ አሻራ፡ የተደበቀው የኢትዮጵያ ሃብት/ በሚል ስያሜ ለአለም ህዝብ ስትታይ ቆይታለች። ገቢም ስታሰባስብ ነበር። በሚለዮን የሚቆጠር ብርም አሰባስባለች። ለሙዚየምና ለሌሎች ቅሪተ አካል ስራዎች እንደሚውልም ተጠቁሟል። የሉሲ አሻራ የኢትዮጵያን አሻራ ይወክላልን? የሉሲ አሻራ የሰው ልጅን አሻራ ያነሳልን? የማይመለስ ጥያቄ።
ቸሩ ቸር ያቆየን!

No comments: