ሳይታክቱም ዘወትር ሊጸልዩ እንዲገባቸው
የሚል ምሳሌን ነገራቸው እንዲህ ሲል፡-
በአንዲት ከተማ እግዚአብሔርን
የማይፈራ ሰውንም የማያፍር አንድ ዳኛ ነበረ፡፡ በዚያችም ከተማ አንዲት መበለት ነበረች፡፡ ወደ እርሱም እየመጣች፡- ከባላጋራዬ
ፍረድልኝ ትለው ነበር፡፡ አያሌ ቀንም አልወደደም፤ ከዚህ በኋላ ግን በልቡ፡- ምንም እግዚአብሔርን ባልፈራ ሰውንም ባላፍር ይህች
መበለትስ ለምታደክመኝ ሁልጊዜም እየመጣች እንዳታውከኝ እፈርድላታለሁ አለ፡፡
ጌታም አለ ፡-
"ዓመፀኛው ዳኛ
ያለውን ስሙ፡፡ እግዚአብሔር እንኪያስ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ለሚታገሳቸውም ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን? እላችኋለሁ ፈጥኖ
ይፈርድላቸዋል፡፡ ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆን?"
ሉቃሰ 18፡1-8
No comments:
Post a Comment