Jan 27, 2014

ዘርዓይ ድረስ

ዘርዓይ ድረስ

ዘርዓይ ድረስ ትውልዱ ሐሴን ፤የሀገሩ ቀበሌ ዘሐጋ ዕድሜው 29 ዓመት ነው፡፡ የርእሰ ደብር ገብረ ጊዮርጊስ ደቀ መዝሙር ነበር፡፡ ያገሩን ቋንቋ ጽሕፈትና ንባብ ተምሮ ከጨረሰ በኋላ ከኢጣልያ ተማሪ ቤት ገብቶ የኢጣልያ ቋንቋ መማር ጀመረ፡፡ ትምህርቱንም እስኪያስፈልገው ድረስ ተምሮ  ከጨረሰ  በኋላ ከኒጣልያ ተማሪ ቤት ገብቶ የኢጣልያ ቋንቋ መማር ጀምረ፡፡ ትምህርቱንም እስኪያስፈልገው ድረስ ተምሮ ሲያበቃ መጀመሪያ አስመራ ፖስታ ቤት ሥራ ይዞ ይሰራ ነበር፡፡
ኢትዮጵያም በጣልያን ተወረረች፡፡
በተወረረች በ3ኛው ዓመት በ1930 በአስተርጓሚነት ወደ ኢጣልያ  ሄደ፡፡ አንድ ጣልያናዊውም የኢትዮጵያን ጥንታዊ ጦር መሳርያ ይዞለት እንዲሄድ ልኮት ነበር፡፡
በጣልያን አገር እያለም የፋሺስት ጣልያን ወታደሮች በኢትዮጵያ አንበሳ ላይ ሲያፌዙ እና ሲያላግጡ አይቶ አዘነ፡፡ ከዚያም አልፎ በዘርዓይ ድረስ ኢትጵያዊነት ማሾፍ ጀመሩ፡፡ በንቀትም ተመለከቱት፡፡ ዘርዓይ የያዘውን ጋሻ እና ጦርም ለመቀማት ሲጠጋ ዘርዓይ የዛን ቀለብላባ አንገት ቀላው፡፡ በሮማ አደባባይ የነበሩ ኢጣልያኖች ላይም ከፍተኛ ጉዳት አደረሰ፡፡ ከዛም በስድስት ጥይት ተመትቶ ቆሰለ፡፡ ተያዘ፡፡ ለፍርድም ቀረበ፡፡ የጌታቸው ካሳን “ኢትዮጵያን አትንኳት” የሚለውን ሙዚቃ ተጋብዛችሃል፡፡

ምንጭ፡- “ኤርትራዊ ኩራቴ ሙሉ ነጻነቴ” ከግራዝማች አስገዶም ረዳ፡፡

No comments: