May 10, 2014

እርጅና አበቃለት? እርጅናን የሚከላከል አዲስ ግኝት Forever young



እርጅና አበቃለት? እርጅናን የሚከላከል አዲስ ግኝት
Forever young የሚል አስተሳሰብ አለ፡፡ የMel Gibsonን ፊልም እና Jay-z በድጋሜ የዘፈነውን I wana be forever young ሙዚቃ ማስታወስ እንችላለን፡፡
ቴክኖሎጂ በሳይስን ጥላ ስር ሆኖ የጸረ-አምላክ ተከታዮች ሴራ ተደብልቆበት የሰውን ውብ አሰራር/ማንነት/ እንዲሁም አምላካዊ ዓላማ ለማፈራረስ ሌት ተቀን አይተኙም፡፡ የአፍሪካ ህጻናት ጤዛ እየላሱ በሚወስዱት የጤዛው ስር ፈርጥ /ዲያመንድ/ በርካታ ኢ-ፍትሃዊ እና ኢ-ተፈጥሮአዊ ሚዛኖች እየተመለከትን ነው! ሞትን ያመልኩታል የሕይወትን ምንዝርነት እና አለማዊ አርግማንን ግን ህያው ለማድረግ ይኳትናሉ!
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ደም ትልቅ ቦታ እና ዋጋ ያለው ሰው ልጅ ነፍስ መቀመጫ እና እግዚአብሔር ማንም ይህንን ደም እንዳይነካው በሚል ትዕዛዝ ለደም ትልቅ ክቡር ቦታ መስጠቱን በተደጋጋሚ እናነባለን፡፡ ደም የህይወት ምንጭ ነው፡፡ በአንዳንድ ሀይማኖት ተከታዮች ውስጥም ደም መለገስን አጥብቀው የሚቃወሙትን ያስታውሷል!
እዚህ ዘመናዎ ቴክኖሎጂ ላይ የምናየውም “አዲስ ደምን በመተካት እድሜን/እርጅናን/ ለመከላከል” የሚደረግ የምርምር ግኝት ነው፡፡ አዲስ የደም ህዋሳትን ወደ ሰው በማስገባት የሰውየውን እድሜ ከማርጀት መጠበቅ!! አስቡት አለም ሁሉ በወጣቶች  ስትሞላ፡፡
አለም በዋት ሰዎች  ብቻ መሞላቷ  አይደለም የቀረበው የጎንዮሽ ጉዳት /side effect/ ሳይንሳዊ መላምት፡፡ የልብ በሽታ ችግር ብቻም አይደለም የሚያስከትለው፡፡ “አዲስ ደም” ወደ ህዋሳቶቻችን ከገባ እና ወደ ጭንቅላት ሲሄድ መልዕክት አስተላላፊ ነርቮቻችንን ያነቃቃቸዋል፡፡ ይህም በአይጦች ተሞሯክል፡፡ የማስታወስ ችሎታንም በከፊል አሳድጎታል፡፡ ሆኖም ችግሩ እዚህ ላይ ነው፡፡ ጡንቻዎቻችን በከፍተኛ ሁኔታ ይጎዳሉ፡፡ deteriorate ያደርጋሉ፡፡ በእርጅና በኩል ከሚመጣው የመርሳት በሽታ አልዛይመር በተገላቢጦሽ እንዲከሰትም ያደርጋል፡፡ አለም ሁሉ በወጣት ትሞላለች፡ አንዳችም አይፈጸምም ማንም ከማንም ጋር አይተዋወቅም…. ሁሉም አይታወስም! ሁሉም አይታወቅም!! ካንሰር በእጅጉ ይስፋፋል፡ ህይወታችንንም “ቤንጃሚን በተንስ” የሚለውን ፊልም ከወዲሁ እንጋብዘዋለን!!
ይህንን የሚጠቁም ቃል ከቅዱሱ መጽሐፍ ይጠፋል ብላችሁ ነው?

ምስጋና፡- ወዳጄ ሰለሞን ዘውዴ በውብ ቋንቋ እንደምገልጸው በማመንህ እና ሀሳቡን ስላካፈልከን ባለህበት ሰላም ይቅረብህ!
source:-http://www.elle.com/news/beauty-makeup/young-blood-anti-aging-research?src=soc_fcbks

No comments: