Nov 24, 2013

The barefoot Emperor



 ዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስን  ማን ይሏቸዋል?

   አጼ ቴዎድሮስ ቁጡ፣ ጦረኛ፣ ጦርነት ብቻ የሚወዱ፣ እብሪተኛ፣ ፍርድ የማይሰጡ፣ ገዳይ፣ ከስልጣኔ ይልቅ የጠበንጃ ብዛትን የሚወዱ ተደርገው ሲወደሱ ከሰማን ሰነባብተናል፡፡
በተለይ የወያኔው አምበል ከአንዲት የ3ወር ጥምቅ ከሆነች “ጋዜጠኛ” ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ በጆሯችን ሰምተናል፡፡ ተገርመናል! ተደምቀናል! አዝነናል! ጋዜጠኛ ሲባል በብዙ መረጃዎች ተመርኩዞ አፋጥጦ የሚጠይቅ፤ ለሚነሱ ጥያቄዎች እና መልሶች ትክክለኛ መረጃን ለማስተላለፍ የተገደደ ባለሙያ ነው! ስልጣን አይመክተውም፣ ገንዘብ አይገዛውም፣ ሰይፍ አያስፈራውም፣ እውቀት አያንሰውም፣ ጥበብ አያጣውም… ይህ ካልሆነ ግን ሙያው ተጭበርብሯል፡፡ ስንቱ የተጭበረበረባት አገር አለችን?
እርስዎ ታሪክን አጥብቀው የሚፈልጉ ከሆነ፣ ትክልለኛ እና የተቀራረበ መረጃ ለማወቅ ከፈለጉ እነ ሰተርን፣ ራሰም እና ሄነሪ ብላንክ የጻፏቸውን መጽሐፍት ብናነብ፤ የጳውሎስ ኞኞን ፣ የአቤ ጉበኛን፣ የፊሊፕ ማርድሰንን፣ የገሪማ ታፈረን፣ የሪቻርድ ፓንክረስትን፣ የአለቃ ዘነብን፣ የአለቃ ለማን፣ የብርሀኑ ዘሪሁንን መጽሐፍት ቢያነቡ የተሻለ መረጃ ያገኛሉ፡፡ የእነዚህን ጥንቅር ከፈለጉ አስተያየትዎን ይላኩልን….
ባጭሩ፡-
አጼ ቴዎድሮስ የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፈር ቀዳጅ ናቸው፡፡
ከአውሮፓውያን የሀይማኖት ስብከትን ሳይሆን ስልጣኔያቸውን አጥብቀው ይፈልጉ ነበር፡፡
የባላንጣቸውን /የንጉስ ልጅ/ የሆነቸውን ተዋበችን አግብተው በፍቅር ይዱዋቸው ነበር፡፡
የመንገድ ስራ መሰረትን ጀምረው አብረው ድንጋይ ሲፈልጡ እና ሲቆፈርሩም ነበር ቺፍ ኢንዲነር “የህዳሰው መሐንዲስ” ይሏቸዋል፡፡
ቲማቲም በእረስሳቸው ዘመን እንደገባም ይነገራል፡፡
የዘመነ መሳፍንት መዳከም እና የአሀዳዊ መንግስት መመስረትን፣ አንድነመትን አጥብቀው የሚፈልጉ ነበሩ፡፡
ኢየሩሳሌምን ከቱርኮች የማስለቀቅ ራዕይ ነበራቸው፡፡
ባለ ደመወዝ ወታደር፣ በአለባበስ የተደራጀ፣በስራ የሚያምን ኢትዮጵየዊን ለመፍጠር የተጉ፡፡
በአንግሊዞችም ሆነ በራቻሰው ወታደር የተፈሩ፡፡
ከ17 ጊዜ በላይ መገደል ሙከራ የተደረገባቸው፡፡
ባዶ እግራቸውን የነበሩ፣ የግል ሕይወታቸው የተንደላቀቀ እና ራስ ወዳድነታቸው ጎልቶ የታየ፡፡
ዘመናዊ የባህር ሃይል መስመር ለመዘርጋት የሞከሩ፡፡
የጋፋት ብረት ማቅለጫ እና ጠበንጃ መምረቻን የዘረጉ…..
የትዳር ሁኔታን ለማስተካለል፡፡
የቤተ-መጽሐፍት ጅማሮ፡፡ 

“ብዙ…. "
ይልቁንም ባለታሪክን ከመውቀስ በእኚህ ሰው የተመሰረተውን አንድነት እና ታላቅነት እንደ ማነቃቂያ ወስደን፤ የተዘረፉብንን ቅርሶች ለማስመለስ ብንረባረብ እና የጠፋብንን የአገራዊነት ስሜት ብንፈልግ ይበጀኛል! ካለበለዚያ የመርዛማዎቹ ቄሳሮች "በሽተኛ" ሆነን መኖራችን ነው!!

No comments: