Jun 11, 2014

በዶክተር በርናንድ እና ሲ/ር እማዋይሽ ገሪማ ቤት

በዶክተር በርናንድ እና ሲ/ር እማዋይሽ ገሪማ ቤት
‹‹‹‹‹‹‹ተስፋ በላይነህ›››››››
ገሪማ ታፈረን በስፋት የምንውቃቸው በጎንደር ከተማ ፈረሳቸው ይዘው ሲጋልቡ፣ ጎንደሬ በጋሻው በሚል ርዕስ የሚጻፉ ወረቀቶችን በማዘጋጀት፣ አባ ታጠቅ ካሳ የቋራው አንበሳ፤ ‹‹የመከራ ደወል ከምጥዋ እስከ መተማ›› ‹‹የብረት ጋሻ›› እና ሌሎችን ስራዎች የሰራ ታላቅ ሰው ነበሩ፡፡ የፊልም ጥበብንም በመጀመር ከሚታወቁት ሰዎች አንዱ እርሳቸው ሲሆኑ ይሕንን ሙያ እና ፍላጎታቸውን በትምህርት በማገዝ ልጃቸው ፕሮፌሰር ሀይሌ ገሪማ አሳክቶላቸዋል፡፡

ዛሬ ደግሞ ከአንደኛው ልጃቸው ሲስተር አማዋይሽ ገሪማ ቤት ተጋብዘን ተገኘን፡፡ ዋናው ግብዣው በቤታቸው ውስጥ እያስገነቡ ያሉትን የሕክምና ማዕከል ለመጎብኘት ነበር፡፡ ይሕ የሕክምና ማዕከል ለወደፊት አገልግሎት መስጠት ሲጀምር በሕክምናው ዐለም ውስጥ ታላላቅ የሕክምና መሳሪያ የሚባሉትን እንደ ሲቲ ስካን እና መሰል መሳሪያዎች ይኖሩታል፡፡ በዘመናዊነቱ እና ጥራት ባለው የሕክመና ማእከልነቱ ተጠቃሽ መሆን እንደሚችል ሳንጠራጠር፤ በመሰራት ላይ ያለው ሕንጻም ሆነ ሙሉ ዕቃዎች ተሰናድተው አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ በጎውን እየተመኘን፤ የሚመለከታቸው አካላትም የበኩላቸውን ትብብር እንዲያደርጉ መልዕክታችንነ እናስተላልፋለን! በጎ ሰዎችን ያብዛልን….! ንስር የሽልማት ድርጅትም እኚህን ሰው በማስታወስ ለህዝቡ ያበረከቱትን አስተዋጽዖ ግምት ውስጥ በማስገባት መሸለሙን እናደንቃለን፡፡
The up coming Hospital in Gondar

የዚህ ሕክምና ማዕከል በዶ/ር በርናንድ አንደርሰን የሚመራ ሲሆን፤ ሲ/ር እማዋይሽ ገሪማ ከሕንጻ ግንባታ ስራ ማማከር ጀምሮ የማዕከሉ ልብ ናቸው፡፡ ዶክተር በርናንድ አንደርሰን በትውልድ ጃማይካዊ- American ሲሆኑ በሕክምናው የሰርጅንነት ማዕረግን ያገኙ በአሁኑ ሰዓት በጎንደር ዮኒቨርሲቲ በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡ “እድሜየን በሙሉ ኢትዮጵያን በማገልገል እኖራለሁ!” ነበር በንስር ሽልማት ጊዜ የተናገሩት…!   
ሲ/ር እማዋይሽ ገሪማ በጎንደር ከተማ ከዓመታት በፊት ጋፋት በተሰኘ ጋዜጣቸው እናውቃቸዋልን፡፡ በአገር ጉዳይ ላይ የሚታዪ ማናቸውንም ክስተቶች እየመዘገቡ፣ እያስታወሱ፣ እየመከሩ ታላቂቷን ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ ሲታገሉ የነበሩ ብርቱ ሴት ናቸው፡፡ እድሜና ጤና ይስጣቸው…!!
Sister Emawayish Gerima

እንግዲህ ከእነዚህ ጥንዶች ቤት ውስጥ መገኘት የሚሰጠውን ልዩ ደስታ ማሰብ የሚከብድ አይመስለኝም፡፡ ቤት የገነት ተምሳሌት ነው፡፡ አባት ካህን ነው፡፡ እናት ሰብሳቢ ናት፡፡ ልጆች የፍቅር መገለጫዎች ናቸው፡፡ የአንድነት፣ የፍቅር ተምሳሌት ነው ቤት፡፡
ከሚወዱት ሰው ጋር አንድ ጣሪያ ስር እንደመኖር ምን ገነት አለ? የሚወዱትን ስብዕና ይዘው በቤት ውስጥ በመተግበር ከመኖር ውጭ ምን ገነት አለ? የሚወዱትን ስራ እና ለሚወዱት ሕዝብ እየለገሱ ከመኖር ሌላ ምን ገነት አ..ለ..? የምድራዊው ገነት ምሳሌ ቤት ነው!! /በነገራችን ላይ ልጆች በቤት ውስጥ የሏቸውም/

ያው በቃ ስዕል በመሳል፣ ቅርጻቅርጾችን በማዘጋጀት፣ መጽሐፍትን በማንበብ እና በመጻፍ፣ የምርምር ስራዎችን በመስራት ያሳልፋሉ፡፡ ምናልባትም በቤት ውስጠ ያሉ ጥሪቶች እንደ ልጅ እየሆኑ ይሆንን ብለን ጠይቀናል፡፡ ይሕ ቤት ለወደፊት ወደ ሙዚየምነት የመቀየር ዓላማን የያዘ ነው፡፡ መሆንም የሚገባው፡፡ ሕዝብ ማዬት ያለበት ምስጢር፤ የአፍሪካዊነት እና የኢትዮጵያዊነት መሰረት የት እንደሆነ የሚማሩበት፤ በኢትዮጵያዊነት ጥልቅ ፍቅር ተነድፈው የሚወጡበት፣ ወደ የት እየሄድን ነው ብለው የሚጠይቁበት ቤት ነው!! 

በፈጣሪ ሀይል በመታገዝ ፍርድን መስጠት፣ በፍትሃዊ አስተዳደር ህግ መሰረት ሰውን ማስተዳደር፣ የስራ ክፍፍልን በየሰው መደብ አስቀምጦ ማስተዳደር መቻል አሁን ዘመናዊው የሰለጠነ የሚባለው ዐለም የሚተዳደርበት ሲሆን መሰረቱ እዚሁ የጥቁሮች እንደሆነ ይመግሩናል፡፡ ዴሞክራሲንም እና ጀመርነው የሚሉት ግሪኮች እዚህ ቤት ዜና የላቸውም… ታላቁ አባት ካህን የሙሴ አማት ዮቶር ጨርሶታል!!
የጥቁር ሃያልነት፣የስልጣኔ ስር መሰረት፣ የሳይንስ እና የምርምር፣ የሰው ዘር መገኛ አፍሪካ መሆኗን ያስታውሱናል፡፡ አብርሃም ከመልከ ጼዴቅ መባረክን ሲያገኝ፣ አስራት ሲከፍል፣ ልጆቹን ሲያስገርዝ ይህን ሁሉ ህግና መመሪያ ያገኘው ከጥቁሩ ሰው እንደሆነ ይነግሩናል፡፡
“አብርሃም ኮፒ ነው” በማለት!!

በዚህች አጭር መጦመሪያ ሜዳ ላይ ይሕንን ቤት ጋልበን አንጨርሰውም፡፡ 

የገነት መገኛንም ከሳይንሳዊው እና ከመጽፍ ቅዱስ ምነጮች ጋር በማዛመድ በዘመናዊው የቦታዎች መገኛ መስፈሪያ ያስቀምጡልናል፡፡ አዲስ አበባ አካባቢ ናት ገነት ይሉናል…!!
ይሕንንም እነ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ የተናገሩትን ቃል በማመሳከር ቅኔ ይፈቱልናል፡፡ ዶ/ር በርናንድ አንደርሰን ፕ/ር አስራት ወልደየስን በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሰርጅን ዶ/ር ብቻ ብለው አያደንቋቸውም፤ የአፍሪካ ታላቅ ሰው ናቸው፤ በእስር ቤት ውስጥ የተናገሩትን ቃል ደጋግመው ይናገሩታል፡፡ “በእስር ቤት ውስጥ ሆኜም ኢትዮጵያን አልረሳም….”
Professor Asrat Woldeyes

የእተጌ ጣይቱን ታላቅነት ይነግሩናል፤ የእምዬ ምኒልክን አስተዋይነት ይነግሩናል፡፡ እኛ ታሪካችንን መናገር አይሆንልንም፡፡ የእኛ ታሪክ በእኛ ሲነገር የጠብ ታሪክ ነው፡፡ የቂም ትርክት ነው፡፡ በሌሎች ሲነገረን ግን አፋችንን ከፍተን ማዳመጥ ብቻ ነው፡፡
Etegie Taytu

ዶ/ር በርናንድ አንደርሰን ሳይንስንና ሐይማኖትን ማነጣጠል አይፈልጉም፡፡ በዚህም አንድ ምርምር ሰርተው በማሳተም ላይ ናቸው፡፡ ትንሽ ግራ የተጋባንበትም ስለነበር በቂ ምርምር እና ጥናት እንዲሁም ክትትል አድርጎ ለመተርጎምም ሆነ በሚገባን አቀራረብ ማዘጋጀት የሚችል ቢኖር ጠቃሚ ይመስለናል፡፡

በባህላችን የእንጀራ መሶብንና የሰበጥራን ሳይንሳዊ ምርምር ምስጢር ሲያስቀምጡልን አስገርሞንል፡፡ በኢትጵያ ውስጥ የሚገኙ የባሕላዊ እቃዎችን ምንነት፣ በሳይንሳዊ ምርምር ጥናት ቢደርግባቸው በርካት ምስጢሮችን ማግኘት እንደምንችል ነው የሚንሩን፡፡ የእነ አልበርት አንስታይን የዩኒቨርስ አመሰራት፣ ከምንም ወደ ትልቅ ይዞታ /Expansion/  ከዛም ወደ ጠባብ እና ወደ መጥፋቱ የሚሄድበትን ትንተና በመሶብ ቅርጽ ያስቀምጡልናል፡፡ የቶ ቅርጽ ምንነት፣ መሰረት፣ በጥንታዊ ግብጽ እና የኩሽ ምድር ጥቅም ላይ መዋሉን፣ የሆረስ እና ኢሲስ ታሪክ፣ የጥቁር ማርያም እና የጥቁር ክርስቶስ ምስል በሚካኤል አንጀሎ ከ1500 ዓመታት በኋላ የተቀየረ መሆኑን በምስል ያስረዳሉ፡፡
ምናልባትም ከግል እምነት አንጻር ሊፈተሸ የሚገባቸው የምርምር መዳረሻዎችም ሊኖሩ እንደሚገባቸው የተወያየንባቸው ነጥቦች ነበሩ፡ ወደ ገነት ለመግባት በርካታ መንገዶችን ተጠቅመን ማግኘት እንደምንችል፡፡ የባለ ስድስት ኮከብ ቅርጽ እና የባለ አምስት ኮከብ ቅርጽ ያላቸውን ልዩነት እና የሉሲን አፈጣጠር በሰፊው ተወያይተንበታል፡፡
ተዘርዝሮ አያልቅም፤ ይሕንን ቤት ወደ ሙዝየምነት ለመቀር መንግስት እና የሚመለከታቸው አካላት የበኩላቸውን ቢያደርጉ የሚገኘውን ጥቅም በገንዘብ ብቻ የምንገምተው አይደለም፡፡ በተጨማሪ እና በዋናነት በመገንባት ላይ የሚገኘው የሕክምና ማዕከል አገልግሎት የሚሰጥበትን መንገድ ብናመቻች የሚል መልዕክት እናስተላልፋለን፡፡
በታላቁ ሊቀ ነብያት ሙሴ እና በድንግል ማርያም ልጅ ክርስቶስ መካከል ያለውን ልዩነት፤ ክርስቶስ በሰላም በፍቅር እና ይቅር በመባባል እንደፈጸመው ያጠናቅቁልናል…!



ሰላም…ፍቅር… ይቅር መባባል….!
Nisir Award visitors 

No comments: