Mar 31, 2015

ጎጆ አልባ ኗሪዎች



ጎጆ አልባ ኗሪዎች!!
********

ከጎጆ ቤት በላይ ያማረ ውብ ጥበብ
አይተን እንዳላየን ግርግር በወጀብ
ክፍላተ ዘመናት የጦርነት ናዳ
አገርን ለማፍረስ ጎጆን ልናናጋ
መሰረት ልንንድ ሴራ ስናበስል ውድቀት ሲሰናዳ
ትላንት የተካበው ዛሬ ሊፈራርስ ቁልቁል ስንዳዳ
ምናለ ብትሰጠን ምናለ ብንፈራ
አንዲት ልዩ ጥበብ አንዲት ልዩ ሥራ
ባንድነት በሕብረት አገር እንዲጠራ
በእውነት በእውቀት ዘመን እንዲበራ
ጎጇችን እንዲያምር ፍቅር እንዲዘራ!!
**********
ለ-ጎጆ አልባ ኗሪዎች!!

No comments: