Feb 5, 2013

አንተ ማነህ? sub liminal message and its influenece



አንተ ማነህ?
ሰዎች የጭንቅላት እና የማንነታቸው ትስስር ግንኙነትና አሰለጣጠን ባለመገንዘባቸው ስሜት ከማገናዘብ የቀደመ ሆ ሲሉ ሆ የተባለ ሲነዳ እንደሚውል የከብት መንጋ ሲሆኑ ካየን ቆየን፡፡
ይህን ሀሳብ ለማቅረብ የገፋፋኝ አንድ ገጠመኝ ነበር፡፡ ከአንድ ወዳጄ ጋር ስለ Subliminal Message በሚለው ርዕስ ስር በተያያዙ ጉዳዮች ስንወያይ የሰው ልጅ ምን ያህል ባላሰበው እና ባላቀደው አልፎም ባልፈለገው እና ባልተፈቀደለት መንገድ እየተመራ መሆኑን የሚያሳይ መረጃ በማግኘቱ ያማከረኝን ነገር ብነግራችሁ ይገርማል፡፡ ከመገረምም አልፎ ምን ያህል ያለ ፍላጎት እየተነዳን ነው ብለን ለረዥም ጊዜ ልናስብ ስለሚያደርግ ይከታተሉኝ፡፡
በአሜሪካ ከሚደረጉ የሚዲያ ማስታወቂያዎች በተለይ ኮሜርሻል አድቨርታይዝመንቶች ውስጥ አብዛኛዎቹ በውስጣቸው Subliminal Message ይዘዋል፡፡ ይህም ማለት በግልጽ የማናያቸው ነገር ግን ውስጥ ለውስጥ መልዕክትን ማስተላለፍ የሚለውን ሀሳብ ይገልጸዋል፡፡ እኛ የምናየው ምናልባት ኮካ ኮላ መጠጥ ማስታወቂያ ሊሆን ይችላል፡፡ እያየን ያለነው የቢራ ወይንም የአልኮል መጠጦችን፣ የሽቶ ማስታወቂያዎችን ሊሆን ይችላል ሌላም ሌላም ነገር ግን በውስጣቸው አገናዛቢው አእምሮአችን ባላገናዘበው መልኩ የዘረኝነት የፖለቲካና የወሲብ መልዕክቶች እንዲሁም የተለያዩ መልዕክቶች ይተላለፋሉ፡፡ የሚገርመው ይህንን ሁሉ የሚመዘግበው Subconscious mind የሚባለው የአይምሮ ክፍል በመሆኑ ይህ የአይምሮ ክፍል ደግሞ የማመዛዘን (Reasoning) ተግባር በተፈጥሮ ማከናወን ስለማይችል መረጃው እንደ ዳታ ተቀማጭ ይሆናል በቀላሉ ለመረዳት ይህንን አስገራሚ አጋጣሚ ልብ ይበሉ፡፡
በአንድ ወቅት በአንድ የሲኒማ ቤት ውስጥ የሚገኙ ታዳሚያን በእቅዳቸው እና በፍላጎታቸው መሰረት የእረፍት ጊዜያቸውን ፊልም በማየት ወደዚያው ያቀናሉ፡፡ የሲኒማ ቤቱ ወንበሮች ሙሉ በሙሉ በተመልካች ሞልቷል፡፡ 5% የሚሆኑት ታዳሚያን እንደተለመደው በእቅድና በፍላጎታቸው መሰረት ለስላሳ መጠጥና ፈንድሻ ይዘው በመግባ ፊልሙ እስኪጀምር ድረስ ያጣጥማሉ፡፡ በዚህ ወቅት ነበር ከፍተኛው ድብቅ ሴራ የተካሄደው፡፡ ከማይክሮ ሰከንድ ባልሞላ ፈጣን የጊዜ ቅጽበት ውስጥ (Drink Coca cola eat popcorn) የሚል ማንም ሊያነበው በማይችለው ፍጥነት ተላለፈ፡፡ ማንም የተመለከተው እና የተገነዘበው ባለመኖሩ ከሰከንድ ሽርፍራፊ ፍጥነት በመተላለፉ ማንም ሰው ሊመለከተው አልተቻለውም ነበር፡፡ ሆኖም ሰብ ኮንሽየስ ማይንዳችን መዝግቦት አልፏል፡፡ ማመዛዘን ስለማይችል ግን ምንም አይነት ውሳኔ መስጠት አይችልም፡፡ ጉዱ እዚህ ላይ ነው አንዳንዴ ይህ የአይምሮ ክፍል የመዘገበውን ዳታ ወደ ኮንሽየስ ማይንድ በማድረስ ይህኛው የአይምሮ ክፍል መልክዕቱን ተቀብሎ አድርግ ስለሚለው በዚህ ወቅት 40%የሚሆን ተመልካች ወጥቶ ኮካ ኮላ እና ፈንዲሻ ለመግዛት ተገደደ፡፡ እንግዲህ ተመልካቹ ፈልጎት እና አቅዶት ሳይሆን የማይገነዘበው የአይምሮ ክፍል በመዘገበው ዳታ መሰረት ያለ ፍላጎት የተገዛ በመሆኑ ነው፡፡ ይህም ማለት የምናያቸው ማስታወቂያዎች ፊልሞች ሙዚቃዎች በውስጥ ለውስጥ በሚተላለፍ መልዕክት ምን ያክል ተጽእኖ እንዳላቸው ለመገንዘብ ነው፡፡ በአሁን ሰዓት ያለው ሚዲያ የSubliminal Message ሰልፎች ጋጋታ ነው፡፡ ኮሜርሻል በመሆናቸው ሳንወድ በግድ የዛ ሀሳብ ወይንም ሸቀጥ ሱሰኛ እንዲሁም ተገዥ እንድንሆን ያደርጉናል፡፡ ስራቸው ትክክለኛ ገንዘብ ማግኘት መሆኑን ሳንዘነጋ፡፡ አንተ (ማንነትና የጭንቅላትህ ሁኔታ) አንድ ስብዕናን ይፈጥሩልሀል፡፡ ልብ  ህሊና ልቦና ተብለው በአጠቃላይ ከአንድ በላይ በሆኑ ስብስቦች አንተነትህን /አንቺነትሽን/ የሚወክሉ የግንባታ ክፍሎች አሉ፡፡ እኛ ለአይምሮ የፈለግነውን ነገር እናዘዋለን፡፡ ለምሳሌ መብላት ስንፈልግ መብላት መጠጣት መራመድ መተኛት መናገር ወዘተ ትልቁ ችግር እኛ የምናዘው ድርጊት አይምሮአችን በማመዛዘን ከተፈቀደለት የአካባቢ ሞራል እና የግል ተጽእኖ በመመርኮዝ አእምሮ አድርግ ያለውን ከሶስቱ መሰረታዊ የግንባታ እቃዎች ጋር በመተባበር ውሳኔ ላይ ይደርሳል፡፡ ይህ የሰው ልጅን ግሩም ከሚያስብሉት ስጦታዎች የሚጠቀስ ልዩ ፀጋ ነው፡፡ ማጥናት ብንፈልግ አእምሮን በማዘዝ ፍላጎትንና ቆራጥነትን በመያዝ እናጠናለን፡፡ አንዳንድ ሰዎች በተለያዩ እጾች ወይም መድሃኒቶች በቡና በኮካ በጫትና በተለያዩ ታብሌቶች በመታገዝ ሊቆዩ እና የተፈለገውን ተግባር ሊያከናውኑ ይችሉ ይሆናል፡፡ መተኛት ስንፈልግ ግን በጦርነት እና በመከራ በመሆኑ ድካምና ህመም እንዲሁም አእመሮአችንን እናስጨንቃለን፡፡ አእምሮአችንም እንደዚህ አይነት ተግባር በሚደጋግምበት ጊዜ የተለያዩ እጾች ሲሸወድ ይለምድና በውስጣቸው በያዙት ኬሚካል ጋር በመዳመር ሱስ ይይዘናል፡፡ አይምሮአችንም ውድ የሆኑ ህዋሳቶቹ እየደከሙ ከአቅም በላይ በመወጠርና በመሰብሰብ ከፍተኛ ጉዳት ያጋጥመዋል፡፡ አይምሮአችን ህዋሳቶቹን ራሳቸውን እያደሱ ጤናማ እንዲሆኑ በቂ የሆነ እረፍት እንቅልፍ የማይጎዱ ኬሚካሎች ማግኘት አለበት፡፡ በአሁን ሰዓት ግን በአለማችን ያለው ነገር ይህን እንድናደርግ አያግዘንም፡፡ በትዕዛዝ እንድንኖር እንድናገናዝብ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎችን የሚወስደው ከተፈጥሮው ከአካባቢ ከትምህርት እና በማንበብ በሚገኝ እርዳታ ሲሆን ይህንን በማድረግ የሚኖር ሰው ኢሞሽናሊቲ (ስሜታዊ) የሚባለው ነገር ከኢንቴሌክቹዋሊቲ (ሃሳባዊ) ከሚባለው የሰው አይነት ስለሚከተል በስሜት ከመነዳት ይልቅ አገናዝቦ ተረድቶ አመዛዝኖ ውሳኔ ላይ ለመደረስ የሚችል ሰው እንድንሆን ያግዘናል፡፡ ይህም ማለት እንስሳ አይደለንም ማለት ነው፡፡ በፍላጎት በእቅድ በማገናዘብ ስንኖር ፍላጎት ደግሞ ደስታ ነው ደስታ ደግሞ የስኬት ጉዞ፡፡ ወደ መጀምሪያው ሀሳብ ስንመለስ በተለያዩ የመረጃ ምንጮች የተከበብነው እኛ የምናነበው የምንሰማው የምናየው ነገር ምን ያህል አእምሮአችንን እየለወጠ መሆኑን የምናውቀው የቀረበልንን መረጃ ምንነት በውስጡ የያዘውን መልዕክት በሚገባ መረዳት ስንችል ነው፡፡ ለምሳሌ ቤተሰብህን ግደል እያለ በግልጽ የሚነግርህን ማስታወቂያ ወይም መረጃ ልትቀበለው አትችልም ምክንያቱም አእምሮህ አገናዝቦ ጥሩ አለመሆኑን ተረድተሃልና፡፡ በድብቅ ባልታየ ሀሳብ  Subliminal Message ቤተሰብህን ጥላ ናቃቸው ከዛም ግደል የሚል መረጃ ግን በተለያዩ ድብቅ መረጃዎች ቢቀርብልህ ቀስ በቀስ ቤተሰብህን መጥላት መናቅ ከዚያም አልፎ ወደ መግደል ደረጃ የምትደርስበትን አጋጣሚ መረዳት ግን አልቻልክም፡፡ እንግዲያውስ በአሁኑ ሰዓት እያየናቸው የሉት የምዕራብያውያኑ የመረጃ መስኮቶች በተለይ ሙዚቃ ፊልም ተከታታይ ፊልሞች ሪያሊቲ ሾዎች እንዲሁም ማስታወቂያዎች እያስተላለፉ ያሉት ባልታየ ድብቅ መረጃዎች ክምችት ነው፡፡ መግደል ደረጃ ላይ እንኳን ባትደርስ ቤተሰብን መናቅ ጓደኛን መጥላት ባልፈለከው መልኩ ለመጠጥ ለወሲብ ጉዳዮች መዳረጋችንን እየዘነጋነው ነው፡፡ በአንዳንድ ዜናዎች የምንሰማው የታዳጊ ወጣቶች አሰቃቂ የግድያ ታሪኮች ስንመለከት አንዱ አስቀያሚው ደረጃ ነው፡፡ እኛ ባላወቅነው መልኩ ሚዲያዎች እነርሱ በፈለጉት መልኩ እያንቀሳቀሱን እንደ አሻንጉሊት (ሮቦት) ቆጥረውናል መልዕክታቸውን በድብቅ እያስተላለፉ ነው፡፡
ሰብኮንሽየስ የሚባለው የአይመሮአችን ክፍል እጅግ መሰረታዊ የሚባሉትን የሰውነት ተግባራት ለምሳሌ የልብ ምት ሚዛናችንን መጠበቅ የጨጓራ ስርዓትን የሳምባ ምት የመሳሰሉትን ይቆጣጠራል፡፡ አንደንዴም ጠቃሚ የሆኑ አስበን የማናደርጋቸው ሪፍሌክስ አክሽን /ንጥቀት/  የሚባሉትን እንደ ማስነጠስ የአይን እርግብግቢትና ሰውነታችን የሚጎዳ ነገር ሲነካ ቶሎ ብለን ውሳኔ ለመስጠት የሚረዳን የአይምሮ ክፍል ነው፡፡ ይህን ሁሉ ተግባር እያመዛዘንን ብናደርገው ጉዳቱ የከፋ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ይህንን የአይምሮ ክፍል ምን ያክል እያወቅነው ነው? ምን ያክልስ እየተጠቀምንበት ነው? ምን አይነት ዳታስ እየሞሉት ነው? የማንነትህ መሪ ማን ነው? አንተ/አንቺ/ ማነህ? ማነሽ? ዘመኑ ሳይንሳዊ ፊውዳሊዝም መሆኑን አትዘንጋ፡፡ በቅኝ አዙር እየተገዛን ነው በአገዛዙ ስር ከሆንን የግድ ተገዢ መሆናችን አይቀርም፡፡ ማንነትህን እየተቆጣጠሩት ያሉት እነርሱ ናቸው ወይስ አንተ? አንተ ማነህ?

No comments: