‹‹ንስሩ›› አሞራ እንዳይሆን!
ንስር የሽልማት ድርጅት በበጌ
ምድር አውራጃ በጎንደር ከተማ ውስጥ የተቋቋመ ድርጅት ነው፡፡ ከስያሜው
እንደምንረዳው ‹‹ንሰር›› ነው፡፡ የተዘነጉ ግለሰቦችን እያደነ፤ በጎ ሰዎችን እያፈላለገ፤ አይዟችሁ የሚል ነው፡፡ በእውነቱ አላማው፣
አነሳሱ፣ አረማመዱ የሚያስመሰግን ነው፡፡ አሁን 5ኛ ዓመቱን ሊያከብርም ነው፡፡
እንደ አነሳሱ እና እንደያዘው
‹‹ሞቶ›› ከዚህ በላይ መራመድ፣ መፍጠን፣ መብረር እና መክነፍ እንዲሁም መታወቅ እንዳለበት ይሰማኛል፡፡
አንድ ነገር ሰምቻለሁ ምናልባትም
ይሄ ‹‹ሩመር›› የሚሉትም ሊሆን ይችላል፡፡ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እያስተዋወቀ ያለው የበጎ ሰዎች ሽልማት መስጪያ ዝግጅት ከየት ታስቦ
እንደተቋቋመ የገለጹልኝ ግለሰቦች ስላጋጠሙኝ ነው፡፡
ሙሉ በሙሉ እጄን እየቀሰርኩ፣ እየነቀፍኩ እና እያብጠለጠልኩ አይደለም፡፡
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የሚያዘጋጀው የሽልማት ድርጅት ከሞላ ጎደል ይዞት ተነሳው ሐሳብ ከንስር ሽልማት ድርጅት ጋር መቀራረቡም
ብቻ ሳይሆን በውስጥ ለውስጥ መረጃ አስተላላፊ ግለሰብ እንደሚኖር ስጋቱ በጭላንጭል ስለታዬ ነው፡፡ በጎነቱ ግን ሽልማት ድርቶች ቢበራከቱ
ጉዳት አለመኖሩ ነው፡፡ ሐሳቡም ቢወራረስ አንቃወምም፡፡
ለንስር ግን ክብር እንስጥ፣ አፈ ቀላጤ ግለሰቦችን መያዝ ስላልቻለ፤
ስሙ ላይጎና ይችል ይሆናል፡፡ እንደዛም ሆኗል!!!
አንዴ አብርሃም ወልዴ ስለ "አይዶል ሾ" ዝግጅት የተናገረውን አልዘነጋውም፡፡ "የጠፋውን ፕሌን ጫካ ውስጥ ሲጫወቱበት፣ ያም መጥቶ ሲነካካው፣ ጥሎት ሲሄድ፣ ያም መጥቶ ሶኮረኩረው፣ ጥሎት ሲሄድ…. መጨረሻ ላይ
ዋናው ሞተር እኛ ላይ ስለነበር/ እነ አብርሃም ወልዴ ጋር/ ልናንቀሳቅሰው ችለናል፡፡" ሲል ሰምተን ንጽጽሩን አድንቀን ነበር፡፡
አሁንም ምክሬ አዲስ ነገር የለውም፡፡ ንስሩ አሞራ እንዳይሆን፤ አሊያም
ቁራ!!!! ቁራ ተልኮ መልዕክቱን ሳይመልስ በዛው እንደቀረው… አይዟችሁ!!!
የድርጅቱ መስራች እና አባላቱ ኤፍሬም ቢያድግልኝ ራዕያችሁ እንደ ንስር እንደሆነ ለመገንዘብ ችያለሁና!!
የድርጅቱ መስራች እና አባላቱ ኤፍሬም ቢያድግልኝ ራዕያችሁ እንደ ንስር እንደሆነ ለመገንዘብ ችያለሁና!!
አይዟችሁ ሞተሩን አንቀሳቅሱት፣ ወጣትነታችሁን አጉኑት፣ የዘመኑን ተራ
ርካሽ ጭብጭባ እና የአፈ ቀላጤዎች ጩኸት ርቃችሁ ማንነታችሁን አሳዩ!!!
ከፖለቲካ ነጻ ሁኑ፣ ማንንም አትፍሩ፣ በጎነትን በተግባር አሳዩ፣ ለሽማት
ብቻ ሳይሆን አመቱን በሙሉም ስራችሁ ይታይ፣ ለማሕበረሱ ግልጋሎት፣ አዳዳዲስ ሐሳቦችን ለግሱ፣ ወጣትነታችሁ በጉልበት፣ በጭንቅላት፣
በተስፋ በሩጫ፣ በሕልም፣ በራዕይ የተሞላ ይሁን!! አይዟችሁ!!!
መዋቅራችሁን አስፋፉ፣ ሰዎችን አማክሩ፣ ጠይቁ፣ እንዳትተኙ ምክንያቱም
ዘመኑ በጣም አስቸጋሪ ነውና‹‹‹‹‹‹፡፡ የገንዘብ አስተሳሰብ፣ አስተሳሰር፣ አስተዳደር የተስፋፋበት ጊዜ ነው፡፡ አይዟችሁ!!!!! ብዙ ግን ይጠበቅባቹኃል!!!
ይጠበቅብናል…. ንስር ነንና!!!!!!
ክብር ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች፤ ለእውነተኞቹ፤ ክብር ለዳንኤል ክብረት/ ለአመቱ በጎ ሽልማት!!/ክብርም ለንስር!!!!!
https://www.facebook.com/groups/197616640408277/
No comments:
Post a Comment