የአርበኛች ውለታ- ኢትዮጵያ ከ1928-1933
በኢትዮያ ታሪክ ውስጥ ወሳኝ
ምዕራፍ እና መንገድ ቀያሽ ከሆኑት የታሪክ ክስተቶች ውስጥ በዋነኝነት የሚጠቀሰው ይህ ጊዜ ነው፡፡ ከ1928-1933 ዓ.ም፡፡
የዘመናዊት ኢትዮጵያ መስራች
አጼ ቴዎድሮስ በእንግሊዝ ሲወድቅ፤ ናፒርን ግብር አብለተው፣ መንገድ እየመሩ ወዳጅነት መመስረት ያቀዱትን ሁለቱን የትግራይ እና
የጎጃም ንጉሶች ነበሩ፡፡ የሰሜኑ ንጉስ አጼ ዮሐንስ በርከት ያለ መሳሪያ ማግኘቱ በኋላ ላይ በሸዋው በአጼ ምኒሊክ ከጣልያን ጋር
ባገኘው መሳሪያ የታየ ነው፡፡ እርስ በእርስ ብንዋደድ ዋነኛው ጠላታችንን መግታት አያቅተንም፡፡ የጎጃሙም መሪ በኋላ ላይ አጼ ዮሐንስን
ከድተውታል፡፡
አጼ ዮሐንስ ጣልያንን መክተውት
ነበር፣ ግብጽን ድባቅ መትተዋል፡፡ በአፍሪካ አቻ የማይገኝለት የጦር መሪ ራስ አሉላ እንግዳ/አሉላ አባ ነጋ/ ኢትጵያዊ ክንዱን
ያሳየበት ነበር፡፡
አጼ ዮሐንስ መተማ ላይ በድርቡሽ
መስዋዕት ሲሆኑ፤ የምኒሊክ እና የጣልያን ስምምነት አድዋ ላይ ቢሻክርም
ከ40 ዓመታት በኋላ ላይ ግን የቂም በቀል ምላሽ ኢትጵዮያን በታሪኳ የማትዘነጋውን እልቂት የቀበረ ነው፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን
መርዝ ፈጃቸው፡፡ ጭንቅላት፣እግር፣እጅ ተቆረጠ፡፡ አንድ ባለመሆናችን ብልቶቻችን ተቆራረጡ፡፡ የመጀመሪያው መቆራረጥ አንገት ነው…
አሁንም አንድ ካልሆንን መቆራረጡ/መገነጣጠሉ/ የሚያቆም አይመስልም፡፡
ፋሺስቱ ቦኒቶ ሞሶሎኒ በወታደርነት
ዘመኑ የአድዋን ድል እያስታወሰ ይመስላል ወደ ስልጣን ያመራው፡፡ ጣልያን 40 ዓመት በሙሉ ቂሟን ለመበቀል ያልሰራችው መሳሪያ አልነበረም….
ኢትዮጵያ በ1928 ተወረረች፡፡
ንጉሱ አዲሱን የንግስና ዘመናቸውን
ሳያጣጥሙ /1923/ ከ5 ዓመታት በኋላ አገራቸው ተወረረች፤ ጥረት አደረጉ… ወደ እንግለዚ መሄድ ነበረባቸው… ለዓለም ሕዝብ ሁኔታውን
አሰሙ፡፡ ሊግ ኦፍ ኔሽን የአሁኑ UN የውሸት ተቋም መሆኑ ከጅምሩ ተመሰከረ… ዓለም ኢ-ፍትሃዊ መሆኗ ተመሰከረ፡፡
5 ዓመታትን በስደት እንግሊዝ
አገር ተቀመጡ….
በዚህ አምስት ዓመታት ቆይታ
ውስጥ ኢትጵያ ያለ ንጉስ ብትሆንም በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ ግን ‹‹ኢትዮጵያ›› ነበረችና ለጣልያን ኢትዮያን አንሰጥም በማለት ተቃውሟቸውን
አሰሙ…. አርበኞች ኢትዮጵያን ለመጠበቅ ተሰባሰቡ… በዱር በገደል፣ በባዶ እግር፣ ያለ እህል፣ ያለ ውሃ፣ ያለ ጥሪት ይህችን አገር
በቅኝ ግዛት መዝገብ ውስጥ ነጻ አገር እንድትሆን በየሜዳው ቀሩ፡፡ ከተማ ገብተው እንኳ ከተደላደለ ወንበር ላይ አልተቀመጡም፡፡
እኔ የማውቀው አያቴ እንኳ ሲሞት
ተቆራምቶ ጣራ ጣራውን እያየ ነበር ያሸለበው፡፡ ኢትዮያን ምን ብሏት ይሆን የሞተው… ሌፍ/ጀ ጃገማ ኬሎ እንኳ አሁን ልሳኑ በመጠኑም
ፈቅዶለት እየተናገረ ነው…. ያኔ የ15 ዓመት ወጣት አርበኛ ነበር፡፡ ዛሬ የ92 ዓመት አዛውንት አርበኛ… ይህንን ቀን የምን ቀን
ነው ብሎ ሲደነጋገር የሚሰማውን የተማረ ወጣት ቢያገኝ ምን እንደሚሰማው ህሊና ያለው ይወቀው፡፡
JAGEma KEllo At age of 15 |
በዚህ ወቅት ኢትዮጵያኖች/ከ1928-1933/
ኢትዮጵያኖች ከሶስት ተከፈሉ፡፡ አንዳንዶች ስደተኛ ሆኑ፣ አንዳንዶች አርበኛ ሲሆኑ አንዳንዶች ግን አስካሪ/ባንዳ ሆኑ… ለጣልያን
ተገዙ፡፡ አገራቸውን ካዱ… ህሊናቸውን ረገጡ… አርበኞች በባንዳዎች እየታደኑ ለፍርድ ቀረቡ… የሞሶሎኒን ምስል እንዲሳለሙ ተደረገ…
በየአደባባዩ ተሰቅለው ማስፈራራያ ሆኑ… በገመድ ታስረው በገሃድ ተጎተቱ….
ከሁሉም በላይ የንጉሱ ልጅ ባል
የነበረው እና አጼ ዮሐንስ የልጅ ልጅ ደጃዝማች ሃይለ ሥላሴ ጉግሳ ዋነኛ ለጣልያን ያደረ ባንዳ ሆነ… በርካታ ባንዳዎች ነበሩ፡፡ ከምን በላይ ባንዳነት አሳፋሪ ስብዕና ነው፡፡
አርበኛነት ሊያስተምረን የሚችል ስብዕና ነው፡፡ የአገርን ክብር ማዋረድ፣ የህዝብን ሀብት መዝረፍ፣ ማንነትን መካድ ባንዳነት ነው፡፡
አርበኛነት ሊያስተምረን የሚችል ስብዕና ነው፡፡ የአገርን ክብር ማዋረድ፣ የህዝብን ሀብት መዝረፍ፣ ማንነትን መካድ ባንዳነት ነው፡፡
Banadas Wearing style |
ዛሬ አርበኞችን የምንዘክርበት
ዕለት ነው፡፡ እንትና ይህን አደረገ፣ መድፍ ማረከ፣ አውሮፕላን ጣለ፣ ሌላም ሌላም እንድንል ሳይሆን ይህችን አገር እንድንጠብቅ፣
እርስ በርስ እንድንተባበር… በአንድነት ሁሉንም ማንበርከክ እንድንችል የምንማርበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ግን ዕለቱን
እየዘነነጋነው ነው… የእፉኝት ልጆ!!
ንጉስ ከ5 ዓመታት በኋላ በእንግሊዝ
ረዳትነት በሱዳን አድርገው ታዋቂውን ት/ቤት የተሰየመለት በጀነራል ዊንጉት ታጅበው ኦሜድላ ላይ ባንዴራቸውን ተከሉ፡፡ የጥቁር አንበሳ
ህብረት፣ የፈረንሳይ መንግስት፣ አርበኞች የዚህ ድል ቀኝ እጆች ነበሩ፡፡
ንጉሱ በሊግ ኦፍ ኔሽን የተናገሩት
ትንቢት ደረሰ፡፡ የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጣልያንን ክፉኛ ጎዳት፡፡ ኢትዮጵያን በዘር ከፋፍሏት የሄደው ጣልያን እና የእንግሊዝ
መሰሪ ሴራ አሁንም ኢትዮጰያን ከመከፋፈል ፖለቲካ አላዳናትም… አርበኞችን የምናስባቸው ተከፋፍለን አይደለም… አርበኞችን የምናስባቸው
የነጮች ጫማ ጠራጊ ሆነን አይደለም… አርበኞች ለዚህች አገር እንዲህ መውደቃቸው ትርጉሙ ሊመነዘር ይገባዋል… አርበኞች ይጮሃሉ!!
በዛን ወቅት አገሬን ህዝቤን
ብለው ለወደቁ፣ ለታሰሩ፣ ለተሰቀሉ እና ለአሞራ ለጅብ እንዲሁም በረሃብ ጥም ለሞቱ ማንኛውም ኢትጵያዊ ክብር ይሁን!!
Symbol Of Ethiopian Patriots... |
1 comment:
teru neger tsafk .... elebehen!
Post a Comment