May 5, 2014

The book Title/ትንሳኤ ናፋቂዎች፡/ መልዕክት ወደ ኢትዮጵያ ሰዎች

The book Title/ትንሳኤ ናፋቂዎች፡/
መልዕክት ወደ ኢትዮጵያ ሰዎች
The Epistel of hope to the Ethiopians

…ሰላም እንደገና ሰፍኖ አሁን ያለው ትውልድ የሚያስብ፣የሚሰማ ብቻ ሳይሆን የሚያዳምጥ፣ የሚያይ ብቻ ሳይሆን የሚያስተውል፣ በዛሬና በተነገወዲያ መካከል አስተማማኝ ድልድይ ሊሆን እንዲችል ለማድረግ ምን መደረግ አለበት?...
ዶ/ር ዮናስ አድማሱ
የድልድዩ መሰረት፡-
ሙሴ ዕብራዊያንን ከ “ባርነት” ሊያወጣ የመጣው ወደ ካህኑ ዮቶር ነበር። በዚያም በጎቹን እየጠበቀ የካህኑ ዮቶርን ልጅ ሲጳራን አግብቶ ልጆቹን ወልዷል /ጌርሳም እና አልኣዛር/።* ታላቅ ጥበብንም አግኝቶ ተመልሶ እስራኤልን ከባርነት ቀምበር አላቅቋል። የእግዚአብሔርንም ድምጽ የሰማው በዚህ ነበር፡፡ ለአርነት ጉዞ ስንቅ የሰነቀው ከዚህ ነው፡፡
ዮቶርም ከልጆቹ ጋር ወደ ምድረ በዳው ሄዶ ሙሴን ጠይቆታል። የድሉን ብስራት ሊጋራ፤ በነጻነታቸውም እግዚአብሔር ስላደረገላቸው ተዓምራት  ዮቶር አምላክን ሊያመሰግን ወደ ሙሴ ሄደ፡፡ ፈጣሪን አመሰገነ። መስዋዕትም አቀረበ።
በተለይ በዚህ ወቅት ሙሴ ከባድ ፈተና የሆነበትን ህዝብ የማስተዳደርን ጥበብ በቀላል መመሪያ ከዮቶር ተቀብሏል። *
ለትዝብት እና ለታሪክ ፍርድ እንዲሆን ኢትዮጵያን ከዘመነ መሳፍንት ማብቂያ ጀምሮ ማለትም ከ19ኛው ክ/ዘመን ከዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ ጀምሮ እስከ 21ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ድረስ ለከ150 ዓመታት በላይ የገዟትን መሪዎች እንመልከት፡፡ ነእነዚህ ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ 6 ዋና ዋና መንግስታትን አስተናግዳለች፡፡ በአማካይ አንድ ንጉስ ለ25 ዓመታት ቆይታ፡፡ ተክለ ጊዮርጊስ እና ልጅ እያሱ እንዲሁም ንግስተ ነገስት ዘውዲቱ መሃል መሃል እየገቡ የተቀመጡ ሲሆን ከተጽዕኖ እና ሃያልነታቸው አንጻር በሰፊው ሲተነተኑ አናያቸውም፡፡
ኢትዮጵያ ሆይ አንድ መሪ ግን ትናፍቂያለሽ! የትላንቱን ሃያልነትሽ ከዛሬው መሰረት ያደርገዋል፡፡ ለነገውም ተስፋ! ትንሳዔ የሚናፍቁ ነፍሳት ተያይዘዋል! የተስፋ መልዕክት ወደ ኢትዮጵያ ሰዎች ከየቦታው ይነሳሳሉ፡፡ ይህችን ምድር ሊያሰክኗት፡፡ ዶማዎቻቸውን አንግበዋል፡፡ ብዕሮቻቸውን ሰድረዋል፡፡ ድልድዮቿን ሊጠግኑላት የተዘረጋው እጆቻቸው ወደ አፈር ማቡካቱ እና ማቅለጡ ብዕርን ወደ መደገኑ  ዞረዋል፡፡ ትንሳዔን ናፍቀዋልና! አንገታቸውን በገመድ አንጠልጥለው፤ እጃቸውን እየቆረጡ ብዕሮቻቸውን ይከለክሉዋቸዋል፡፡ ስለ እውነት ግን ይታሰራሉ-ይሰቃያሉ-ይሞታሉ- ስለ አርነት ይዘምራሉ- ነጻነትን ይስሳሉ- ትንሳዔ መናፈቃቸውን ከቶ አላቆሙም- በመንፈስ ናቸውና ትንሳኤን ያምናሉ-ትንሳኤ ናፋቂዎች ናቸው!! ትንሳኤ ናፋቂዎች…

 Coming soon....

No comments: