ይህንን ጥያቄ ለዓመታት አንስቼዋለኹ፡፡ ከወዳጆቼ ጋርም ተነጋግሬበታለሁ፡፡ “የሚልየኔሙ”
ጀግና ምናምን ተብሎ የተነገረለት አባ ታጠቅ ነው፡፡ ነግር ግን አባ ታጠቅ በደቡብ የኢትዮጵያ ክፍል ጥሩ ስም የለውም፡፡ ሚኒሊክም
ያው፡፡ መለስ ዜናዊን የመረጠም ነበር፡፡
እንደ ኢትዮጵያ ላሉ አገራት አንድ ጀግና መምረጥ እጅግ ይከብዳል፡፡ ምክንያቱም በጎሳ
፣ በሃይማኖት እና በቋንቋ ለተከፋፈለች እና አንዱ በአንዱ የበላይነቱን
ለማሳየት በተቆራረጡበት እና በተዋጉበት አገር በአንድ ድምጽ የምንስማማበት ጀግና ማግኘት ከምላስ ላይ ጠጉር እንደመፈለግ ሆኖብኛል፡፡
ሰፊ እና ጥልቅ ሃሳብ/ውይይት የሚፈልግ ርዕስ ነው! ግራኝ አህመድም እኮ ጀግና ነው! ዮዲትም! ኢትዮጵያ ውስጥ እኮ ለዮዲት የክብር
ወንበር የተቀመጠላትን ቦታ ጎብኝቻለሁ፡፡ ግራኝ አህመድም ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች ታሪክ ሰሪ ጀግና ነው! ስለዚህ መሪ ጀግናን በዚህች
አገር ለማግኜት እንቸገራለን፡፡
የኋላ ታሪካችንን ያላጠኑ ሰዎች መለስ ዜናዊን እንደ ጀግና አድርገው መለስ ሰጥተውኛል፡፡
ነገርግን እነ አጼ የሐንስ፣ ተክለጊዮርጊስ፣ ሚኒልክ፣ ቀ.ኃ.ሥ፣ መንግስቱ እና መለስ የቆሙባትን መሬት ለአንድነቷ መሰረት የሆነላት
መይሳው ካሳ መሆኑን የሚክድ ኢትዮጵያዊ ያለ አይመስለኝም! ግን ከወሎዋ ንግስት ወርቂት ጋር በነበረው አለመግባባት ኦሮሞዎች ላይ
ከፍተኛ ልዩነት ተፈጥሮ ስለነበር በደቡቡ የነበረው የኢትዮጰያ ህዝብ ካሳን እንደ ጀግና አድርጎ ለመቀበል ይከብደዋል፡፡
ለኔ ጀግና ግን ወደ ኋላ ታሪክ ሳይመልሰን አይቀርም፡፡ ዮቶር! የሙሴ አማት! ለእስራኤል
ህዝብ ስልጣኔ መሰረት፣ የህዝብ አስተዳደር ትምህርትን የሰጠ፣ ሙሴን ያሰለጠነ ኢትዮጵያዊ ዮቶር ነው፡፡
ከዛም ንግስተ ሳባ
ከዛማ ህንደኬ
ከዛም ካሌብ
ከዛም ላሊበላ
ከዛም /ተክለ ሃይማኖት የዛጔን ስርወ መንገስት ወደ
ሸዋው ያስታረቀ/
ከዛም ዘርዐ ያእቆብ
ከዛም ገላውዲዎስ
ከዛም ፋሲለደስ
ከዛም ታጠቅ
ከዛም ዮሐንስ
ከዛም ሚኒሊክ
ከዛም ኃይለስላሴ…
ለኔ ከመሪዎች እነዚህ ለዕጩነት ቢቀርቡ የምመርጠው ይኖረኛል፡፡ ሆኖም ከግን ሃይማኖቴ እና ቋንቋዬ ተጽዕኖ እንዳደረገብኝ ሳልደብቅ አላልፍም፡፡
ታሪክን ግን ከእነዚህ ነገሮች
ውጭ ሆነን መመልከት አለብን! ይህ ከሆነ ጀግና ማግኘት አይከብደንም፡፡ ጀግናማ ሞልቷል!
ንግስት እሌኒ፣ ተዋበች/ የአጼ
ቴዎድሮስ ሚስት/ ጣይቱ የተለየ ስፍራ አላቸው፡፡
መሪም ሚስትም የተጠቀሰላቸው
ቴዎድሮስ እና ሚኒልክን አገኘን፡፡ ከሁለቱ ማንን ልምረጥ?
ሚኒልክን ደቡቡን ሲያቀና እነ
ባላቻ ሳፎን፣ ፊታውራሪ ሐብተጊዮርጊስ ቢነግዴን አና ሌሎችን በማሳመን/በማሸነፍ/ አንድነትን ለማጠናከር ችሏል፡፡ ለነጮችም ዕፍረት
ለጥቁር ህዝብም ኩራት የሆነውን አድዋን ያገኘነው በዚህ አንድነት ነበር! የመረብ ምላሽን እና የጅቡቲን ነገር እያነሱ ታሪክን ለማጣመመም
የሚሞክሩ አሉና ምን መልስ አለህ ብትሉኝ
አሁንስ ስልጣን ላይ ያሉት መረብ
ምልሽን መች ፈቱት! ይሆናል መልሴ፡፡
እነ ፊታውራሪ ገብርዬ እነ አሉላ
አባ ነጋ፣ ስንት አርበኞች/ አብርሃ ደቦጭ አና ሞገስ አሰግዶም/ ፣ ራስ አበበ አረጋይ ኧረ ስንቱ…. ጀግና በበዛበት ሀገር ሁላችንንም
የሚያስማማ አንድ ጀግና ማግኘት ሲከብድ እንዴት ያሳዝናል?
ማን ይን ጀግና?
ብዬ ሳሰላስል… ሳፈላልግ….
ክርስቶስ ብቻ ሆኖልኝ አረፈ!
2 comments:
እዉነት ነዉ አንድ ጀግና ማግኘት ይከብዳል . . . ምክንያቱም ለቁጥር ሚያታክቱ በየዘመናቱና ክፍላተ ሀገራቱ የሚነሱ ጀግኖች አሉን . . . ጠበን አሰብንም እንደ ኢትዮጲያዊ አሰብን ቁም ነገሩ ጀግና የምታበቅል ሀገር ልጀች ነን . . . ካንተ ጋር የምቃረነዉ ግን ለምን አንድ እንዲኖረን እንደፈለክ ግልጥ ስላልሆነልኝ ነዉ . . . አንድ የሚያስማማን ማግኘቱስ ጥቅሙ ምኑ ላይ ነዉ . . . በመሰረቱ ይህ በራሱ መጣዉ አሁን ባለዉ ታሪክን አጣሞ የማሳየት ተንኮለኛ እሳቤ ነዉ . . . የአክሱም ሀዉልት ለወላይታ ምኑ ነዉ የሚል ጥራዝ ነጠቅ በሚመራዉና ጠፍጥፎ በሰራዉ ስርዓት ዉስጥ እንደ ቦይ ዉሃ እየፈሰስንለት ነዉ . . . የምንስማማባቸዉ ነገሮችን ለማጥፋት ቆርጠዉ በዓላማ የሚንቀሳቀሱ ጥቂት ጠባብ ጭንቅላቶች በሚያናፍሱት አሉባልታ እን የምኒልክን ጀግንነት ማቃለል ሊገርምህ አይገባም . . . ምክንያቱም እነዚህ የእፉኝት ልጆች ጠባብ ጭንቅላታቸዉ ሊገነዘብላቸዉ ያልቻለዉ ግዙፍ ሀቅ እንኳን የኛ የአፍሪቃ ጀግና መሆናቸዉን ነዉ . . . ኦሮሞ በምኒልክ ተገፋ ትግሬዉ ምኒልክን አይወድም የሚባል እንቶ ፈንቶ የሚያናፍሱ ሰዎች ምኒልክ ባቀኗት ሀገር ዛሬ በነፃነት ባልኖሩ ነበር ዛሬ ጣላንኛ ባወራን ነበር ሌላም ሌላም . . . እና በዚህ አካሄድ እሳቸዉ ብቻ ሳይሆኑ ብዙ አያሌ ጀግኖች በጋራ ማወደስ የሚያስችሉን ትንተናዋች በአመክንዮ ማቅረብ ይቻላል . . . የጠባብ አስተሳሰብ ዉጤት የሆኑትን የታሪክ ጉድለት ያለባቸዉን ሃሳቦች እያነሳን እየተብሰለሰልን የምናናፍስ ከሆነ ግን አደጋ አለዉ . . . ሌላዉ ክርስቶስ እዚህ እንደ ጀግና ማንሳትህ ነዉ ነገሩ ባልከፋ ግን እያወራን ያለነዉ ስለ ሰዉ ልጆች ታሪክ ሊያዉም ስለ ኢትዮጲያ ነዉ ታዲያ እየሱስን እዚህ ምን አመጣዉ . . . እሱንስ ከማን አወዳድረን ነዉ ጀግና ለማለት የደፈርነዉ? . . . እሱ የጀግና ፈጣሪ እንጂ በራሱ ጀግና አይደለም!
ለማንኛዉም ይመችህ በርታ!
ወዳጄ እጅጉን ደስ አለኝ፡፡ የተፈለገውም ይህ ነበር፡፡ ያለንን ሃሳብ በነጻነት እንድንለዋወጥ እና የተሸለውን አስተሳሰብ ይዘን ተሸለን ለመገኘት፡፡
በቅድሚያ አንድ ጀግና ለምን ተፈለገ የተባለበት ምክንያት መልስ ከምን መዓዘን እንደተጠየቀ ለማመልከት ልሞከር፡፡ አንድ ሀገር አንድ ጀግና ብቻ ሊኖራት አይችልም፡፡ ያውም እንደኢትዮጵያ ላለች አገር፡፡ የጀግና ባለሀብቶች ነን! ክብር ለጀግኖቻችን፡፡
ሆኖም አዲሱ ትውልድ ካለፈው ትውልድ ተሽሎ መገኘት አለበት! በታሪክ ውስጥ የተከሰቱትን ታሪካዊ ክስተቶች እያጠና፣ እየተማረባቸው፣ እየተወያየባቸው፣ እየተመካከረባቸው ተሻሽሎ ቀጣዩን ትውልድ የበለጠ ሊያስተካክል ይገባል፡፡ ስለዚህ አንድ ጀግና መፈለግ ማለት አንድነታችንን መፈለግ ማለት ነው! አንድ ጀግና መፈለግ ማለት ብሔራዊነትን ማጠናከር ማለት ነው፡፡ በታሪክ ተጎዳን የሚሉት ከታሪክ መማር እንዳለባቸው ሊያሳዩን ይገባል፡፡ በታሪክ ደግሞ መታበይ እና መኩራራት ብቻውን ፋይዳ የለውም ታሪክ መስራት ነው የሚቀድመው! ስለዚህ ትግሬዎች ሚኒልክን የሚጠሉበትን ምክንያት ካላቸው ያቅርቡ እና እንወያይበት፣ ብዙውን ጊዜ ለውይይትም የቀረብ ሃሳብ ነው- መጨረሻው ጥላቻ እና ቂም ብቻ ነው! ኦሮሞዎችም እንደዚሁ፡፡
ነገር ግን እኔ በ “ብሔሬ” ብቻ ተንቆራጥጬ ታሪክን ለማጣመም እና ወገናዊ የምሆን ከሆነ ብሔራዊነትን ለማምጣት የሚከብድ ይሆናል፡፡ ተጎዳቻለሁ/ተበድያለሁ/ የሚለውም ክፍል ታሪክን ማዬት ያለበት ከጊዜው አኳያ እንጂ ከአሁኑ መነጽር መሆን የለበትም፡፡ አሉላ አባ ነጋ እኮ ለምንልክ ወግኖ አገር ዳር ድንበርን አስከብሯል፡፡ በጊዜው የነበሩትን “ባንዳዎች” ያስመለሰ እና ያግባባ የትግሬው አሉላ ነበር፡፡ ይህ ነው አንድነት ማለት! ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስም ቦሩ ሜዳ ላይ የመሰከሩትን አንዘነጋም፡፡
ስለዚህ አንድ ጀግና በምንፈለግበት ጊዜ ሁላችንም በፍቅር፣ በመተሳሰብ፣ በመከባበር እና በአንድነት ሆነን መሆን አለበት፡፡ የፍቅር፣ የመከባበር፣ የመተሳሰብ እና የአንድነት ንጉስ ደግሞ ለኔ ክርስቶስ ነው! ክርስቶስን ይዘን ስንወያይ፣ እውነትን ይዘን ስንመካከር ሁሉም ይሰምራል፡፡ ክርሶስትም እኮ ሰው ነበር፡፡ ከዛሬ 2000 ዓመታት በፊት የነበረ ልክ አንደማንኛውም ሰው ምድርን የረገጠ፣ ያስተማረ፣ የመራ ነበር፡፡ ስለዚህ በሰውነቱ እናውቀዋለን፡፡ እሱን ስናውቅ ደገም ሌሎችን ማወቅ አይከብደንም፡፡ ሁሉም ግን ስለፍቅር ይሁን -አምሃ ወንድሜ!
በዚሁ ቀጥል፡፡ ግልጽ ካልሆነልህ እናከህ አሁንም ለመወያየት ፈቃደኛ ነኝ፡፡ የታሪክ አጣማሚዎችን ተዋቸው፣ ከአባታቸው ዲያቢሎስ ነው፡፡ እኛ ግን እንወያይ!
እግዚአብሔር ይስጥልኝ!
Post a Comment