ሜዱሳ
ግሪኮች የሚያመልኳቸው በርካታ አማልክት አሏቸው፡፡ በአፈታሪክ የሚዘከሩ ፤ በተለያዩ ስያሜዎች ተሰይመውም የሚጠሩ፡፡ የሚመለኩም!
እነዚህን በርካታ አማልክት በአሁኑ
ሰዓት በሚዲያው በተለይ በሙዚቃው እና “በፊልም ኢንደስትሪዎች” በታዋቂ እና “ዝነኛ” በሆኑት “ፈርጦች” ሲተዋወቁ፣ ሲሰየሙ እንዲሁም
ሲዘፈንላቸወም እናያለን፡፡ ባለፈው የባለ አንድ አይንን አርማ ምንነትን በመጠኑም ስንቃኝ ለመጥቀስ ሞክረናል፡፡ http://tesfabelaynehh.blogspot.com/2013/10/one-eye-symbol.html
አሁን ደግሞ በጣም ካስገረሙኝ የአማልክት ስያሜ አንዱ የሆነውን ሜዱሳን ላስተዋውቃችሁ፡፡
አሁን ደግሞ በጣም ካስገረሙኝ የአማልክት ስያሜ አንዱ የሆነውን ሜዱሳን ላስተዋውቃችሁ፡፡
“ሜዱሳ” በምስል፡-
ሜዱሳን ከክርስቶስ ልደት በፊት የነበረች ጭራቅ መሰል ባሕርያ ያላት እጅግ
“የሚያምር” ጸጉር የነበራት በጾታ ሴት የሰው ፍጡር ነበረች፡፡ እንደ አፈታሪኩ አገላለጽ “ሜዱሳ” የነበራትን የሚያምር ጸጉር ወደ
ተናዳፊ እባቦች እንደተለወጠባት ይነገራል፡፡ ይህ ጽሑፍ ስለአማልክቶች ምንነት፤ አስከፊነት እና ታሪክ ለማሳወቅ የቀረበ አይደለም፡፡
ማምለክ የአመለካከት ውሳኔ ነው በሚለው አመክንዮ ሄደን ከተግባባን ስለአማልክቶች ምንነት ወደ የግል አስተሳስብ እና ፍላጎት በመተው
የዚህ ጽሑፍ አላማ ወደ ሆነው ጭብጥ እናልፋልን፡፡
“ሪሃና”ን የማያውቅ የለም፡፡
በአሁኑ ሰዓት አለም እየሰማቸው እና እያወቃቸው ካሉ “ፈርጦች” ውስጥ “ቀንደኛዋ” ናት፡፡ “የኢሉሚናቲ ንግስት” /illuminati
Princes /ነኝ ስትልም ታይታለች፡፡
በአንድ የሙዚቃ ክሊፕ ውስጥ የተወሰደውን ምስል ይመልክቱ፡፡
በያዝነው አመት ደግሞ ሪሃና
የሜዱሳን ምስል ተላብሳ በአንድ የእንግሊዝ መጽሔት ብቅ አለች፡፡ እንዚህ ፈርጦች ከሚታወቁበት የአውሬው ልዩ ፍቅር እና ቁርኝትን በሚገባ የታየበትን ምስል ይመልከቱ፡፡
የዚችህን ሙዚቃ እያዳመጡ ምን ያህል ተመስጠዋል? ምን ያህል ተነድፈዋል?
No comments:
Post a Comment