ኢትዮጵያ እና የሚስጥራዊ ቡድናት ተጽዕኖ
ተስፋ
በላይነህ
በመላው አለም
የነበሩ
ነገስታት/መሪዎች
በንግድ፣
በአምልኮት፣
በባህል፣
በፖለቲካ
እና
በጋብቻ ቁርኝት እርስ
በርስ
ታሪክን ሲጋሩ
ሰምተናል-አንብበናል-አይተናል፡፡
የኔ
የሁልጊዜ
ጥያቄ
የሚሆነውም
ኢትዮጵያንና
የሌሎች
መንግስታት
ትስስርን
፤ ኢትዮጵያን የሚስጥራዊ ቡድኖች
ተጽእኖ
ማፈላለግ፤ መጠየቅና መላምት ማቅረብ የሚበጅ እንጂ የሚያስኮንን እና የሚጎዳም አይመስለኝም፡፡
የፖለቲካ ፓርቲዎችም ልብ እንዲሉት የሚሻ ጉዳይ ነው፡፡ ማለትም የኢትዮጵያን ታሪክ ስናስብ የውጭ ሃይላትን ጣልቃ ገብነት በማሰብ፤
የደረሰውን ውስብስብ ሴራ በማጥናት፤ ይህንን ሴራ ያደረሰውን አስከፊ ጉዳት/እልቂት በመለየት ሊመጣ የሚችለውን ተያያዥ ችግር ለመቀነስ
እና መፍትሄ ለመውሰድ የሚጠቅም መሆኑ የሚያጠያይቅ አይደለም፡፡
ወደ ኋላ
ረዥም
ርቀት
ተጉዞ
መመርመር
እንደ
ርቀቱ፣
ብዙ
ጊዜና
ጉልበት
እንዲሁም
የመረጃው/ማስረጃ/
እጥረት
ስለሚኖር
ለጊዜው
ይቆየን፡፡
ነገር
ግን
የንግስተ
ሳባ
ከሰለሞን
መመለስን
እንደ
ማጣቀሻ
መቃን /ሪፈረንስ ፍሬም/
በመውሰድ
የዚህ
ዘር
ሃረግ
ወደ
ሆነው
የሰለሞን
ዘር
ዘውዳዊ
አገዛዝ
ስር
እንወድቃለን፡፡
በእውን ይህ ዘውድ ለሚገባው እና ለተገባው ሰው ተላልፏል የሚለው ጥያቄ የራሱ መጽሐፍ የሚወጣለት ስለሚሆን ወደ ጎን እንተወው፡፡
ሚስጥራዊ ቡድናት ከሰለሞን ታሪክ ጋር የተያያዘ ረዥም ታሪክ እንዳላቸው ይነገራል
እና ኢትዮጵያም ከዚሁ ጠቢብ ጋር የተሳሰረችበት ያፈጠጠ ታሪክ አላት፡፡ በዚህም መሰረት ከንግስተ ሳባ ጀምረን የኢትጵያን ታሪክ
በማየት የሚስጥራዊ ቡድናት ትስስርን እንድንገነዘብ፣ እንድናጠና እና መላምት በማቅረብ ከባርነት ለመውጣት፣ ከውስብስብ ችግር ለመላቀቅ
ከሚረዱን ጉዳዮቻችን በተቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው፡፡
ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው
የረዥም ታሪክ ባለቤት ስንሆን ተጨባጭ ማስረጃ ማግኜት ስለሚከብድ በንግስተ ሳባ የነበረንን ሁነታ ለማገናዘብ እንቸገር ይሆናል፡፡ የሰለሞን ዘር
ዘውዳዊ
አገዛዝ
በተቋረጠበት
የዛጔ
ስርወ
መንግስት
ሲተካም
እንኳ
የሚስጥራዊ
ቡድኖች
ህልውና
በምድራችን
ስያሜን ቀይሮ ብቅ ያለበት ወቅት ነበር፡፡ “ቴምፕላሮቹ” የደመቁበት
ወቅት የንጉስ ላሊበላ ዘመን ነበረ፡፡ ግራም ሃናኩክ በ the
sign and the seal መጽሐፉ ላይ የላሊበላን ዘመን ከቴምፕላሮቹ ጋር የነበራቸውን ቁርኝት ለመጥቀስ ሞክሯል፡፡
በተለይ
በስፋት
የተቀመጠውና
ከዛጔ
ስርወ
መንግስት
የቅዱስ
ላሊበላ
ታሪክ
ከ
ቴምፕላሮች
ጋር
የነበረው
ትሰስር
ብዙ
ለማሰብ
በር
የከፈተ
ነው፡፡
በ13ኛው መቶ
ክ/ዘመን
የነበረው
የመስቀል
ጦርነት
ከኢትዮጵያ
ወደ
እየሩሳሌም
የሚጓዙ
ሰዎችን
ከቦታው
ርቀትና
ወደ
ቦታውም
እስኪሲደርሱ
የነበረው
አለመመቻቸት
ንጉስ
ላሊበላን
ከሱልጣን ሳላዲን ጋርም በመወያዬት "ዳግማዊት እየሩሳሌምን"
ኢትዮጲያ
ውስጥ
ለመገንባት
አስቻለው፡፡
ድንቅ
ውቅር
አብያተ
ክርስትያናትም
ተገነቡ፡፡
የሚስጥር
ማህበራትን
በዋነኝነት
ሊያመላክቱ
ከሚችሉ
ማስረጃዎች
አንዱ
ምልክቶች
በመሆናቸው
በላሊበላ
ውቅር
አብያተ
ክርስትያናትም
የምናገኛቸው
የስዕልና
የቅርጻቅርጽ
ምልክቶች
ብዙዎችን
እስከ
ዛሬ
እያነጋገረ
ይገኛል፡፡
ለወደፊትም
እየበዛ
መሄዱ
አያጠያይቅም፡፡
የቀደሙት ነገስታቶቻችንን
የውጭ
ግንኙነት
በምንመለከትበት
ወቅት
ከውጭው
አለም
ጋር
የሚኖራቸው
ቅርርብም
ሆነ
ትስስር
‹‹በየዋህነትና››
ሴረኛ
መሆናቸውን
አለመገንዘብ
ትልቁ
ችግር
እንደሆነ
ለመውሰድ
እገደዳለሁ፡፡ ይህም የሆነው
የኛ
ነገስታት
ከነበራቸው
አምላካዊ
ፍቅርና
ክብር
የተነሳ
ማንኛውንም
መስቀል
የያዘ፣
የክርስቶስን
ስም
የጠራን
ሁሉ
በርቀት
አምኖ
ሌላ
ሚስጥር
ሊኖር
እንደማይችል
ማሰባቸው
በመጠኑም
ቢሆን
እንድንመለከት
ፍንጭ የሚሰጠን ሐሳብ ነው፡፡ /ሙሉ በሙሉ
መደምደም
ባይቻልም/፡፡
ዋነ
ቁም
ነገር
ነው
ብዬ
የምወስደው
ነገር
ግን
በግለሰብ
ደረጃ
እንትና
የዚህ
ግለሰብ
አባል
ነበረ፡፡
ይህኛው
ቀንደኛ
ተከታይ
ያኛው
ደግሞ
ተቃዋሚ
ነበር
ወደ
ሚለው
ሳይሆን
ከጀርባ
የሚኖሩትን
ተጽእኖዎች
በማገናዘብ፣
በማመሳከርና
መላምት
በመስጠት
ለኛ
ህልውና
የሚበጀውን
መውሰድ
ነው
ዋናው
ጭብጥ፡፡
በተለይ
በተለይ
አንዳንድ
የጽሑፍ፣
የስዕል
እና
የዜማ
መረጃዎችን
በማገናዘብ
ጥያቄ
እያቀረቡ
ልንወስድ
የምንችለውን
ውሳኔ
ለየግላችን
መገምገም
እንችላለን፡፡
ለወደፊትም
እንድንጠነቀቅ
ይረዳናል፡፡
በተለያዩ ጊዜያት በሚስጥራዊ
ቡድናት ጉዳይ ከተለያዩ ሰዎች ጋር በአጋጣሚ ለመወያዬት እድሉ ተፈጥሮ
ነበር፡፡ በዚህም ጉዳይ የእይታ አድማሳችንን እንድናሰፋ እና የአጽዕኖት
አቅጣጫችንን ወደኛ እንድናተኩር አመቻችቶልናል፡፡
ሚስጥራዊ ቡድናት በአሁኑ
ሰዓት በሙዚቃው፣ በፊልሙ በስፋት እየተንቀሳቀሱ እና ዓላማቸውን እያሳኩ ይገኛሉ፡፡ በውጭው ዓለም ያለውን ትዕይንት እያስተዋሉ እየተላለፉ
ያለውን ድብቅ አላማ ብቻ ላይ ከማተኮር ወደ ሀገራችንም መመልከት
ብንችል የበለጠ የሚጠቅም መሆኑ የሚካድ አይደለም፡፡ በዚህ ወቅት ነበር ወደ ኢትዮጵያችን መዘውራችንን ቃኝተን ስናተኩር ያልተለመዱና
ያልተጠበቁ ጥርጣሬ ውስጥ የሚከቱ ምልክቶችን ያስተዋልን፡፡ የብርሃንና
ሰላም ማተሚያ ድርጅት አርማ ብንመለከት የባለሶስት ጎን ቅርጽ ሆኖ በውስጡ የጸሐይ ምስልም ተቀምጧል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
በባለክብ ቅርጽ የሚሽረከሩ ሶስት ጥማጣሞች የ666 ቁጥርን ሊፈጥር ይችላል፡፡ ሌሎች ሌሎች…
በዚህም ዋና መሰረተ ሀሳብ
በመስማማት ሀገራችን ውስጥ በድብቅ እና በጉልህ የሚታይን የሚስጥራዊ ቡድናት አሻራ ለመለየት መላምት በማቅረብ፤ ማስረጃም በመጠቆም
ውሳኔውን ለየግል መተው ላይ ያደርሰናል፡፡
ስለ ማዶና እና ስለ ሌዲጋጋ የግብረሰዶማውያንን ጠበቃ ሆነው የሚያቀነቅኑትን
ዘፈን ብቻም መመልከት የለብንም ፡፡
እንግዲህ
የግለሰቡን
ማንነት
ላይ
የመፍረድና
የመፈትፈት
ስራ
ሳይሆን
ሁልጊዜም
ለሚቀርቡልን
ነገሮች
የሚጠይቅ
አዕምሮ
እንድንይዝ
የሚረዳ
ሃሳብ
እንዳለኝ
ጠቅሻለሁ፡፡
ኢትዮጲያ
በታሪክ
ከምትታወቅባቸው
እሴቶች
አንዱ
አረንጓዴ
ቢጫ
ቀይ
አርማ
ቀስቴን
በደመና
አኖራለሁ
ተብሎ
ፈጣሪ
ኖኅን
ቃልኪዳን
እንደገባለት
የምናውቀው
ነው፡፡
ሆኖም
ቀስተ
ደመና
ከ3
በላይ
ቀለማትን
መያዙን
እየተገነዘብን
በምንለብሰውም
ጥለት
3 ቀለማትን
እያኖርን
ቀስተ-ደመና
ያለበት
ጥለት
የሚያደርግን
ሰው
ስናሰብ
አሁን
ካለው
ተጨባጭ
መረጃ
ቀስተ
ደመና
የግብረሰዶማዊያን
መለያ
በመሆኑ
ላለመረዳት
ችላ
የምንለው
ነገር
መሆንም
የለበትም፡፡
እርግጥ
ነው
ምዕራባዊያን
ቅጡ
ውጥንቅጡ
ግራ
ቀኙም
ዞሮባቸው
የአለምን
ህግ
በቀየሩ
ቁጥር
እኛ
ፈጽመን
መረበሽና
መለዋወጥም
የለብንም፡፡
ቀስተ
ደመና
የኢትዮጲያ
መለያ
ለዓለምም
ቃልኪዳን
ሆኖ
ሲያገለግል
እንደሚኖር
ማንም
አይሽረውም፡፡
ነገር
ግን
አሁንም
ምዕራባዊያንን
ስናያቸው
በፍቅር
ስም፣
በነጻነት
ዝማሬ፣
በፈጣሪ
ህልውና፣
በፖለቲካ
ሸቀጥ፣
በዘፈን
ሃይል ብዙ ባዕዳን
አምልኮታችን
እያስተላለፉ
በሚገኙበት
ሰዓት
የነርሱን
ስራ
ከመፈተሸና
ለመጠየቅ
ባሻገር
የኛንም
ችላ
ማለት
ተገቢ
ሆኖ
አላገኘሁትም፡፡
እንደውም
በተቻለን
መጠን
የኛዎቹ
ላይ
ማተኮር
እንዳለብን
አምናለሁ፡፡
የኛውን
ታሪክ
የኛውን
ስነጥበብና
ፖለቲካ
ላይ
መወያቱ
እንደሚጠቅምም
ማሰብ
ህጸጽ
ያለው
አይመስለኝም፡፡
ሌላኛውም
የዘፈን
ግጥም
ውበትን
በጽሐይ
አምሳል
የመወከል
ጉዳይ
ጸባዬ
ሰናይ
በሚለው
ዘፈን
ላይ
ስለምናገኝ፡፡
ውበትን
ከግብጽ
ቆነጃጅት
ጋር
ማመሳሰልና
ጸሐይንም
ማቅረብ
አሁንም
ከነዚህ
ሚስጥራዊ
ቡድኖች
ቀንበር
ስር
መውደቅ
በመሆኑ
የሚታለፍ
አይሆንም፡፡
ሚስጥራዊ ቡድናት በጸሐይ ያመልካሉና!
እንግዲህ
ከላይ
ለመጥቀስ
እንደሞከርኩት
በአገራችን
የሚገኙ
ነገስታትና
ታላላቅ
ሰዎች
ለሚስጥራዊ
ቡድኖች
ምንም
አይነት
ግንዛቤ
ሳይኖራቸው
በተዘዋዋሪ
ግን
ተገዥና
ተጠቂ
ሆነው
እናያለን፡፡
ቀ.ሃ.ሥ
ከእንግሊዝ
መንግስት
ያገኙትን
ከፍተኛ
ማዕረግ
ለምን
ከማን
እንዴትና
ምን
ብለው
ላይቀበሉ
ይችሉ
ይሆናል፡፡
ነገር
ግን
ተቀብለዋል፡፡
እነ
አጼ
ቴዎድሮስ
እነ
አጼ
ዮሐንስም
ለእንግሊዝ
አቻዎቻቸው
ስመ
ክርስቶስ
ና
በመስቀል
ቅርጽ
መመሳሰል
በአንድ
እምነት
ስር
ሆኖ
በመገመት
ሲጻጻፉ
አንብበናል፡፡
የላሊበላንም
የምመለከተው
ከዚህ
ጋር
ነው፡፡
ምልክቱም
ቢኖር
እንኳ፣
አምነውበትና
ገብቷቸው
የተቀበሉት
ነው
ብሎ
ለማመን
ግን
ያዳግተኛል፡፡
አሳማኝና
ተቀራራቢ
ማስረጃ
ከሚያቀርብ
ሰው
ግን
ለመማማር
ዝግጁ
መሆኔን
እመሰክራለሁ፡፡
/የዴርቶጋዳው ጸሐፊ በዣንቶዣራ መጽሐፍ ለመጥቀስ ሞክሯል/፡፡
ከቅርብ ገዥዎቻችን የምንገነዘበው
ነገርም አለ፡፡ ቀ.ኃ.ሥ በዋነኝነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ በእጃቸው የሚፈጥሩት ምልክት፣ የቅዱስ ጊዮርጊስን ስም ለቢራ ምርትነት መለጠፍ፣
የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት አርማ፣ የኢትዮጳያ ንግድ ባንክ አርማ፣ ከ33ቱ የጣልያን መልቀቅ በኋላ የአብርሆት ዘመን / የኢሉሚኔሽን
ዘመን/ በጥርጥር እንድናይ እንገደዳለን፡፡ የአሜሪካ መንግስት ትስስር እንዲሁም የመጨረሻ ዘመን ዓመታት ከዚህም ባሻገር የአብዮቱ
መምጣት ከሚስጥራዊ ቡድናት እጅ የጸዳ ነው ብሎ መማን አንችልም፡፡
17ቱ አመት የደርግ አገዛዝም
ከሚስጥራዊ ቡድናት ተጽዕኖ መላቀቅ የቻለ ነው ብለን መቀበልም አይቻልም፡፡
በጣም በሚታይ መልኩ እና ብዙ ማስረጃዎችን ማቅረብ የምንችልበት ሌላኛ ው አገዛዝም ትኩረትን የሚሻ ነው፡፡
በአሁኑ
ዘመን
እንዲህ
መረጃ
በኪስና
በእጅ በሆነበት ጊዜ
ግን
ሚስጥራዊ
ቡድናትን
አላውቅም
ማለት
የሚከብድ
ሲሆን
ሳያውቁ
ለሚያደርጉትም
ማስገንዘቢያ
የመስጠት
አላማ
ተቀባይነትን
ሊያገኝ
ይችላል፡፡
ስለዚህ
በድምጻዊ
ቴዎድሮስ
ካሳሁን
እና መሰል የኪነጥበብ ሰዎች እና ሌሎችም አካላት ከሚስጥራዊ ቡድናት ሴራ እንዲጠነቀቁ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡ በጽሑፌ አጠቃላይ
ይዘት ማስጨበጥ የምፈፈልገው እና በአጽእኖት የምናስቀምጠው ይህንን
ይሆናል፡፡
ጥሩነቱ
ከዚህ
በኋላ
የሚወጡት
ስራዎችንም
እንዲፈትሽና
እንድናተኩር
የሚረዳን
ይሆናል፡፡
ቅንጅት ለአንድነት እና ለዲሞክራሲ ይዞት ብቅ ያለው የ ‘v’ ምልክትም በቀላሉ የሚታለፍ አይደለም፡፡ በ “አገቱኒ” መጽሐፍ ማን
እንዳወጣው ቢጠቀስልንም ምልክቱ ከሚስጥራዊ ቡድናት ምልክትነት አንጻር ታይቶ ይሁን አይሁን ማወቅ ይከብዳል፡፡
በቀድሞ ጠ/ሚንስትራችንም
በብዙ
መልኩ
ጥያቄ
የምናነሳበት
ጉዳዮች
አሉት፡፡
አሁንም
በግለሰብ
ደረጃ
የሚነሱ
ባለመሆናቸው
ትተውልን
ባለፉት
ስራዎች
ላይ
መጠያየቅ
ሙሉ
የተፈጥሮ
መብታችን
ነው፡፡
‹‹የህዳሴው
መሐንዲስ››
በመባል
የሚታወቀው
ጠ/ሚንስትር
ህዳሴ
/ትራንስፎርሜሽን/ በሚለው
ሃሳብ
ውስጥ
አንድ
ትውልድ
ከመንፈሳዊነት
ወደ
ቁሳዊነት
ሲሻገር
ተመልክቻለሁ፡፡
የአገር
ፍቅርም
ወደ
ብሄር
ብሄረሰብነት
ሲለወጥ
እያስተዋልን
ነው፡፡
ሚስጥራዊ
ቡድናትም
ከሚፈልጓቸው
ዋና
ዋና
ግቦች
ውስጥ
የመንፈሳዊነት
መጥፋት፣
የአገር
ፍቅር
መወገድ፣
የሰው ልጅን ተፈጥሮአዊ አላማ ማጥፋት በመሆኑ ይህንን
ግብ
ከማሳካት
አንጻር
እንዴት
ልናየው
እንደምንችል
ማሰብ
እንዳለብን
ተማምነንበታል፡፡
መጠየቅ
ተፈጥሮአዊ
መብት
መሆኑ
ግልብ ነው!
የማኬያቬሊ
ፍልስፍናም
ተደምሮ
፤ ክርስቶስ በደሙ
የዋጃት
ቤተ
ክርስትያን
ውስጥ
የራስ
ምስልን
ማስቀመጥ፤
መለስ እውነት ነው! ተብሎ ሲሰበክም ሰምተናል፡፡ “የመለስ ራዕይ” በራሱ ትልቅ አነጋጋሪ ጉዳይ ነው፡፡ በተለይ
ብዙዎችን
እያነጋገረች
ያለቸው
የሰንደቅ
አላማ
ልዩ
ምልክት
ባለ
አምስት
ኮከብ
አርማ
አመጣጧ
እንዲሁም
የተሰጣት
ትርጉም
ሁልጊዜም
እንቆቅልሽ
የሆነች
ምስክር
ነች፡፡
እኔ
በበኩሌ
ይህችን
ምልክት
ከባንዴራ
ተለይቶ
ማየት
የዘወትር
ህልሜ
ነው፡፡
ምንም
እንኳ
የህገ
መንግስቱን
ደንብ
ከመጠበቅ
አንጻር
ባለ
አምስት
ኮከብ
ምልክት
የሌለበት
ባንዴራ
ይዞ
መገኘት
እንደተከለከለ
ሁሉ
መንግስት
በተለዋወጠ
ቁጥር
ባንዴራ
ላይ
እንዲህ
አይነት
አሻራ
ማስቀመጡ
ብዙዎችን
ከጥያቄ
አልፎ
ጥላቻን
እንዲይዙ
ማድረጉን
በአይኔ
እና በጆሮየ
- አይቻለሁ ሰምቻለሁ፡፡
መለስ ዘናዊ በኬንያ ባንዴራውን ገልብጠው የያዙበት አጋጣሚ ነበር፡፡ ገዢው መደብ
የሚይዘው
ባንዴራ
ላይ
ምልክት
ማስቀመጥ
እንዲሁም
ማንም
የማይነካካው
ሰንደቅ
አላማ
እንዲኖር
በመመኘት
የግል
ሃሳባቸውን
ያስቀመጡ
ጥቂቶች
አይደሉም፡፡
ሆኖም
ሁሉንም
ለጊዜ
የምንሰጠው
ፍርድ
ይሆናል፡፡
ታሪክ ይፋረድ!
በብዛት
ወደ
ውጭው
አለም
የመጎብኘትን
ዕድል
ገና
በአልጋ
ወራሺነት
ዘመናቸው
ያገኙት
አጼ
ኃይለ
ሥላሤ
ብዙ
ሊያጠያይቅ
የሚችል
ጉዳይ
አለ፡፡
ሌ/ ኮለኔል ምንግስቱ ኃይለማርያም እና ጠ/ሚር መለስ ዜናዊም ከሚስጥራዊ ቡድናት ጋር የነበራቸውን ግንኙነት ካወቅን ምን ምን እንደሆኑም
ከተረዳን እና ከለየን መፍትሄው የተወሳሰበ አይሆንም፡፡ በጉልህ የሚታዪትን ጨምሮ ውስብስብ እና ሚስጥራዊ ጉዳዮችን መለየት የኢትዮጵያዊያን
የቤት ስራ ነው፡፡ ነጻ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያዊያን! ይቀጥላል…