ፍቅር
ከዚህ ቦታ ፈገግ ብሎ ነበር፡፡
/የአለማችን
ረዥሙ የግጥም መድበል/
በተስፋ በላይነህ
የጥበብን
ሃይል የምናውቀው የተደበቀን ምስጢር ወደ ገሃድ ማውጣቱ፤ የተሰወረን አዚም፤ የጠፋን መንገድ በማመላከት መስመር ማስያዝ መቻሉ፤
በጦር በሰይፍ እንኳ የቀረበን ፍርድ ለእውነትና ለእውቀት ወግኖ መገኘቱ ከዛም ለትውልድ ቅርስ ሆኖ መዘከሩ ነው፡፡
ምንም
እንኳ ጥቂት ሃጥአን ብዙዎችን ነፍሳት የማጥፋት ሃይል ቢኖራቸውም፤ ጥቂት ወይንም አንድ እውነት አለምን እንደሚገዛም
አይተናል፡፡ በዚህ እውነት ስር የሚወጡም በርካታ የጥበብ ስራዎች ብዙዎችን የመለወጥ ሃይል ሲኖራቸዋል፡፡
በአሁኑ
ጊዜ ብዙ ነገሮች ጠፍተውብን፤ መድረሻው ርቆብን፤ ማረፊያው በጠጠር ተደግፎ በአሜኬላ ታጥሮ፤ ፍጻሜው ታክቶን የምንንከራተት
ስንቶቻችን ነን? ‹‹አፋልጉን›› በሚል ጩኸት የምናሰማ ብዙዎቻችን መሆናችንን ቤት ይቁጠረው፡፡ በዚህ የጩኸት ዓለም ውስጥ
እውነትንና የጠራ እውቀትን ማግኘት ከባድ በሆነበት ዘመን እውነትና እውቀት የለችም ብሎ እጅን አጣጥፎ መቀመጥ ከሰውነት ተርታ
የሚያስወጣን በመሆኑ መቼም ቢሆን ለእውነት መታገል ይኖርብናል፡፡ ‹‹አፋልጉን!›› እያሉ የመጮኽ ትግል ::
አሜሪካኖች ለየት ያለ የሙዚቃ አቀንቃኝ ብቅ ካለች /ካለ/
በአለማችን አስገራሚዋ/ው የሙዚቃ አቀንቃኝ ብለው መጮኽ ያዘወትራሉ፡፡ ሌላኛውን ዓለም ሳያዩ ፣ ሳይወዳደሩ በአለም አንደኛ!
ማለት ይወዳሉ:: ይህም ትልቁ የንግድ ሴራቸው ነው:: እኔም
በእነርሱ ንግድ አለም ሥርዓት አይደል ያደኩት:: አዎ! በአለም ረዥሙ የግጥም ስንኝ በሚለው ጩኸት ርዕስ ስር የኤፍሬም ስዩምን ‹‹ፍቅር እዚህ በተፈለገ ብሎ ነበር›› የሚለውን የግጥም መደበል በአለም
አንደኛ ረዥሙ የግጥም ስንኝ ለማለት ተገደድኩ፡፡ እውነት ነው በአለም ረዥም ግጥም ስንኝ ማነው ቢባል ማንም ይወራረደኝ ፍቅር
ኢዚህ ቦታ ፈገግ ብሎ ነበር የሚለው ግጥም ነው ኤፍሬም እነርሱ ባይጽፉትም ፤ አነርሱ ባያነቡትም እኔ ግን አንብቤ ፅፌዋለሁ ትችላልህ! ኤፍ፡፡
ኤፍሬም ስዩም “ሶሊያናን” የግጥም ሲዲ በ 1998 ሲያቀርብልን
ለግጥም የስነ ጥበብ ዘርፍ ከፍተኛ ትርጉምና ዋጋ ያስጠበት ዓመት ነበር፡፡ ተፈጥሮ በለገሰችው ስልቅልቅ ጉሮሮ፤ ቅላፄ፣ ዐርምሞና ምሳጤ መሰረት የተለያዩ ሃሳቦችን በያዙ ግጥሞች ወደ ትልቅ ባህር ወደ ሚወሰዱ
ዜማዎች ታጂቦ አስከመኮመን፡፡ ግጥምን ልክ አንደ ሙዚቃ ስራ ወስደን በቤተሰብ መሃል እያዳመጥን የምንወያይበትን መድረክ
ከፈተልን፡፡
ግጥምን በድምፅ በማሰማት እነ ሎሬት ባለ ቅኔ ፀጋዬ ገ/ መድህን ፣ እና አበባው መላኩም ሞክረውልናል ታገልም ሊካተት ይችላል፡፡ ሌሎችም…
መዚ ቃል ( የብርሃን ክንፎች) ለኤፍሬም ቀጣይ ስራው ነበር፡፡ በ
2004 ዓ/ም የለቀቀው ይኸው ስራ አሁንም ጥበብ የጋለ ብረቷን ለኩሳው በ 2005 ዓ/ም ‹‹ፍቅር እዚህ ቦታ ፈገግ ብሎ ነበር››
በሚል ርዕስ ለየት ባለ አቀራረብ በሚስብ ይዞታ በሰማያዊ መደብ ሁለት
ተበአትና እንስት የአዕዋፍ ፍጡራን በፍቅር ማዕድ ተቆላልፈው ተስለው በነጭ ቀለም ዳርቻ ስር ፍቅር እዚህ ቦታ ፈገግ ብሎ ነበር የሚለውን መድበል እንኳችሁ
አለን ኤፍሬም:: የሸፉኑን ሥዕል አልፈን አንድ ገጽ ስናልፍ በጥቁርና ነጭ ቀለም የተጣለ የገጣሚውን
ከደረት በላይ ምስል እናገኛለን፡፡ አንድ ፈላጊ የሚመስል አትኩሮ የሚያይህ ሰው ይመለከትሃል፡፡፡ በመጠኑም
ቢኾን እንደ ግጥም ለማንበብ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ይዘህ ልትቆይ
ትችላለህ፡፡ ትገልጣለህ “ተበረከተ” ለሶልያና የሚል ጽሑፍ ታገኛለህ
በሶልያና ፍቅር እንደተነካ በግልጽ ማየት ችያለሁ::
ፍቅር ደግ ነገር ነው! ከዛም ስትገልጥ ማውጫው ላይ በግጾች አምድ ስር ሀ፣ሐ፣ሠ፣ኀ እና አ በሚሉ ፊደላት ለየት ያሉ ሃሳቦችን እናያለን፡፡ በብዛት የለመድነው
በሮማን ቁጥር ሊኸን ይችላል፡፡ በአሁኑ ወቅት የገጽ ዉጥሮችን በግዕዝ
ቁጥር ማየት አልተለመደም፡፡ ይስማዕክ ወርቁ የቀንድ አውጣ ኑሮ የግጥም መድበል ላይ ገጾች በግዕዝ ቁጥር መፃፋቸውን አድንቄ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ በፊደል ማየቴ ደስ አለኝ፡፡ ነገር ግን ሌሎች የግጥሞች ገጾች
የቀረቡት በህንድ/አረብኛ ቁጥር በ1 2 3 ተጽፈዋል፡፡ በግዕዝቁጥር ቢጻፉ ኖሮ የመድበሉን ውበት በጣም ሊያሳምሩት
እንደሚችሉ አሰብኩ፡፡
ትገልጣለህ የግጥሞቹ ማውጫ ያልቅና ባደ ገጽ ታያለህ፡፡ በጣም የስነ-ጽሁፍ አድናቂ ፍልስፍናም ነካ የሚያደርገህ ኮኾነ ባደ ገፁን ልታነበው ትችል ይኾናል፡፡ ባደ መኾኑን ሳትገነዘብም ታልፍ ይኾናል ይሆናል፡፡
የምስጋናው እፍል
ይከተላል፡፡ ቤተሰቦችንም ለማመስገን ያቀረበውን ምክንያት በጣም ወድጃዋለሁ፡፡‹‹የእናንተን ለእናንተ መናገር ራሴን በራሴ ከማክበር
እኩል ስለሚኾን በልብ ከልብ ለልብ›› ይላል፡፡ ለገፀ ሀ
ደግሞ ከዛው ይህችን መድበል ሕይወት የዘራበትን ሰው ዘሚካኤልን ያመስግነዋል፡፡ እኔም በበኩሌ እጅጉን አመሰግኜዋለሁ፡፡
እንዲህ ሰው በጣፋበት ዘመን ስው ሲገኝ ያሰደንቃል፡፡ “ዘ” ብድራቱን የላይኛው ይከፍልህ፡፡ ከዛም ስንገልጥ በገጽ ሠ ላይ የምናገኘውን
የዚህን መጽሐፍ ትልቁን ክፍል ነው:: ጠማረ አሚን
የሚለውን እናገኛለን፡፡
‹‹ሁላችንም የግላችን የሆነ sound truck አለን ያ sound
track ያለፈ ጊዜያችን የአሁን ማንነታችን ነው፡፡ እያለ ሕይወትን በሙዚቃ እያዋዛ እያመሳሰለ የህይወታችን መሰረት የሆኑትን አሁን ቅድም
ዛሬ ትላንት አምና ካቻምናን ያስቃኘናል:: ያለፈው ሕይወታችን በአሁንና በነገ ማንነታችን ላይ ያለውን ተጽዕኖ ምላሽም
ያስቃኘናል::
አራተኛው አንቀጽ ላይም …ትናንሽ የሸክላ ጭረቶች የሙዚቃውን ጣዕም ይረብሹታል…
ከሙዚቃ ሐዘንተኛ መንፈስ ይልቅ ባለዋቂ ጥፍሮች የተቧጨሩ የሸክላው
ጀርባዎች…ዜማውን ያበላሹታል፡፡ አንድ ወዳጄ ውብ እኔነቱን ብዙ ምርጥ ዜማዎችን በማንነቱ ላይ እንደተሸከመ ራሱን በራሱ ለመስበር
ሲሞክር ሞክሮም ተሰባብሮ ስብርባሪው ተለቅምና ታሸጎ ወደ ዘላለም
ፀጥታ ሲጓዝ ተመልክቼአለሁ፡፡ በዚህም ከታላላቆች መስበር የታናናሾች ጭረት እንዲጎዳ አስተውያለሁ፡፡ የምትለውን አንቀጽ ውበቷ ጎልቶ
ታይቶኛል፡፡ ቀሪውን ጦማረ አሚን /እውነተኛ-የታመነ ደብዳቤ/ ሃሳብና ይዞታ እስከ ገጽ ተ ድረስ ያንብቡ፡፡ ብዙ ይማራሉ፤ ብዙ
ያስባሉ፤ ብሉ ይጠይቃሉ ይመራመራሉ፡፡ምናልባት ፀጥታ የሌለበት ስፍራ
ወይንም ህሊናዎን ሰብሰብ አድርገው ካለነበቡት ምን ለማለት እንደፈተለገ ሊያገኙት ስለማይችሉ በትህትናና በትዕግስት ኢኒዱያነቡት
እመክራለሁ፡፡
ይቀጥላል
በ ኀ ገጽ ደግሞ ‹‹ዋዜማ›› በሚል ርዕስ ስር ከደመና ልትቀዳ ተራራውን
ወጣች የሚል የመዝገቡ ተስማን አድባር ስዕል አስታወስኩት በማለት ህልሙን ይነገራናል …ህልም…ከዛም የዮፍትሄን ስለት ጠቅሶልን ህልሙን ለመፍታት
ሊተረጉምልን ይተርክልናል፡፡
‹‹ቅደመ ታሪክ›› የሚል ግጥም ይጀምራል፡፡ ያንብቡት! የግጥሙም የመጨረሻ
ስንኝ እንዲህ ትላለችበ ግርጌው ላይ በ29 -02 2004 ተጻፈ ይላል፡፡
‹‹ታዲያ በዚህ
አገር የፍቅር ማደሪያው የትኛው ልብ ነው?›› ብሎ በመጠየቅ
በገንዘብና በቪላ ተደልላ ለሄደችበት ሴት የተፃፈ በማስመሰል ረዥሙ የግጥም ወንዝ ይፈሳል፡፡
ገጽ 1 ‹‹ዕለተ ቅዳሜ ፒያሳና ቦሌ›› በቃ ከዚህ ጀምሮ እስከ ገጽ 100 ድረስ አንድ የግጥም ሃሳብ ያነባሉ:: ለዚህ ነው በአለም ረዥሙ የግጥም ስንኝ በማለት በአለም ድንቃድንቅ መዝገቦች ስፍራ የሸለምኩት፡፡ ከአንድ
ታሪክ ከአንድ ቅዳሜ ተነስቶ አዲ አበባን የአዲስ አበባን ሰዎች ወጣቶች ሴቶች ልጆች ኢትዮጵያን የምናይባቸው ግጥሞች ቀርበዋል:: በተለይ ከመጀመሪያው ገጽ የቀረቡት ----የቤት
ልጅ ( ፀጉሯን የምትሰራውን እፎይ ብላ ተቀምጣ ያረፈቸውን የፒያሳ ልጅ ከቦሌ ቀለማት ቆነጃጅት ጋር ያነፃፀረበትን ወገን ስቄበትም ተደንቄበትም አልፌዋለሁ፡፡
ለአራት ሰባት ምግብ
አዘው፤ በጋዜጣ ምናምን ነገር ያየዙትን ወጣቶች ‹‹ቀኑ ቅዳሜ ነው›› ያለበትን ምክንያት ወድጄዋለሁ፡፡
በአንዳንዱ ገጽ የተለያዩ ግጥሞች የሚመስሉ ስንኞች በተለያየ ርዕስ ስር
ቢቀርቡም እርስ በርሳቸው የተያያዙና የተደጋገፉ አንዱን ካለነበብን
የሌላኛው የማይገባን ግጥሞች ናቸው፡፡ ምናልባት እንደ ሌሎች የግጥም መድበሎች ከመሃል አንድ፤ ከዳር አንድ እያደረግን የምናነበው
ከኾነ አይገባንም፡፡ በአብዛኛው ሁሉም ማለት ይቻላል በ 21 -04-2004 እስከ 29 -04 2004 ባሉት ቀናት ውስጥ የተጻፉ
መኾናቸውን በግርጌ ማጣቀሻቸው ማየት ይቻላል፡፡ ኤፍሬም ስዩም በዚህ
የግጥም ስራው አንዲት የወደዳት ያፈቀራት አብሮ ትኖር የነበረችን ሴት እያስተዋወቀ ለሌላ ባል የተሰጠችውን ፍቅረኛውን የበለጠ ሃብት ፈለጋ ወደ ሌላ
ወንድ ጋር ሄዳ የምታሳልፈውን ሕይወት ከጓደኛዋ ከጎረቤት ከሰራተኛ እና እራሱም የሚያየውን እየጠቀሰ ይተርክልናል፡፡ ምናልባት ትግስተኛ
አንባቢ ካልሆኑ በዚህ ዘመን ደግሞ ‹‹ምን ያለ ፍቅር ነው›› ልትሉ ትችላላችሁ፡፡ የዋዛ እንዳይመስላችሁ፡፡ በገጽ 87 ላይ በምናገኛት
‹‹ደባል ታቦት›› የግጥም ስንኝ ብዙ ልንማር ብዙ ልናውቅ ብዙ ልንለወጥበት የምንችልበትን ሃሳብ በአዲስ ቀን 01-03-2003 ወደ ኃላ በመመለስ ያቀርብልናል፡፡ አዲስ ቀን ነው፡፡ ምናልባት
ግን 2003 ዓ/ም በስህተት የተገለጸ ሊሆን እንደሚችል ገመትኩ፡፡ ምክንያቱም በገጽ 87 የምናየው ‹‹መቼም›› የተሰኘችው ግጥም
የተጻፈችው በ02-03-2004 በመሆኑ፡፡
ከዚህ በገጽ
91 ስንበት በሚል ያቀረበው ግጥም የዚህ ሁሉ ታሪክ መገባደጃ በመሆን ቻዋ !! ይላታል፡፡ ‹‹ሁሉም ከንቱ ነበር›› የሚለው ቀጣይ
ግጥም በገጽ 92 ይቀርብልናል፡፡ አራት ጊዜ አንብቤዋለሁ፡፡ ወድጄዋለሁ!
የመጣሁበትን ጉዞ ሁሉ አሳረፈኝ፡፡ አስተማረኝ፣ መክረኝ፣ እንድጠይቅ አደረገኝ፡፡ ተባረክ ኤፍሬም!
ለዚህ ዘመን፣ ለዚህች አገር፣ ለዚህ ትውልድ፣ ለሽማግሌ ለነገስታት የተጻፈ ግጥም፡፡
ህልማችን መተኛት
ህልማችን መጠጣት
ተሰብስቦ ማውራት ማውራት ማውራት ማውራት-- ---
አዎን በዚህ ሀገር
ሁሉም ከንቱ ነበር፡፡
ሽማግሌው መውራት
ወጣቶቹ ማውራት
ነገስታቱ ማውራት
ማውራት ብቻ ጥበብ ሕይወት የሆነበት
እርስ ኢትዮጲያ ናት፡፡
ያንብቡት! ከዚያ
በገጽ 97 ላይ ሐያሲ በሚል የግጥም ስንኝ የግጥሙ ፍሰት ይቋጫል፡፡ በ 30 02- 2004፡፡
በገጽ 101 መውጫ ወዳሻችሁ በሚል ርዕስ የተጻፈን ደብዳቤ ከምጠብቀው
በላይ በእያንዳንዱ መስመር እፈልጋት የነበረችውን የመድበሏን ዋና ገጸ-ባሕርይ ‹‹ምንም›› አጥብቂ እንድፈልግና ያቀረበበትን የአፋልጉኝ
ርዳታ በምልክተ ያስቀመጠበትን ‹‹ዘይቤ›› ከሚገባው በላይ ለመረዳትና ልጁንም በማድነቅ ምነው ፅሑፍ ባለለቀ አስብሎኛል፡፡ እነዚህ
4 ገጾች የጸሐፊውን ልዩ ችሎታ ያሰዩ ሃሳቦች የተሰነቁበት ልዩ ክፍል ነው፡፡
በዚህ ዘመን የምንፈልገው ጸሐፊ ከራሱና ከፈጣሪው ጋር ተጣልቶ እኛንም የሚያጣላን፤
ውዥንብር ፍልስፍና ሳይኾን በብዙ መንገዶች በስነ-ጥበባዊ ወዝ እያዋዛ ራሳችንን፣ አገራችንን ፈጠሪያችንን ፈልገን ለለውጥው የምንነሳበት ሀሳብ የሚጠቁምን
ነው፡፡ ጥበብ ከሰይፍ ከጦር የበለጠ ሀይል አላት ያልኩበት ምክንያትም ይህ ነው፡፡
ጸሐፊዎች-
ገጣሚዎች ስነ-ጽሑፍ ሰዎች ከዚህች ስራ ብዙ ሊማሩ ይገባል፡፡ አንባቢያን ከዚህ መጽሐፍ ብዙ ነገር ትፈልጋላችሁ፡፡ እናትን ፈልጎ ለማግኘት ቢያንስ ወደ እውነት ፍለጋ መንገድ የምትመራ ድንቅ መጽሐፍ፡፡ ኤፍሬም ስዩም በእውነት ትችላለህ!
የራስን ፍለጋ ጨርሰህ እርፍትህን ሽተህ ሌሎች እንዲፍልጉና እንዲያርፉ ለማድረግ መሞከርህ ያስመሰግንሃል፡፡ እውነትን እንድንይዝ
እውቀትን ጥበብን እናገኝ ዘንድ ፈጣሪ ይርዳን፡፡ እናታችን ጠፍታለች ጭራሽ ደግሞ መገኛዋ ጠፍቶ ላትገኝ ስትዋትት ከማየት ፍለጋው
ይጠንከር፡፡በማንም እጅ ስር ተይዛ ሲያሻቸው ሊጨብጧት ሲያሻቸው ሊገነጣጥሏት የሚሹ ሀይሎች አሉና ሁላችንም እንታደጋት፡፡ እናታችን
ጠፍታለች፡፡ አፋልጉን ከጠፋች ልክ 38 አመቷ፡፡
No comments:
Post a Comment