Nov 6, 2013

"የግንቦት ስላሴ"

                         “የግንቦት ስላሴ”
አንዳንድ ሰዎች አሉ...!

በግንቦት ሥላሴ ጠላ የሚጠምቁ
ጌሾውን፣ እህሉን በልብ የሚያደቁ፡፡
አንዳንድ ሰዎች አሉ
መናፍቃን ሆነው ቀኖና ደምሳሾች
ባህልን ትውፊትን ውድቀትን አሳሾች…
አሉ፡-
በግንቦት ስላሴ ሰክረው የሚጣሉ
የግንቦት ስላሴን ክብር የሚያቃሉ…
አሉ…!
የሥላሴን ፍጥረት አውሬ የሚያደርጉ
ከሰውነት ተርታ ወጥተው የሚያዋጉ፡፡
አሉ…!
                       በፍጥረት አንድነት ሰላም የማያምኑ
                       በመንፈስ እርዛት ለጦር የመነኑ
                       ሰውን አሰቃይተው ረግጠው የገዙ
                       ፍቅርን አመንምነው ቂም በቀል ያስያዙ
                       አሉ…!
                       በግንቦት ስላሴ ሰክረው የሚጣሉ
                       የግንቦት ስላሴን ክብር የሚያቃሉ…
                       አሉ…!
               *ኢትዮጵያ ሆይ ደምሽ እንዳይፈስ፤ እንባሽ እንዳይዘንብ! ሰላምሽ እንዳይደፈርስ፤ ሰላም!

1 comment:

Unknown said...

ስላረካከሱት ግንቦት ሃያ እያሉ፣
በግንቦት ስላሴ ሰዎች ተማማሉ።
በግንቦት ስላሴ ሥራ ተሰማሩ፣
የግንቦት ስላሴን ክብር ሊያሰክብሩ።
ከሰውነት በታች ስለ ተዋረዱ፣
ለነፃነታቸው ጫካ የወረዱ፣
በግንቦት ስላሴ እንዳይታረዱ፣
መንገድ የዘጋዉን ግንዱን ቢያስወግዱ፣
እንደምን ይባላል ቅኖና የካዱ ?
በግንቦት ስላሴ የተጠነሰሱ፣
በቅኖና ታሰረው የማይበሰብሱ፣
አሻፈረን ያሉ አሉ የተነሱ።
ሕዝብንና ፍቅርን ንቀው ለረገጡ፣
የግንቦት ጥንስሶች ይሄውና መጡ።